አዲስ ዘመን በ “አጀንዳ/ደብዳቤዎች” አምድ ስር ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው በሚል በሐሙሱ የነሐሴ 10 2004 ዕትም የ “አወል አባ ፊጣ-ከለቡ”ን አስተያየት አስፍሯል፡፡
ረመዷን ሊሰናበተን ቢበዛ ሁለት ቀናት ብቻ በቀሩበት በዚህ ሰዓት “ሮመዳን ከሪም” ሲል የተመኘልን የ“ሮመዳን ለሰላም” ፅሁፍ አዘጋጅ ግለሰብ ከፅሁፉ ሁለት ነገሮችን አትርፏል፡፡ የመጀመሪያው ልምድ ያለው ፀሐፊ መሆኑን የሚመሰክር መጣጥፍ ማዘጋጀቱን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የቀለጠ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ካድሬ መሆኑን ማስመስከሩ ናቸው፡፡ ጉዳዩ ወቅታዊ እና መቋጫ ያልተበጀለት ሐቅ ከመሆኑ ጋር በቀር አምዱን ካፍ እስከ ገደፉ የሞሉት ቃላት በጌታዬ ስም እምላለሁኝ ፍፁም ከእውነት የራቁ እና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ እንዲውሉ የተዘጋጁ ናቸው፡፡
“አወል አባ-ፊጣ” የፅሁፉ አዘጋጅ በመሆን አስተያየታቸውን ሲለግሱ ከተስተዋሉት አንኳር ጉዳዮች መካከል ሙስሊም ያለመሆናቸውን ማሳበቁ ይገኝበታል፡፡ ለነገሩ አዲስ ዘመን ጋዜጣ መሠል ዓይነት ዘዴ ሲጠቀም የመጨረሻው ቢሆን እንጂ የመጀመሪያው ባለመሆኑ አይደንቅም፡፡ የተቃውሞ ሂደቱን ህገ ወጥነትና ፖለቲካዊነትን ለማሳመን ብዙ የጣሩት ፀሐፊው “እውነታውን” ለማን እየነገሩት እንደሆነ ግራ እስከሚገባ ድረስ እነሱ “ጥቂት” እያሉ የሚጠሩት ሕዝብ የሚያውቃቸውን የፈጠጡ እውነታዎች በሙሉ ያለምንም እፍረት በተቃራኒው በመገልበጥ ለዛ ባለው አማርኛ አቅርበውታል፡፡
ላለፉት 8 ወራት የሐይማኖት የመብት ጥያቄዎቻችን ተገቢውን ምላሽ ያግኙ በማለት አደባባይ የሚገኘው ሙስሊም ሕብረተሰብ ለወራት ይቅርና ለአንድ የተቃውሞ ውሎ ሳይቀር የተቃውሞ መድረኩ ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆን የሚያደርገው ጥረት ለውጭ ተመልካች ሳይቀር እጅጉን ያስገረመ ነው፡፡ይህ ሠላማዊ ሒደት ፍፁም ያልተዋጠላቸው ማን አለብኝ ባይ የፀጥታና ደሕንነት ኃይሎች እጅግ ለበርካታ ጊዚያት የተቃውሞውሒደት በማደፍረስና አቅጣጫ ለማስቀየር ሞክረዋል፣ እየሞከሩም ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ሕዝበ ሙስሊሙ ለተቃውሞ ከወጣባቸው በርካታ የተቃውሞ ሳምንታት ውስጥ ረብሻ የተፈጠረው በአንዱ ሳምንት ብቻ ነው- ረመዷን በገባ በሁለተኛው ቅዳሜ፡፡ ይኸውም በአንዋር መስጂድ ራሳቸው የፀጥታና እና የደሕንነት ኃይሎች ያቀዱትን እውን ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡ ለ 8 ወራት በሰላም እየተጓዘ ቆየው ሂደት የራስ ምታት ስለሆነባቸው ለጥያቄው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በአንድ አጋጣሚ ሁከትና ረብሻ ፈጥረው ሲያበቁ “ተቃውሞው ህገ ወጥ እና ፖለቲካዊ ነው” ብሎ በመፈረጅ ሂደቱን ለማኮላሸት ያዘጋጁት መላ ነው፡፡ ከዚህ ተንኮላቸው ትልቅ ትምህርት የወሰደው ሙስሊሙ ህዝብ ሰላማዊ የሆነውን የተቃውሞ ሒደት