ጥያቄያችንን
ከስምንት ወር በላይ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ ታላላቅ የዓለማችን ኢንሳይክሎፒዲያዎችና
መዝገበ-ቃላት ሰላማዊ ትግልን ‹‹ከዜጎች ፍላጎት ተቃራኒ የሆነ ህግን ወይም ስርዓትን ለመቃወም ወይም ለማስወገድ
የሚደረግ ሁከት አልባ ንቅናቄ›› ሲሉ ይገልጡታል፡፡ በዚህ ረገድ የኛ ንቅናቄ መነሻው ‹‹በሕገ-መንግስቱና በሌሎችም
የሃገሪቱ ህጎች ላይ የሠፈሩ ድንጋጌዎች ይከበሩ›› የሚል እንጂ ‹‹የተደነገገ ሕግ ይጣስ ወይም ይሰረዝ አልያም
ስርኣቱ ይቀየር›› የሚል ባለመሆኑ እስከዛሬ በዓለማችን ከታዩት ሠላማዊ ትግሎች ይለያል ብለን እንገምታለን፡፡
በዓለም ላይ ዜጎች መንግስትን ‹‹ህገ-መንግስቱን አክብር›› ብለው ለወራት ሲደክሙ፣ ሲታሠሩ፣ ሲሰደዱና ሲሰቃዩ
የኛው የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም፡፡
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግል ህገ-መንግስታዊና ሠላማዊ ከመሆኑም ጋር በዓለም ሕዝብ ፊት የሚታይ የህግ ጥሰትና ውንጀላን እያስተናገደ ነው፡፡ ጥያቄዎቻችን ቀጥተኛና ግልጽ ቢሆኑም መንግስት ከመንግስት በማይጠበቅ መልኩ ነገሮችን አወሳስቦና የማይገናኙትን ሁሉ እያገናኘ ለማደናገር ይሞክራል፡፡ ሶስቱ መሠረታዊ የፍትህና የነጻነት ጥያቄዎቻችን ትኩረት የሚያደርጉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስትን ከማክበርና ከማስከበር ጋር ነው፡፡ ሆኖም፤ ‹‹ህገ-መንግስቱን ማክበርና ማስከበር የሁሉም ዜጎች ግዴታ ነው›› የሚለው መንግስት ግን ‹‹ህገ-መንግስቱ ይከበር›› ማለታችንን እንደ ነውር ቆጥሮት የማስፈራሪያና የስድብ መዓቱን ሲያወርድ ሰንብቶ አሁን ደግሞ የዱላ መዓቱን ያወርድ ጀምሯል፡፡ ትናንት አሳሳ፣ አወሊያ፣ አንዋር ዛሬ ደግሞ ደሴ የገፈቱ ቀማሾች ሆነናል፡፡ ነገ ደግሞ ማን ይሆን ተራኛው?
ሠላማዊያንን ለመደብደብና ለማሰቃየት የሚሰጧቸው ምክንያቶች ደግሞ ከድብደባቸው በላይ በዓለም ሕዝብ ፊት የሚያሳፍሩ ናቸው፡፡ ያለመታደል ሆኖ እንጂ እንዲህ ባለ በዲሲፕሊን የታነጸ የመብት ጥያቄ አቀራረብ ባሸለመ ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል……
መንግስት የገዛ ዜጎቹን ለማሠርና ለማጋጨት ቀን ከሌት ሲደክም የሐሰት ክስ ሲያቀርብ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ሳትሆን አትቀርም፡፡ እኛን እንኳ አይፍሩን፡፡ እንደው ታሪክን እንኳ አይፈሩም? ለነገሩ በታሪክ መወቀስን የሚፈሩት ስለ ታሪክ ትክክለኛ ግንዛቤ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ በአምባገነናዊ ሥርዓት ዘመን በአንድ ቀን ሰልፍ ከምንም ተነስቶ በሚያዝያ 12/1966 የአንድ ቀን ሰልፍ ከዜሮ ተነስቶ የተመሠረተው ቤታችን - መጅሊስ - ዛሬ ‹‹ዲሞክራሲያዊ ነኝ፣ ሕዝብ ጌታዬ ነው›› በሚል ስርዓት ውስጥ ሆነን ‹‹መጅሊሳችን ቆሸሸ እናጽዳው›› ስንል ግን ከስምንት ወር በላይ ፈጀ፡፡ ለዚያውም ሰዎች ተገደሉ፤ ቆሰሉ፣ ታሰሩ፣ ከስራቸው ተባረሩ፣ ተሰደዱ ወዘተ… ወዘተ… ይሄ ነው እንዴ ዴሞክራሲው? ለዚህ ነው የሕዝብ ልጆች ሕይወታቸውን የገበሩት? ይህ እንዲመጣ ነው ሠማዕት የሆኑት? ዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በሠላም ስለጠየቁ ይህን ሁሉ የዱላ መዓት የምታወርዱ ባለሥልጣናት እንደው ለአንድ አፍታ ብቻ ቆም ብላችሁ አስቡ እስቲ ሰማዕታቱ ድንገት መጥተው ‹‹የሞትነው ለዚህ ነበር? ጭቆናን ስም ቀይረን ለማምጣት ነበር?›› ቢሏችሁ ምን ትመልሱ ነበር? ወይስ ‹‹ትግላችንማ በድል ማግስት አርበኞች ተጠለፈ (hijack ተደረገ) እኮ›› ልትሏቸው?
