Tuesday, July 31, 2012

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላለፉት ስምንት ወራት ሲያካሂድ የነበረው ሠላማዊ የተቃውሞ ሂደት

" ولا تهنوا ولا تحزنوا وأنتم الأعلون إن كنتم مؤمنين "
‹‹አትስነፉ፣ አትዘኑም፤ ምዕመናን እንደሆናችሁ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ›› ሱረቱል ኢምራን፤ 139

ስምንት አታካች ወራት፡፡ አታካች የተቃውሞና የጥያቄ ወራት፡፡ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላለፉት ስምንት ወራት ሲያካሂድ የነበረው ሠላማዊ የተቃውሞ ሂደት ከሁሉ በፊት ሠላምን በሚወደውና ስሙም ‹‹ሰላም›› በሆነው ጌታ አላህ ፊት የሚያስመሰግነው ነበር፡፡ በመቀጠልም ሙስሊም ባልሆነው ወገናችንና በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ፊት የተወደሰ ሆኗል፡፡ ነገር ግን፤ ሕገ ወጥ በሆኑትና በሙስሊሙ ደምና ላብ ሆዳቸውን ሞልተው ለሚያድሩት ህገ-ወጦቹ የመጅሊስ አመራሮችና በ
ሙስሊሙ ላይ ድብቅ አጀንዳቸውን ማራመድ ለሚሹት ጥቂት ባለስልጣናት ይህ ሠላማዊና ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ‹‹አክራሪነት፣ ጽንፈኛነት፣ አዲስ እስልምና፣ ወዘተ›› ነው፡፡
ዜና ስልጤ ዞን

ያለፈው እሁድ ማታ የተወካዮች ምክር አፈ ጉባኤ ወደ ስልጤ ዞን ዋና ከተማ (ወራቤ) አምርተው ነበር፡፡ ከዚያም የዞኑን ሰብሳቢና የካቢኒ አባላት ከሰበሰቡ በኋላ የሚከተሉትን ማስፈራሪያዎች አሳልፈው የገቡበት ጨለማ ሳይነጋ ወደ አዲስአበባ ተመልሰዋል፡፡

ትእዛዝ ቁጥር አንድ፡- ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ባለቤቱ ኒቃብ የምትለብስ ከሆነ እንዲያስወልቃት ይህን ካላደረገ ግን ከሥራ እንዲባረር፡፡ በዚህም ለተራው ህዝብ ማስተማሪያ እንዲሆኑ፡፡

ትእዛዝ ቁጥር ሁለት፡- እያንዳንዱ የዞኑ ነዋሪዎችም በነፍስ ወከፍ የሙስሊሙን ህዝብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አናውቀውም ብለው እንዲያወግዙና የሙስሊሙን ህዝብ ተቃውሞ አንደደግ
ፍም እንዲሉ እንዲገደዱና ፒቲሽን እንዲፈርሙ የሚል ነው፡፡

የአጋች ታጋች ድራማ በአወልያ፡፡

የአጋች ታጋች ድራማ በአወልያ፡፡
by: Hasen Safewan
ቀኑ ጁመዓ ነው፡፡ የእለት ጉርሴን ፍለጋ ቀኑን ሙሉ የደከመውን አካሌን ለማሳረፍ ወደ ቤቴ ከማምራቴ በፊት የአወሊያ መስጊድ የአዛን ጥሪን ሰምቼ የኢሻ ሰላቴን ለመስገድ ወደ መስጊድ አቀናሁ የአዛን ጥሪውን ያደረገው ሙአዚን ለሰላት እንድንዘጋጅ ኢቃም አድርጐ እንዳበቃ የመስጊዱ ኢማም የኢሻ ሰላት ማሰገድ ጀመሩ ሰላቱ ተሰግዶ እንዳበቃ እጅግ በጣም ጥቂት የሚባሉት ከመስጊድ ወጥተው እንደሄዱ የሱና ሰላቴን ሰግጄ ዱዓ በማድረግ ላይ ሳለሁ የመስጊዱ ዙሪያ በፌዴራል ፖሊስ እንደተከበበ ሹክሹክታ ተሰማ፡፡ ሙሰሊሙ እዚህ ግባ የማይባል የመብት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በየመስጊዱ የሚደርስበትን ወከባ ማየት የተለመደ ስለሆነ በሰዓቱ ለነገሩ ክብደት አልሰጠሁትም ነበር፡፡

