ድምፃችን ይሰማ
ሰሞኑን መንግስት ተብሊግ ጀመዓ ላይ እየደረገ ያለው ዘመቻ እጅግ ግራ የሚያጋባ ሆኖአል፡፡ መንግስት አህባሽን ከሊባኖስ እንዳመጣ የተብሊግ ጀመዓ አመራሮችን “ወሃቢያን” ለማጥፋት አብረን መስራት አለብን የሚል ከባድ ጫና ቢያሳድርባቸውም በሳል አመራሮቹ እጃቸውን አዚህ ጉደይ ውስጥ እንደማይከቱ ግልጽ የሆነ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሰሞኑን ይህን አቋማቸውን መበቀያ በሚመስል ሁኔታ አመራሮቹን ማሰርና ማንገላታቱን ተያይዞታል፡፡ በዛሬው ዕለትም ከጀመዓው አመራር (ሹራ) አባላት መካከል ኡስታዝ ሙሐመድ ዐብዱልቃድርና ሌሎች ለጊዜው ስማቸውን ማወቅ ያልተቻለ ግለሰቦች ተይዘዋል፡፡ ከተለያዩ ክልሎችም እስካሁን 90 አካባቢ የሚሆኑ የጀመዓው አባላት መያዛቸውን ለጀመዓው ከሚቀርቡ ምንጮች ማወቅ ተችሏል፡፡
ድምፃችን ይሰማ
ማስታወሻ!!!
የፊታችን ጁምአ በዝምታ ነዉ ተቃዉሟችንን የምንገልፀዉ ሲባል ባለፈዉ ጁምአ እንዳደረግነዉ በአስደንጋጭ ዝምታ እጅ ለእጅ በመያያዝ አፉችንን በፕላስተር ወይም በመሀረብ ወይም በጨርቅ በመሸፈን የተለያዩ መፈክሮችን በብዛት በብዛት በመያዝ ተቃዉሟችንን መግለፅ ይጠበቅብናል:: ማንኛዉም አይነት ሁከት, ረብሻ እና ብጥብጥ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎን ከማድረግ መቆጠብ ይኖርብናል:: የጁምአ ሰላት ከተጠናቀቀ ቡሀላ ሁላችንም ባለንበት ቦታ በመቀመጥ ተቃዉሟችንን መግለፅ ይጠበቅብናል:: ከሰላማዊዉ አካሄዳችን ዉጪ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ስንመለከት በሞባይላችን መቅረፅ እንዳለብን አንዘንጋ::ማንኛዉም አይነት በዝምታ ተቃዉሟችንን ሊገልፅልን የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ሁሉም በአንድነት በመናበብ ማስኬድ ይኖርብናል:: ይህ የዝምታ ተቃዉሞ ፀረ ሰላም ሀይሎች ያሴሩብንን ሴራ በቀላሉ ስለሚያከሽፍና ለክርስትና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ሰላም ወዳድ መሆናችንን እና በኢቲቪ የሚነዛዉ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ዉሸት እንደሆነ ማሳየት ያስችለናል:: በመጨረሻም የኢትዮጲያ ህዝበ ሙስሊም ያነሳዉን ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች መዘንጋት አይኖርብንም:: እነዚህም 1ኛ. የመጅሊስ አመራሮች በሙስሊሙ የተመረጡ ስላልሆኑ ይወረዱና ህዝበ ሙስሊሙ ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት የእምነት መሪዎቻችንን እንምረጥ::2ኛ. መንግስት ከሊባኖስ ያስመጣዉ አህባሽ የሚባለዉ ከኢስላም የወጣን አስተምህሮ መንግስት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በግዳጅ ለመጫን የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ ያቁምልን:: 3ኛ. አወልያ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ብቸኛ ተቖም በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በሚያምናቸዉና በሚመርጣቸዉ ቦርድ ይተዳደር የሚሉ ናቸዉ:: ከነዚህ 3 ጥያቄዎች ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ ለመንግስት አላነሳንም::" ኢስላማዊ መንግስት መመስረት ጥያቄያችን አይደለም!!!!" አክራሪነትን እናስፉፉ ብለንም አልጠየቅንም". በሀይማኖት ሽፉን አንዳችም ድብቅ አላማ የለንም:: ይህንን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ሊያዉቀዉ ይገባል:: በመንግስት ሚዲያዎች የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስለተነዛ ሶስቱ ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎቻችን ህገ ወጥ ሊሆን አይችልም:: ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበርልን ነዉ ያልነዉ!! የሀገራችን ሰላም ከማንም በላይ ያሳስበናል:: የፊታችን ጁምአ የምናካሂደዉን የዝምታ ተቃዉሞ ሂደት ላልሰሙት አሰሙ::እዉነት ሁሌም አሸናፊ ናት!! አላሁ አክበር!!
