Wallah, last night we served over a thousand
people and this was the largest gathering FHF ever had. I personally want to
thank the volunteers for all your hard work and Masha'Allah you guys are all
great (I'm sure everyone else would agree with me). Without you guys we
wouldn't have been as successful as we were! Jazakhallah khair for all you have
done and I am glad I had the pleasure/honor of working with each and everyone
of you. May Allah (swt) reward all of you immensely for your hard work! I LOVE
ALL OF YA'LL.
Nuru Yimam,
Sedeqa and Unity organizing Chair
በአሜሪካ ዋሽንግተን
ዲሲ ና አካባቢው የሚኖሩ
ኢትዮጽያዊያን ሙስሊሞች ታላቅ የዓንድነትና
የሰደቃ ፕሮግራም አካሄዱ። በዚህ
ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ
በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው
የሚኖሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት ፕሮግራም
በሃገር ቤት መንግስት በሙስሊሞች
ላይ የሚያደርሰውን በደልና ግፍ
ከማውገዝ በተጨማሪ የህዝበ ሙስሊሙ
ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ
እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም
ገልጾል። ትላንት ቅዳሜ ጁላይ
28 በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ
በእስር ላይ ለሚገኙ ወንድሞችና
እህቶች አላህ ከጨቆኞች እስር
ነጻ እንዲያወጣቸው እንዲሁም በፖሊስ
ድብደባና ጭስ ለተጎዱ ወገኖች
አላህ አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ዱአ
ተደርጎል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ
በአሜሪካ የሚገኙት በድር ኢትዮጽያ፣
ፈርስት ሂጅራ፣ ነጃሽ የፍትህ
ካውንስል እና ሰላም ፋውንዴሽን
በጋራ ለመስራት የኢትዮጽያ ሙስሊም
ቅንጅት መስርተዋል። ቅንጅቱም
የመጀመሪያ የጋራ ስራ ያደረገው
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ
ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት
ሀሙስ ኦገስት 2 ያካሂዳል። ኢንሻአላህ
በቀጣይም ቅንጅቱ የታሰሩ እንዲፈቱና
የሙስሊሙ መሰረታዊ መብት እንዲከበር
ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ትግሉን
አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ
ተችሏል::
በአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ የቢላል ኮሚኒቲ ሴንተር ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ጁላይ 28 አካሄደ:: በዚህ ፕሮግራም ላይ የተካፈሉት ሙስሊሞች በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉን የመብት ረገጣ በመቃወም እየተደረገ ያለዉን ሰላማዊ ትግል እንዴት መርዳት እንዳለባቸዉና የመፍትሄ አቅጣጫም ተወያይተዉ ማስቀመጣቸዉን ምንጮች አስታዉቀዎል:: ከመፍትሄ አቅጣጫዎቹም መካከል ሁሉም አባል በዱአ እንዲጠናከር, በሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለዉን በደል በመቃወም ፊርማ ማሰባሰብ, የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፎችን ማካሄድና ገንዘብ ለማሰባሰብ ወስነዎል:: በሰደቃዉ ፕሮግራም ላይ በተካሄደዉ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ወደ አስር ሺህ(10,000) ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻላቸዉን አሳዉቀዎል:: ይህም የተሰበሰበዉ ገንዘብ መንግስት በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ በወሰደዉ የሀይል እርምጃ ሂወታቸዉን ላጡ ሙስሊሞች ቤተሰቦች, በጥቃቱ ለቆሰሉና ለተጎዱ እንዲሁም በእስር ላይ ሆነዉ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ንፁሀን ሙስሊሞች መርጃ እንደሚዉል ተገልፆል::የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም ከኢትዮጲያ አልፎ የተለያዩ የአለም ሀገራት በሚኖሩ ኢትዮጲያዉያን እየተካሄደ ይገኛል:: ይህ ሁላ በአለም ሀገራት እየተካሄደ የሚገኘዉ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም በኢትዮጲያ የሚካሄዱትን የአፍሪካ የመሪዎችን ስብሰባ ለማደናቀፍ ይሆን??? መልሱን እዉነት ከዘገቡ ለሚያቅራቸዉና ለሚያማቸዉ ለኢቲቪ ጋዜጠኞች ትተን እናልፈዎለን!! አላህ ሰደቃቸዉን ይቀበላቸዉ::
ነጃሺ
ኢስላማዊ ማህበር በሳንያጎ ጁላይ 29/2012 ታላቅ የአንድነት የስደቃና ፕሮገራም በደማቅ ሁኔታ አከናወነ፡፡ ከ 800-1000 የሚሆኑ
መስሊምና ክርስተያኖች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሙሰሊሞች ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ መፍጠር እና የፓናል ውይይት ተደረጓል፡፡
በዝግጀቱ ላይ የነጃሺ ጀማኣ አባላት፤ የኦሮሞ ኮሚኒቲ አባላት፤ ክርስተያን ወገኖች እና የቢላል ጀማኣ አባላት ከሎስ አንጀለስ ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ዝግጀት
ላይ የኢትዮጰያ ሙሰሊሞች እያደረጉት ያለውን ሰላማዊ ትግል ሁሉንም ወገን ያሰደመመና እሰከ መጨረሻ ከጎናቸውእንደሚቀሙ ቃል ገብተዋል፡፡
በቀጣይ ታላቅ
ሰላማዊ ሰልፍ ለማደረግ እንደመፍትሄ ሃሰብ ቀርቧል ቀኑን ለወደፊት ይገለፃል፡፡
No comments:
Post a Comment