ዛሬ
አንዋር መስጂድና ዙሪያው ምናልባትም በታሪኩ ከፍተኛውን የሰው ቁጥር አስተናግዷል፡፡ ከተክለሃይማኖት እስከ ጎጃም
በረንዳ ከኩርቱ ህንጻ እስከ አዳራሽ ድረስ በሰዎች ተሞልቶ የወትሮው የመርካቶ ጫጫታ በአስደንጋጭ ጸጥታ ተቀይሮ
ውሏል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሊበጠብጡት ለመጡት ሰላም አስከባሪ ነን ባይ ሰላም አደፍራሾች አንድም ዐላማቸውን
ሊያሳኩ የሚችልበት ክፍተት ሳይሰጥ እጅግ በሰለጠነና በተረጋጋ መንገድ ተቃውሞውን ሲገልጽ ውሏል፡፡ አንድ ጊዜ ሁለት
እጆቹን አቆላልፎ በማንሳት የኮሚቴዎቹ መታሰርን የመቃወምና እነሱን ካሰራችሁ እኛንም እሰሩን የሚል መልዕክት
በሚሰጥ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ የደረሰበትን አፈና በሚገልጽ መልኩ አፍ በመያዝ እንዲሁም ሰላማዊነቱን በሚገልጽ መልኩ
እጆቹን አንስቶ በማውለብለብ የታየው ትርዒት እንደተራበ አንበሳ ካሁን አሁን ዱላ ለማሳረፍ ሲዘጋጁ የነበሩትን
ፌደራል ፖሊሶች አንዳንዱን ሲያዝናና ሌላውን ሲያበሳጭ ውሏል፡፡ በየህንጻው አናት ላይ ካሜራቸውን ደግነው ካሁን
አሁን ሆን ተብለው የተደረደሩትን ባዶ አውቶቡሶች ሲሰበሩ ለመቅረጽ ጓግተው ሲጠብቁ የነበሩ ለሆድ ያደሩ ጋዜጠኞችን
የሙያ ስንምግባር ቢኖራቸው ኖሮ የኢትዮጲያን ህዝብ ስርዓት አክባሪነት ለዐለም ሊያስተዋውቅ የሚችል ትዕይንት ቀርጸው
እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል፡፡ ውድ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ! ይህን ዐይነቱን ፍጹም ሰላማዊ ትግል እየደረገ ያለን
ህብረተሰብ በአሸባሪነት ከመወንጀል በላይ ምን የከፋ ወንጀል ይኖር ይሆን? መንግስት ሳምንቱን ሙሉ ያሉትን ሚዲያዎች
ሁሉ ተጠቅሞ ሙስሊሙን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ ቢሞክርም ህዝቡ ለመንግስት ማስፈራሪያ እጅ ሳይሰጥ ጥያቄው
ሳየመለስና ኮሚቴዎቹ ሳይፈቱ የሚተኛበት ሞራል እንደሌለው በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ የዚህ ሰላማዊ ህዝብ ፍትሃዊ
ጥያቄዎች ለምን እንዳልተመለሱ ዊኪሊክስ መሰል ተዐምር መጥቶ ወደፊት እንቆቅልሹን እስኪፈታልን ሁላችንም በጉጉት
እንጠብቃለን፡፡
ፍጽም ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ!!!
የዛሬው ጅምአ የሚለየው መንግስት ሆን ብሎ ከጎጃም በረንዳ እስከ ሀብተ
ጎርጊስ ድልድይ ድረስ 10 በላይ የሚሆኑ አንበሳ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ከሰጋጁ መሃል የነበሩ ሲሆን የህዝቡን
ትእግስት በመፈታተን ለመስታዎት ሰበራ ድራማ የተዘጋጁ እንደነበር ማንም በቦታው የነበረ ሰው ይረዳል።ሌላ ጊዜ
አርብ እለት ከ
5:30
ጀምሮ ይዘጋ የነበረው የ አውቶብስ ተራ ፒያሳ መንገድ ዛሬ ሆን ተብሎ ትእይንተ ህዝቡን ለማስተጛጎል እስከ 7
ሰዐት መንገዱን ክፍት በማድርግ ፖሊስ ከንቱ ሙከራ አድርጓል።በሳሉ ሙስሊም ግን ቀሽም ድርሰትና ድራማ ላይ ለትወና
አይመጥነንም በማለት ንቆ አልፎታል።
No comments:
Post a Comment