Monday, July 30, 2012

የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም


http://www.bilalcommunication.com/bci/images/photo%20a.jpg
Wallah, last night we served over a thousand people and this was the largest gathering FHF ever had. I personally want to thank the volunteers for all your hard work and Masha'Allah you guys are all great (I'm sure everyone else would agree with me). Without you guys we wouldn't have been as successful as we were! Jazakhallah khair for all you have done and I am glad I had the pleasure/honor of working with each and everyone of you. May Allah (swt) reward all of you immensely for your hard work! I LOVE ALL OF YA'LL.
 Nuru Yimam,
Sedeqa and Unity organizing Chair
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጽያዊያን ሙስሊሞች ታላቅ የዓንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም አካሄዱ። በዚህ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢው የሚኖሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት ፕሮግራም በሃገር ቤት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰውን በደልና ግፍ ከማውገዝ በተጨማሪ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም ገልጾል። ትላንት ቅዳሜ ጁላይ 28 በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ በእስር ላይ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች አላህ ከጨቆኞች እስር ነጻ እንዲያወጣቸው እንዲሁም በፖሊስ ድብደባና ጭስ ለተጎዱ ወገኖች አላህ አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ዱአ ተደርጎል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የሚገኙት በድር ኢትዮጽያ፣ ፈርስት ሂጅራ፣ ነጃሽ የፍትህ ካውንስል እና ሰላም ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት የኢትዮጽያ ሙስሊም ቅንጅት መስርተዋል። ቅንጅቱም የመጀመሪያ የጋራ ስራ ያደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ሀሙስ ኦገስት 2 ያካሂዳል። ኢንሻአላህ በቀጣይም ቅንጅቱ የታሰሩ እንዲፈቱና የሙስሊሙ መሰረታዊ መብት እንዲከበር ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል::
http://www.bilalcommunication.com/bci/images/photo-b.jpg

በአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ የቢላል ኮሚኒቲ ሴንተር ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ጁላይ 28 አካሄደ:: በዚህ ፕሮግራም ላይ የተካፈሉት ሙስሊሞች በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉን የመብት ረገጣ በመቃወም እየተደረገ ያለዉን ሰላማዊ ትግል እንዴት መርዳት እንዳለባቸዉና የመፍትሄ አቅጣጫም ተወያይተዉ ማስቀመጣቸዉን ምንጮች አስታዉቀዎል:: ከመፍትሄ አቅጣጫዎቹም መካከል ሁሉም አባል በዱአ እንዲጠናከር, በሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለዉን በደል በመቃወም ፊርማ ማሰባሰብ, የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፎችን ማካሄድና ገንዘብ ለማሰባሰብ ወስነዎል:: በሰደቃዉ ፕሮግራም ላይ በተካሄደዉ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ወደ አስር ሺህ(10,000) ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻላቸዉን አሳዉቀዎል:: ይህም የተሰበሰበዉ ገንዘብ መንግስት በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ በወሰደዉ የሀይል እርምጃ ሂወታቸዉን ላጡ ሙስሊሞች ቤተሰቦች, በጥቃቱ ለቆሰሉና ለተጎዱ እንዲሁም በእስር ላይ ሆነዉ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ንፁሀን ሙስሊሞች መርጃ እንደሚዉል ተገልፆል::የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም ከኢትዮጲያ አልፎ የተለያዩ የአለም ሀገራት በሚኖሩ ኢትዮጲያዉያን እየተካሄደ ይገኛል:: ይህ ሁላ በአለም ሀገራት እየተካሄደ የሚገኘዉ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም በኢትዮጲያ የሚካሄዱትን የአፍሪካ የመሪዎችን ስብሰባ ለማደናቀፍ ይሆን??? መልሱን እዉነት ከዘገቡ ለሚያቅራቸዉና ለሚያማቸዉ ለኢቲቪ ጋዜጠኞች ትተን እናልፈዎለን!! አላህ ሰደቃቸዉን ይቀበላቸዉ::
 
ነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር በሳንያጎ ጁላይ 29/2012 ታላቅ የአንድነት የስደቃና ፕሮገራም በደማቅ ሁኔታ አከናወነ፡፡ 800-1000 የሚሆኑ መስሊምና ክርስተያኖች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሙሰሊሞች ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ መፍጠር እና የፓናል ውይይት ተደረጓል፡፡
በዝግጀቱ ላይ የነጃሺ ጀማኣ አባላት፤ የኦሮሞ ኮሚኒቲ አባላት፤ ክርስተያን ወገኖች እና የቢላል ጀማኣ አባላት ከሎስ አንጀለስ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ዝግጀት ላይ የኢትዮጰያ ሙሰሊሞች እያደረጉት ያለውን ሰላማዊ ትግል ሁሉንም ወገን ያሰደመመና እሰከ መጨረሻ ከጎናቸውእንደሚቀሙ ቃል ገብተዋል፡፡ በቀጣይ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማደረግ እንደመፍትሄ ሃሰብ ቀርቧል ቀኑን ለወደፊት ይገለፃል፡፡

