ዜና ስልጤ ዞን
ያለፈው እሁድ ማታ የተወካዮች ምክር አፈ ጉባኤ ወደ ስልጤ ዞን ዋና ከተማ (ወራቤ) አምርተው ነበር፡፡ ከዚያም የዞኑን ሰብሳቢና የካቢኒ አባላት ከሰበሰቡ በኋላ የሚከተሉትን ማስፈራሪያዎች አሳልፈው የገቡበት ጨለማ ሳይነጋ ወደ አዲስአበባ ተመልሰዋል፡፡
ትእዛዝ ቁጥር አንድ፡- ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ባለቤቱ ኒቃብ የምትለብስ ከሆነ እንዲያስወልቃት ይህን ካላደረገ ግን ከሥራ እንዲባረር፡፡ በዚህም ለተራው ህዝብ ማስተማሪያ እንዲሆኑ፡፡
ትእዛዝ ቁጥር ሁለት፡- እያንዳንዱ የዞኑ ነዋሪዎችም በነፍስ ወከፍ የሙስሊሙን ህዝብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አናውቀውም ብለው እንዲያወግዙና የሙስሊሙን ህዝብ ተቃውሞ አንደደግ

ፍም እንዲሉ እንዲገደዱና ፒቲሽን እንዲፈርሙ የሚል ነው፡፡
ከዚያም ጧቱኑ ይህን ለመከወን የተንቀሳቀሱት ካቢኒዎች ሙስሊም የኢህአዲግ አባላትን በመሰብሰብ ከላይ የተቀበሉትን ‹‹ትኩስ ድንች›› ለአባላቱ አስተላልፈዋል፡፡ የድርጅቱ አባላቶች ግን በአንድ ድምፅ ትእዛዙን እንደማይቀበሉና በዚህ ምክንያት ከሥራ ካባረሯቸውም ምክንያት ጠቅሰው ደብዳቤ እንዲፅፉላቸው በፅኑ ጠይቀዋል፡፡ በመጨረሻም ከስብሰባ ሲወጡ እንዲፈርሙ ቢታዘዙም ባለፈው ጊዜ ‹‹የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች አክራሪዎችንና አሸባሪዎችን ተቃወሙ፡፡›› ተብሎ በኢቲቪ የተሰራውን የሀሰት ዜና አይነት እንዳይሰራባቸው በመስጋት አቴንዳንስ ላይ አንፈርምም ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ስብሰባው የቀን ሙሉ የነበረ ሲሆን በጧቱ ስብሰባ አቴንዳንስ ላይ የፈረሙት ፊርማ ያለአግባብ ለሌላ ጥቅም ከዋለ እነርሱ ሌላ ፒቲሽን አሰባስበው ሀሰትነቱን እንደሚያጋልጡ ተናግረዋል፡፡
እንደሚታወሰው ባለፈው ሳምንት የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች የሙስሊሙ ህዝብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን እንደተቃወሙ የሚያሳይ ምስል የያዘ ዜና በኢቲቪ ተላልፎ ነበር፡፡ እውነታው ግን ኢቲቪ ላይ እንዳየነው አይደለም፡፡ ሰልፈኞቹ የወራቤ ነዋሪዎች ሳይሆኑ ከስልጤ ዞን ስምንት ወረዳዎች በስምንት የነፃ አይሱዙዎች የመጡ ናቸው፡፡ የወረዳ ካድሬዎችና በአበል የተሰበሰቡ ችግርተኛና ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎችን ያካተተ ሰልፍ ነበር፡፡ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሰዎች እንደነገሩን ከየወረዳው የተሰበሰቡት ሰዎች መመለሻ አጥተው በወዳጅ ዘመድ እርዳታ ወደቤታቸው እንደተመለሱ ታውቋል፡፡ አብዛኞቹም እየሆነ ያለውን የማያውቁ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ጧት ማለዳ ላይ ግርግርና ሰልፍ መኖሩን በአይናቸው ከማየታቸው በስተቀር የተደረገው ሰልፍ የወራቤ ከተማ ነዋሪዎችን እንደማይመለከት የሚናገሩት የወራቤ ነዋሪዎች ሌላ የማስተባበያ ሰልፍ ለማድረግ ቢጠይቁም አልተፈቀደላቸውም፡፡ ነገር ግን ፒቲሽን አስገብተው ሰልፉ እነርሱን እንደማይወክል አሳውቀዋል፡፡ በገጠርማው የዞኑ አካባቢዎች ላይ ግን በግዳጅ የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንዲቃወሙና ፊርማ እንዲፈርሙ እየተገደዱ ነው፡፡
በተያያዘ ዜናም ደማቁን የስልጤ ዞን አንድነትና የሶደቃ ፕሮግራም አደራጅተዋል የተባሉ ባለሀብትና ኢማም (ቁጥራቸው አራት ይጠጋል) በፖሊስ እየተፈለጉ መሆኑ ታውቋል፡፡
ወደመጀመሪያው ዜናችን ስንመለስ የአቶ አባዱላ ትእዛዝን እንደማይቀበሉ የሚናገሩት የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች በዲናቸው እንደማይደራደሩና እየተጫነባቸው ያለውን አዲስ የአህባሽ አስተሳሰብ እንደማይቀበሉ አበክረው ገልፀዋል፡፡

No comments:
Post a Comment