Wednesday, August 14, 2013

ይህን ሁሉ እያከበሩ የሀይማኖት አባቶችን ዘንገተዋቸው ነው?? ወይስ ኮሚኒስት እንደሆኑ እያሳዩን ነው?!!¡!

በቢላል ጋዜጠኞች መታሠር የሲፒጄ ቅሬታ

በቢላል ጋዜጠኞች መታሠር የሲፒጄ ቅሬታ
Photo: በቢላል ጋዜጠኞች መታሠር የሲፒጄ ቅሬታ
ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነትና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅት - ሲፒጄ
የቢላል ራዲዮ ጋዜጠኞች መታሠር ያሣዘነው መሆኑን ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነትና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ አስታውቋል፡፡

ሲፒጄ ዐርብ፣ ነኀሴ 3/2005 ዓ.ም ከናይሮቢ ባሠራጨው መልዕክቱ ለራዲዮ ቢላል የሚሠሩት ሁለት ጋዜጠኞች ለአንድ ሣምንት ያህል ያለ ክሥ መታሠራቸው ያሣሰበው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ራደዮ ጣቢያው በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የሚስሊሞችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በስፋት ሲዘግብ መቆየቱንም ሲፒጄ አስታውቋል፡፡
የፀጥታ ኃይሎች ሐምሌ 26/2005 ዓ.ም ጋዜጠኞቹን ዳርሰማ ሶሪን ከቤቱ አጠገብ እንዲሁም ኻሊድ ሞሐመድን ወደሥራው እየሄደ ሳለ ይዘው ያሰሯቸው መሆኑን የራዲዮ ቢላል ኃላፊ ሞሐመድ ሐሰን የነገሩት መሆኑን ሲፒጄ አመልክቷል፡፡
ጋዜጠኞቹ በማግሥቱ ወደፍርድ ቤት ቢወሰዱም ፖሊስ ምርመራውን እስኪጨርስ በሚል በጥበቃ ሥር እንዲቆዩ መደረጉን አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች እንደጠቆሙት ሲፒጄ ገልጿል፡፡
ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነትና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ቡድን ሲፒጄ እስከአሁን አካሂጄዋለሁ ባለው ክትትልና ፍተሻ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ ገብቷል በሚል እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን ጨምሮ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ጉዳዮች እየተከታተለ የሚዘግበው የኢንተርኔት ራዲዮ ቢላል ዋሽንግተን፣ ጆሃንስበርግ እና አዲስ አበባ ላይ ፅሕፈት ቤቶች ያሉት መሆኑን አመልክቷል፡፡
ሲፒጄ የራሱን ክትትልና የዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን እማኝ አድርጎ ሲናገር የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሠልፈኞችን፣ የማኅበረሰብ መሪዎችን እና ነፃ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ውጤቶችን በመዝጋት ተቃውሞዎቹን ለማፈን እየጣረ መሆኑን በዚሁ መልዕክቱ ገልጿል፡፡
ስለሁኔታው ለቪኦኤ መግለጫ የሰጠው የሲፒጄ የምሥራቅ አፍሪካ አማካሪ ቶም ሮድስ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑን ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከዕለት ወደዕለት ለመረጃ እየጠበበች ያለችና ለዜናና ለመረጃ ሙሉ በሙሉ ዝግ እንደሆነችው ጎረቤቷ ኤርትራ ልትሆን ትችላለች የሚል ሥጋት እንዳለው የገለፀው ሮድስ ቀደም ሲል ተይዘው በእሥር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ጉዳይ እና የእሥር ቤት ሕይወታቸውን በቅርብ ለመከታተልም አዳጋች መሆኑን ሮድስ አመልክቷል፡፡
“ነፃ አስተሳሰቦችንና በእንዲህ ዓይነቱ ብሔራዊ ጉዳይ ላይ ያሉ አመለካከቶችን ለማፈን መሞከር - አለ ሮድስ በዐርቡ የሲፒጄ ዘገባ ላይ ባሠፈረው አስተያየቱ - መፍትሔ አያመጣም፡፡ እንዲያውም ‘መንግሥት የሚደብቀው አንዳች ነገር አለ’ የሚለውን ጥርጣሬ ይበልጥ ያባብሰዋል፡፡”
ጋዜጠኞቹ የተከሰሱት ሲፒጄ ‘ግልፅነት ይጎደለዋል’፤ ወይም ‘የተድበሰበሰ ነው’ በሚለው ፀረ-ሽብር ሕጉ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ሐምሌ 26/2005 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር የዋለው ዳርሰማ “የሙስሊሞች ጉዳይ” ይባል የነበረና የተዘጋ መፅሔት ላይም አምደኛ እንደነበረ ሲፒጄ አስታውሶ የመፅሔቱ ዋና አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸው ከየካቲት 2005 ዓ.ም፣ ማኔጂንግ ኤዲተሩ ሰሎሞን ከበደ ደግሞ ከሰኔ 25/2005 ዓ.ም ጀምሮ በእሥራ ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡
የመፅሔቱ ሁለት አዘጋጆች አክመል ነጋሽ እና ኮፒ ኤዲተሩ ይስሃቅ እሸቱም ሃገር ለቅቀው መሰደዳቸውን የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች እንደጠቆሙት ሲፒጄ አክሎ ገልጿል፡፡
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሣካም፡፡
ያለፉትንና የአሁኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጨምሮ ባለሥልጣናቱ በሚሰጧቸው መግለጫዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሥራው፣ ወይም በሚፅፈው ፅሁፍ ወይም ሃሣቡን በመግለፁ ምክንያት የሚታሰው ሰው እንደሌለና ከታሠረም የሚታሠረው በወንጀል አድራጎት መሆኑን፤ ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት እንደሚታይ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡
ለተጨማሪ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

የቢላል ራዲዮ ጋዜጠኞች መታሠር ያሣዘነው መሆኑን ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነትና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ አስታውቋል፡

'Salat Man' is symbol of resistance for Muslims in Ethiopia - Opinion - Al Jazeera English