ጥያቄያችን ግልጽ በመሆኑ አንዴ ተናግረነዋል አንደግምም አንልም ዛሬም ካልገባችሁ እንደግመዋለን፡፡ ጥያቄዎቻችን ፍጹም ኃይማኖታዊ ናቸው፡፡ ፖለቲካዊ ወይም ድብቅ አጀንዳ እንደሌለንም በአደባባይ ተናግረናል እየተናገርንም ነው፡፡ ጥያቄዎቻችን ከዚህ የሚከተሉት እንደሆኑ ዛሬም እናስታውሳቹኋለን፡፡
1. መጅሊስ የኛ እንጂ የመንግስት ቤት ባለመሆኑ፣ ተግባሩም መንፈሳዊ እንጂ አለማዊ ባለመሆኑ ምክንያት ሕዝበ-ሙስሊሙ መንፈሳዊ መሪዎቹን ከመንፈስ ተቋሙ (ከመስጂድ) በነጻነት የመንግስትም ሆነ የሙሰኛው መጅሊስ አመራርና የሙስና ግብረ አበሮቹ ጣልቃ ሳይገቡበት ይምረጥ፡፡
እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ጉዳይ አለ፡፡ ይኸውም፤ መንግስት ነጻ ምርጫ እንፈልጋለን ስንል ‹‹አክራሪ፣ አዲስ እስልምና፣ እስላማዊ መንግስት፣ ወዘተ›› የተባሉ ጭራቆች ፈጥሮ ሊያሸማቅቀን እየሞከረ ይገኛል፡፡ መቼም ጤነኛ ህሊና ያለው ሠው ሁሉ እንደሚገባው ነጻ ምርጫና አክራሪነት የሚገናኙ አጀንዳዎች አይደሉም፡፡ እኛ ስለ ፍትሃዊ መንፈሳዊ አባት ስናወራ ስለ እስላማዊ መንግስት መለፈፍ ተራ የማምታታት ተግባር ካልሆነ በቀር ‹‹ሆደ-ሰፊ ነኝ›› እያለ ራሱን ከሚያንቆለጳጵስ መንግስት አይጠበቅም፡፡ ሆኖም፤ ‹‹አክራሪነት አለ›› ከተባለም ቁጭ ብለን ብቻውን ርዕስ ይዘንለት ማውራትና ከመላው ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጋር መፍትሄ መፈለግ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙስሊሙ ፍጹም ፈቃደኝነቱን ለመግለጽ ይፈልጋል፡፡
2. ‹‹አሕባሽ›› የተባለውን መጤአስተሳሰብ በግድ አይጫንብን
ፖሊስና ህብረተሰብ የተባለው የሚዲያ ፕሮግራም ላይ ሁሌም የማትቀር ‹‹ከሕዝብ ዓይን የሚደበቅ ወንጀል የለም›› የምትል መፈክር አለች፡፡ እውነት ነው፡፡ እውነት ስለሆነም ነው የመንግስት ጣልቃ ገብነት ከኛ ዓይን ተሠውሮ ሊፈጸም ያልቻለው፡፡ ወይስ ለመንግስት ጣልቃ ገብነት ጊዜ የማይሠራ መፈክር ነው?
መንግስት ለዚህ ጥያቄ ‹‹እኔ ጣልቃ አልገባሁም›› የሚል ምላሽ ሠጥቻለሁ፡፡ አሁንም አልገባሁም ህገ-መንግስቱ ያግደኛል የሚል የሌባ አይነ ደረቅ ዓይነት ምላሽ እየሠጠ ይገኛል፡፡ ሙስሊሙ ለዓመታት ሲያመሰግነው የነበረውን ሥርዓት እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ የመክሰስና የመውቀስ አባዜ የለውም፡፡ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ ሳይሆን ከፊት ለፊት እንደገባ የሚያሳዩ ብዙ አስተማማኝ ማስረጃዎች አሉን፡፡
3. አወሊያ ነጻነቱን ጠብቆ የአካዳሚክ ሥራውን ያከናውን ዘንድ ከማንም መዳፍ ይላቀቅ
ይህ የቅንጦት ጥያቄ አይደለም፡፡ ጥያቄው የሕዝብን ኃብት ከጥፋት የመታደግ እንደዚሁም በዓለም ላይ ውጤታማ የአካዳሚ ሥራ እየሠሩ እንደሚገኙ የትምህርትና የማህበራዊ አገልግሎት እንደሚሠጡ ተቋማት ሁሉ ነጻ ሁኖ መመራቱ ለመንግሰት እንዴት ሊዋጥለት አልተቻለውም፡፡ ይሄም፤ እንቆቅልሽ ነው፡፡
4. ኮሚቴዎቻችንና በመብት ጥያቄው የተነሳ የታሠሩ ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ይፈቱ!
ኮሚቴዎቻችን መንግስትም ጭምር እንደሚያውቀው ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸሙም፡፡ ታሳሪዎቹም ሆኑ በየቦታው የተደበደቡ የተገደሉትም ወንጀላቸው ሙስሊም መሆናቸው ከዛም ሲያልፍ መብታቸውን መጠየቃቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡ እነዚህን ሠዎች በመንግስት ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ለኢትዮጵያውያን ግን ‹‹የሠላም አምባሳደሮች›› መሆናቸው - እየቆየ መጥፎ ነገር ሊፈጥር የሚችል በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል፡፡
በመጨረሻም፤ ኢህአዴግ መቼም ከአሁን በኋላ ህዝብ አያስፈልገኝም እንዳለ ይገመታል፡፡ በመጪው ዓመትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምርጫን ሊወዳደር ሲመጣ መወዳደሪየው ምን ይሆናል? ጭቆናውና የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት? ወይስ ምኑ?

No comments:
Post a Comment