ድምፃችን ይሰማ
ሁለተኛው የትግላችን ምእራፍ ጅማሮ
ዛሬ ላይ ሁነን ከአመት ወዲያ አሻግረን ስናስብ ብዙ ነገሮች በሚገርም ሁኔታ ተለዋውጠዋል፡፡ በለውጡ ሂደትም ለታሪክ የሚተርፍ ትምህርት አገኘን፡፡ እኛም ለሌሎች ብዙ አስተማርን፡፡ ውድ ኮሚቴዎቻችን ይሉት እንደነበረው በተጨባጭ ያስመዘገብነው ግን ያማረ አካሄድን እንጂ ያማረ ውጤትን አልሆነም፡፡ በእርግጥ አላህ ዘንድ የትኛው የተሻለ ሆኖ ታስቦልን እንደሆነ ማናችንም አናውቅም፡፡
አህባሽ በአራት እግሩ ዘው ብሎ ገብቶ መስጂዶቻችንን ማወክ በጀመረባቸው ወቅቶች አብዛኞቻችን በቤታችን ያጎነበስንበትና ቀልባችን የፈቀደውን ምላሳችን ለመናገር ያልቻለበት አንዳንዶቻችን ደግሞ በነገሩ የተደናገርንበት ወቅት አሰለፍን፡፡ ጀግኖች የኢስላም ልጆች በሰሩት ድንቅ ስራ አህባሽ በየትኛውም ስምና መልክ ተመስሎ ቢመጣ በየትም ቦታ አድማጭ ላያገኝ በየትኛውም አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተንኮታኮተ፡፡ የአህባሽ መንኮታኮት ደግሞ እጅግ በርካታ የዲን አገልጋይ ከየተደበቁበት እንዲወጡ ሰበብ ሆነ፡፡ ኮሚቴዎቻችንና ዱአቶቻችን ቀድመውም ሁሉም የሚያውቃቸው ብርቅዬ ልጆቻችን እንጂ በአህባሽ ሰበብ የፈለቁ የዲን ተቆርቋሪና ኻዳሚዎች አይደሉም፡፡
በሰሞነኛ የብርቅዬ ልጆቻችን መታፈን ‹‹ጥያቄአችንም ሳይመለስ ልጆቻችንንም አስበልተን›› አይነት የተቃጠለ አንጀት የሚያሰማው ሮሮ ይስተዋላል፡፡ በሌላው ወገን ግን ‹‹ጥያቄአችንም መመለሱ አይቀሬ ነው፡፡ በልጆቻችን ላይ ወሰን ያለፉ በዳዮች ደግሞ ለታሪክ መማሪያ መሆናቸው አይቀሬ ነው›› የሚል ሙሉ እምነት ይስተዋላል፡፡ እውነታውም ይኽ ነው፡፡ ምናልባትም ይህን ያህል ወራት አሳልፎ ለዚህ ለተከበረውና የድል በር ለሆነው የረመዳን ወር ላይ ይህ ክስተት መከሰቱ የወሩን ትሩፋት መላው ህዝባችን እንዲያጣጥም አላህ ፈልጎ እንደሆነም ሁላችንም እንጠረጥራለን፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም በርሃብ የፈዘዙ አይኖቹ ስር ያማረ ምግብ አስቀምጦ ከማፍጠሩ በፊት የድረስልን ተማፅኖውን በእንባ ታጅቦ ወደ አላህ እያሰማ እንዴትስ ለዚህ የደረስነው አላህ መልካም ቢሻልን እንደሆነ መጠርጠር ይነሰን፡፡
አሁን ፀሃይ እየወጣች ነው፡፡ ምርጥ የኢስላም ልጆች ‹‹እኔ እያለሁ---›› እያሉ ወደፊት እየገሰገሱ ነው፡፡ እስር እና ዱላ ቀምሰው የወጡ ወንድሞችና እህቶች ያሉበትን የሞራል ጥንካሬ ላየ ሁላችንም ታስረን በወጣን ያሰኛል፡፡ በአይነቱ ልዩ ሆኖ የሚቀጥለውን ጥያቄአችንን የማስመለስና በግፍ በምርኮነት የተወሰዱብንን ውድ ልጆቻችንን ከእጃችን የምናስገባበት የትግል ምእራፍ ሊጀመር ነው፡፡ በእርግጥ ዛሬ ላይ ሁላችንም እኩል ሃላፊነት አለብን፡፡ ሃላፊነታችንንም ለመወጣት እኩል ቁርጠኝነቱ እንዳለን በየሰው ውስጥ የምናየው ወኔ አስረጅ ነው፡፡ ነገር ግን መሪ ማግኘት ግዴታ ብቻ ሳይሆን የአላህም ሱና ነው፡፡ ይህ ሱና ደግሞ አይቋረጥምና በኛ ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ምትክ አላህ እየሰጠን ነው፡፡
