መላው የኢትዮጵያ ሕዝም ሆነ መንግስት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ጥያቄያችን በጣም ቀላልና የፖለቲካ ጥያቄ አለመሆኑን የተረዳሁት በሥፍራው የነበሩ አንዳንድ የፖሊስ አባላት በግርግሩ መሐል ከሚያወጣቸው የተደበላለቁ ቃላት ነው፡፡ አንዳንዶቹ እንዳትመቷቸው እያሉ ሲጦሁ ሌላኛው ጺም ያሳደጉትን አጥብቃችሁ ያዙ ሲል የሌላው እምነት ተከታይ የሚያበቅለው የጽድቅ ጺም ሙስሊሙ የሚያበቅለው የሽብር ጺም ተደርጐ መወሰዱ እጁጉን አሳዘነኝ፡፡ የጺሙ ጉድማ መች በዚህ አበቃ በአንዋር መስጊድ ቅዳሜ ቀን በተደረገው ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ደህንነቶቹ ፊታቸውን ሸፍነው ከባድ አመጽ እንደሚካሄድ አስመስለው የፖሊስ ኘሮግራም ማድመቂያ ኣድርገው ሰላት ለመስገዱ የገቡ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ጺም ስላሳደጉ ብቻ ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ እንደው ማሸበር፣ አደጋ ማድረስ ቢፈለግ እራስን አጋልጣ ነው እንዴ) ሊበላት ያሰባትን አማራ ችግራ ናት ይላታል ካልሆነ በስተቀር፡፡ ከመስጊድ ወጥተን ወደ ተዘጋጀልን ካሚዮን ሲወስዱን ከአጠገቢ የነበረው አንድ ፖሊስ አይዛችሁ ይህንን ሁሉ በደላችሁን እግዛብሄር ያያል ሲለኝ በአውንታ እራሴን ከመነቅነቅና በእንባ ከመታጠብ ውል በዱላ የዛለው አካሌ በቂ መልስ ለመስጠት ተስኖት ነበር፡፡ ለአንድነት ሰደቃው ምግብ ለመሥራተ ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት እናቶቻችንና እህቶቻችን ላይ ሲደርስ የነበረው ስቃይ እነሱን ሴት የወላቸው አይመስልም ነበር፡፡ ወደ ተዘጋጀልን መኪና አምርተን በአንድ ካሚዩን ከሁለት መቶ በላይ ሰው እርስ በራሳችን ደራርበው አንገታችንን ወደ ታች እንድናቀረቅር ትዕዛዝ አስተላልፈው ካጐሩን በኋላ ትንፋሽ አጥሮት ትንፋሽ ለመውሰድ ቀና የሚል ከተገኘ አናቱ ላይ ለሚያርፈው የፌዴራል ዱላ እራሱን ማዘጋጀት የግድ ነበር፡፡ አሰቃሲው ጉዞ ተጀምሮ ትንሽ እንደተጓዝን ከየአቅጣጫው አላሁ አክበር የሚል ጽምስ ስንሰማ ሕዝቡ ከቤት እንደወጣ ብናውቅም በውጭ የነበረውን ትዕይነት መመልከት እንዳንችል የፌዴራሉ ዱላና የተኩሱ እሩምታ ጋሬጣ ሆኑብን፡፡ መቼም እንዳይደርስ የለ ከረዠም አሰልቺ ጉዞ በኋላ ወደ ተዘጋጀልን የድቄት መጋዘን ስንደርስ ውረዱ የሚል ትዖዛዝ ሲመጣ አየር ለመሳብ ያልተጣደፈ አልነበረም፡፡ ከነበረው ሩቅና አስልዊ ጉዞ ሁላችንም ሸዋ ሮቢት የወሰዱን መስሎን ነበር፡፡ ለካ ያ ሁሉ ጉዞ ኮልፌ የፖሊሶች ማሰልጠኛ ፈጥኖ ነበር፡፡ ዱቄት በተከማቸበት መጋዘን ውስጥ እንደገባን ሰላማዊ አየር በማግኘታችን ለታላቆ አላህ ምስጋናችንን ከማቅረብ አልቦዘንም፡፡ በቀጣዩ ቀን የነበረው ወሎአችን በአብዛኛው ቃል በመስጠትና በመቀበል ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ቃል የሚቀበሉት ፖሊሶች በሶት ቡድን ተከፍለው ቃላችንን ለመቀበል ከተዘጋጁና የቪድዮ ካሜራቸውን ከወደሩ በኋላ እንደ እጣ ፈንታችን አንድ በአንድ እየተጠራን ቃል ለመስጠት ገባን፡፡ ቃል ተቀባይ መርማሪዎቹ ከሚጠይቁት ጥያቄ መረዳት እንደቻልኩት የተፈለገው