የወቅቱ የኢትዮጵያውያን ሙስሉሞች ጥያቄ እና በኢትዮጵያ ያሇው አዴሎዊ ስርዓት

የወቅቱ የኢትዮጵያውያን ሙስሉሞች ጥያቄ እና በኢትዮጵያ ያሇው አዴሎዊ ስርዓት

ይዴረስ ሇመሊው ኢትዮጵያውያን
ሰሊምታችን እና መሌካም ምኞታችን ከሁለም ነገር ይቀዴማሌ፡፡ ይህን መሌእክት ሇእናንተ ሇወገኖቻችን እንዴንፅፍ ያነሳሳን ምክንያት አንዴም በሃገሪቱ በመንግስትም ሆነ በማንኛውም ዜጋ ስሇሚከናወኑ ጉዲዮች መረጃ የማግኘት መብታችሁን ከማክበር ሲሆን በላሊ በኩሌ ዯግሞ ሰሞኑን የኢትዮጵያ የራዱዮ እና የቴላቪዥን ጣቢያዎቻችን ከወትሮው ሇየት ያሇ የጭንቅ ቀን አይነት መረጃ ማቅረብን በማዘውተራቸው አንዴ ሇህዝብ ግሌፅ ሉሆን የሚገባ እውነታ በመኖሩ ይሄንን ሃሊፊነት ሇመወጣት ነው፡፡
Read Full Article

Sunday, July 29, 2012

What happen on July 13th, 2012 in Addis Ababa ?

በመዲናችን በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግፍ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ህዝቦች
         ልብ የሚሰብረውና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተፈፀመው እጅግ ኢ‐ህገመንግስታዊ እና የጭቃኔ ተግባር ከተፈፀመ እነሆ እንደ ቀልድ ሶስት ቀናት አለፈው፡፡ ጉዳዩ ታይቶ የማይታወቅ እንደመሆኑና በየትኛውም መለኪያ ምክንያት ሊሰጠው የማይችል እንደመሆኑ መጠን እንዲህ በቀላሉ ሲታለፍ ሁለት ነገሮችን ያሳያል፡፡ አንድም የህዝበ ሙስሊሙን ለሰላም ሲል ደሙን እና ህይወትን እንኳን እንደሚገብር ያሳየበት በሌላ በኩል ግን እንዲ...ህ አይነት ግፍ ተፈፅሞ እንኳን ሰላማዊ ነን በሚል ይህ ግፍ ድጋሜ ላለመከሰቱ ዋስትና በሌለበት ሁኔታ ለጭካኔ እርምጃ ድጋሜ እድል ሊሰጥ እንደሚችል፡፡ በእርግጥ ተጨባጩ የሚያሳየን የመጀመሪያውን ሙስሊሙ የሰላሙን አማራጭ እስከመጨረሻ እንጥፍጣፊ ድረስ እንደሚከተል፡፡ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ለህዝብ የሚያቀርቡት መረጃ ለህሊና የሚከብድ ነውና ህዝባችንን ሊያደናግር ስለሚችል ጥቂት ስለአሳዛኙ ክስተት ልንል ወደዱ፡፡ ሰለባ ከነበሩት ወንድሞችና እህቶች ያደመጥናቸውን በጥቂቱ ቀንጭበን ብናይ መንግስት
አይኑን በጨው አጥቦ በሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅቶቹ ያስደመጠን ድራማ አይደለም በእውነትነት ሊቀበሉት ህግ በሚተገበርበት ሃገር ቢሆን ኖሮ በክስ የሚያስፈርድ ወንጀል በሆነ ነበር፡፡
Read Full Article

ዲናችንን ለመጠበቅ ምላሽ የሚሹ 68 ወሳኝ ጥያቄዎች



ዲናችንን ለመጠበቅ ምላሽ የሚሹ 68 ወሳኝ ጥያቄዎች
ቀጣይ እርምጃዎቻችን ምን ይሁኑ?
መንግሥት የሙስሊሙን የመብት እንቅስቃሴን በማጠልሸት ለማጥቃት መወሰኑን ሰማን፡፡ ‹‹ኮሚቴው ያደራጃቸውን ቡድኖች በማሰማራት አወሊያን ዘረፉ፣ ጥቃት ፈጸሙ፤የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባን ሆን ብለው ለመበጥበጥ ያደረጉት ሙከራ በፌደራል ፖሊስና በሕዝቡ ትብብር ከሸፈ፡፡›› እና መሰል መግለጫ በመስጠት ብሎም ድራማ በማዘጋጀት ኮሚቴዎቻንንም ሆነ እንቅስቃሴው ዉስጥ ያሉትን ለማጥቃት መዘጋጀቱን ሰማን፡፡ ዕቅዳቸው ደግሞ ሙስሊሙ ዳግም በማያንሰራራበት መልኩ ለማጥቃት ነው፡፡ ታዲያ ዝም ብሎ ማየት ወንጀሉ ምነኛ ከበደ? እስቲ ተወያዩበት ምን ምን ብናደርግ ጸረ-ኢስላም ዘመቻውን በመግታቱ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ እንችላለን? እኔ ለመነሻ ስለዲኔ ይህን ልበል፡፡ የናንተንም አስነብቡን፡፡ ይህን መነሻ ሃሳብ ኮፒ እያደረጋችሁ እስከ ገጠር ድረስ አስነብቡ፡፡ ተወያዩበት፡፡ እናንተው በሚያመቸው መልኩ አሻሽሉት፡፡ አዳብሩት ለጥያቂውም መልስ በመሻት እንተግብር፡፡