ውድ የኢስላም ልጆች፡፡ አሁን እያገኘናቸው ያሉት ምትኮች በብዙ መልኩ ኮሚቴዎቻችን የሄዱበትን አይነት አካሄድ ለመሄድ አይችሉም፡፡ አይጠበቅባቸውምም፡፡ የትግሉ ሂደትም ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ እንቅፋት የበዛበት ይሆናልና ለዚያ የሚመጥን ጠንካራ ስልት መቀየሱ ግድ ነው፡፡ እየተደረገ ያለውም ይኼው ነው፡፡ ሶስቱ ጥያቄዎቻችን ምን እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ አሁን የጨመርነው አራተኛ ጥያቄ ደግሞ የታሰሩ ኮሚቴዎቻችንና ውድ ልጆቻችን ይፈቱ ይህን መሰሉ አምባገነናዊ ትገባርም በአፋጣኝ ይቁም እንደሆነ ሁላችንንም ያስማማናል፡፡ ታዲያ ይህን በተግባር ለመለወጥ ከመቼውም የተለየ ብስለት፤ አንድነት፤ ጥንካሬ እና የሁል ግዜ መለያችን ሰላማዊነት ያስፈልገናል፡፡ ህዝባችን ለሌላም ሊተርፍ በሚችል መልኩ በዚህ ተክኖበታልና መካሪ አያሻውም፡፡ እጩ መሪዎቻችንም አሁን ያለው በአንፃሩ ሰከን ያለው ሁኔታ ነገሮችን በጥልቀት ለማጥናት እድል እንደሚሰጣቸው እናምናለን፡፡
እኛ ደግሞ አንድ ነገር ግን ከወዲሁ መስራት ይኖርብናል፡፡ ከመንግስት በማይጠበቅና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ መንግስት እያጠፋው ያለውን ስማችንን ለማደስ የድርሻችንን መወጣት አስቀድመን እንጀምር፡፡ በርካቶች የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ወሬዎችን በተቃራኒው እንደሚረዱት ቢታወቅም ጥቂቶች ግን በተለይም የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ሊደናገሩ እና የጥያቄአችን አላማ እና እስከአሁን ያሳለፍናቸው ለእኛ አኩሪ ለመንገስት ግን አሳፋሪ ሂደቶችን ባለመረዳት በቀጣይ በምንጀምረው አዲስ የትግል ምእራፍ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳርፍ ስለሚችል በአፋጣኝ በዚህ ስራ ላይ ልንረባረብ ይገባናል፡፡ ለዚህም የሚሆኑ አማራጭ ዘዴዎችን ድምፃችን ይሰማ በቅርቡ ይፋ እንደምታደርግ እየገለፅን በቀጣይ ታግለው ሊያያታግሉን እያኮበኮቡ ላሉ ጀግኖች አላህ የነስር ሰበብ ያድርጋቸው እያልን እኛን በፈተናው ፀንተን ከምንመነዳው ያደርገን ዘንድ አላህ በትእግስት እና በአንድነት እንዲያቆየን በዱአ እንበርታ፡፡
ድምፃችን ይሰማ
ዛሬ ከታማኝ ምንጮች የደረሱን መረጃዎች መንግስት በኢቲቪ ያቀረበው ዶክመንተሪ ፊልም ባሰበው መልኩ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን ሙስሊሙ ላይ ማነሳሳት ባለመቻሉ ይህንኑ ዐላማ ለማሳካት ሌላ ዘዴ እንደቀየሰ ያሳያሉ፡፡ ሙስሊሙ ተቃውሞ የሚወጣበትን ዕለት ጠብቆ በአቅራቢያ የሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን በማቃጠል (ምናልባትም የሙስሊም ምልክት ባላቸው ሰዎች ሊሆን ይችላል) ክርስቲያኑና ሙስሊሙ መሐል መቃቃር ለመፍጠር ታስቧል፡፡ ይህን እርኩስና ያለፈበት የከፋፍለህ ግዛ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግ መጪው ጁሙዓ በአንዋር መስጂድ ታስቦ የነበረው የተክቢራ ተቃውሞ በተክቢራ መሆኑ ቀርቶ በዝምታ እንዲሆን ሰፊ ምክክር ተደርጎበት ተወስኗል፡፡ በመሰረቱ የደረሰብን ግፍና መከራ በተክቢራ ጩኸንም የማይወጣልን መሆኑን የምንረዳ ቢሆንም የመንግስትን እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግና ቀኑ ፍጹም የተረጋጋ ሆኖ እንዲያልፍ ከማሰብ አንጻር በየክልልሉ የታሰቡት የተክቢራ ተቃውሞዎች እንደተጠበቁ ሆነው በአንዋር መስጂድ ግን ጁሙዓ ተቃውሟችንን በአስደንጋጭ ዝምታ እንገልጻን፡፡ ሁላችንም ለተፈጻሚነቱ የተለመደውን ትብብር እንድናደርግና ላልሰሙት እንድናሰማ እንጠይቃለን፡፡ ህዝብ ሰላም አስጠባቂ መንግስት ደግሞ ሰላም አደፍራሽ የሆነበት አገር ግን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ???
No comments:
Post a Comment