ሰደቃውን ያዘጋጁት ኮሚቴዎቹ ናቸው እንድንል ሲላቸው በማግባባት አልሆንላቸው ሲል በማስፈራራት ኮሚቴዎቹን የሚወንጅል ቃል በመዝገቡ ላይ ለማስፈርና በካሜራ ለመቅረጽ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ በእርግጥ የዚህ ዓይነት መንፈስ የነበረው በሁሉም መርማሪዎች ሳይሆን በጥቂቶቹ ላይ ነበር፡፡ በቅዳሜው ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ወደ ሰንዳፋ የወሰዳቸውን ሙሰሊም ወንድሞቻችንን ጥፋተኛ ነኝ ያለው እየተለቀቀ ጥፋተኛ አይደለሁም የሚል ካለ ሸዋ ሮቢት እንደሚላክ ማስፈራሪያ እየተሰጠው ባዘጋጁት ካሜራ እየቀረጹ እንደለቀቁ የገፈቱ ቀማሽ የነበረ የአኼራ ወንድሜ አጫወተኝ፡፡ በውሸት ሰውን ለመወንጀል ማስረጃ ለመሰብሰብ ከመድከም ይልቅ ሀቁን ለማወቅ ቢደክሙ ኖሮ መንግስትንም እያገለገሉትን ያለውን ፓርቲ ከመንኮተኮት በታደጉት ነበር፡፡
የውጭው ትእይንት
በውጭ የነበረውን ትዕይንት የእኔን መታገት ሰምተው ወደ አወሊያ ከመጡት ቤተሰቦቼ ክፉኛ ድብደባ የደረሰበት ወንድሜ የነበረውን ትዕይንት ሲነግረኝ እኛ ላይ የደረሰው ድብደባ የተመራቂ ፖሊሶቹን ዱላ ማሟሻ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሙሰሊሙ የወንዶሞቹን የድረሱልኝ ጥሪ ሰምቶ እጅና እግሩን ይዞ በድንጋጤ ወደ አወሊያ በተመመበት ወቅት መንገድ ላይ የጠበቀው ጭለማን ተገን አድገው የመሸጉ የፌዴራል ፖሊስች ርህራሄ ያልተሞላበት ዱላና አስለቃሽ ጭስ ነበር፡፡ በጣይ የሚገርመው በአካባቢው የነበሩና በሁኔታው የተዳነገጡ የሌላ እምነት ተከታዮች የሁኔታውን ምንንት ለማወቅ ፖሊሶቹን ሲጠይቁ ከአንዳንዱ ፖሊሶች ይሰጥ የነበረው ምላሽ ሙስሊሞቹ ክርስቲያኖቹን እየጨፈጨፉ ነው ውጡና አግዙን ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የሌላ እምነት ተከታዮች ለፖሊሶቹ ሲሰጡት የነበረው አጻፋዊ ምላሽ በድብደባው የተጐዱትን ሙሰሊሞች ቤታቸው አስገብተው በመሸሸግና በማዳን ለሕዝብ እልቂት ምንም ደንታ የሌላቸው ክፉ ኣሳቢዎችን ሰንካላ ፍላጐት ማክሸፍ ነበር፡፡ በምሽቱ ሙስሊሞቹ ላይ ሲያርፍ የነበረው ዱላ አህባሽ፣ሰለፊያ፣ሱፍያ፣ወሐብያ ብሎ ሳይለይ ወደ አወሊያ በተመመው ሕዝብ ላይ ነበር፡፡ ልብ ያለህ ልብ በል፡፡
መጪው ግዜ ረመዳን ነው ~~~~~~~~~~~~~~^~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ሁላችንም በያለንበት ዱአ እናድርግ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ~ ያ አላህ የኛን ጉዳይ ለማን ትተውብናለህ ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ¤¤ እባክህን እርዳን ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ¤¤¤¤¤¤¤ እኛ ደካሞች ነን ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሁሌም ጭንቀታችን ና ሀዘናችንን የምናሰማው ለአንዱ ፈጣሪያችን ላንት ብቻ ነው !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
by: Hasen Safewan
No comments:
Post a Comment