ዳር ለማድረስ ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ ከዚህ የረብሻ ሳምንት በኋላ በአላህ እገዛ በከፍተኛ ጥንቃቄ በተፈጠረው ነገር ባለመደናገጥ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሙስሊም ከመላ አዲስ አበባ በአንዋር መስጂድ በመሰባሰብ ሶስት የጁምዓ ተቃውሞዎችን አካሂዷል-(ሁለት የዝምታ እና አንድ የተክቢራ ተቃውሞዎች)፡፡ ይሁንና እነኚህም ሶስት የተቃውሞ ሳምንታት አልተፈተኑም ማለት አይደለም፡፡ ምሳሌ እናንሳ፡፡ በአንደኛው የተቃውሞ ሳምንት ሙስሊሙ ተሰባስቦ በተቀመጠበት አጋጣሚ አንድ የአንበሳ አውቶብስ ከመርካቶ በይርጋ ኃይሌ በኩል በሕዝብ መካከል እንዲያልፍ ይታዘዛል፡፡ ይህን ለማድረግ ባሱ ፈራ ተባ እያለ ተንቀሳቀሰ፡፡ ወታደሮቹም የተቀመጠውን ጀመዓ በመቅረብ ተነስተው መኪናውን እንዲያሳልፉ በድፍረት ያዛሉ፡፡ ሁኔታውን ቀድሞ የተረዳው ጀመዓ በሁኔታው በመገረምና በመሳሳቅ ተነጋግረው ሲያበቁ ተነስተው በመጠጋጋት መኪናው እንዲያልፍ ያደርጋሉ፡፡ ሾፌሩ ግን እስከ ኃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ድረስ የተቀመጠውን ኡማ እንዴት እንደሚያልፈው አሻግሮ በመመልከት ሲጨናነቅ የፊቱ ገፅታ ያስነብብ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ እንደማይዘልቀው በማሰብም የህዝቡን የልብ ትርታ የተጋራበትን ውሳኔ አሳየ፡፡ ብዙም ሳይርቅ ወደ ጥግ ሆኖ ቆመ፡፡ በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ያደረጉት የሚገርም ነበር፡፡ ይኸው የደኃ ንብረት የሆነው የፈረደበት አንበሳ ባስ በብዛት ህዝብ በሚቀመጥበት መካከል ተደርድሮ እንዲቆም ይታዘዛል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ረብሻ ለማስነሳት በመሞከር በውስጥ የሰገሰጓቸው የደህንነት አካላት በመኪኖቹ ላይ ድንጋይ እንዲወረውሩ በማድረግና ተቃውሞው ሰላማዊ ይዘቱን በማስቀየር ለሚፈጠረው ሁከት ሙስሊሙን ተጠያቂ በማድረግ ለመወንጀል መመኮራቸው ይገኝበታል፡፡ይህም ሳይሳካላቸው አልፏል፡፡አልሐምዱሊላህ፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ ምላሽ እንዲሰጥባቸው፣ እስካሁንም ድረስ አጥጋቢ ምላሽ ያልተሰጣቸውና ያቀረባቸው ሦስት ጥያቄዎች በይዘትም በቁጥርም አልጨመሩም፣ አልቀነሱም፡፡ በሐይማኖት ሽፋን የቀረበ የፖለቲካ ጥያቄም የለም፡፡ የተከተለውም የፖለቲካ አካሄድም የለም፡፡ ወደ ሌላ ጥያቄም አልተሻገሩም፡፡ ጥያቄዎቹ እስካሁን ድረስ ባልተመለሱበት እና ህዝቡም ተቃውሞ ማሰማቱን በቀጠለበት ሁኔታ ሙስሊሙ የፈጠረው ብጥብጥ፣ ረብሻ፣ አመፅም ሆነ ሁከት የለም፡፡
ፀሐፊው “ቡድኑ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ያግኝም፣ አያግኝም ምንም የሚደንቀው ጉዳይ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ጥያቄዎቹ ሊመለሱ ባይችሉ ኖሮ፤ ሰበቡ ብጥብጥ ለማስነሳት እንደመልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ፍላጎት ነበረው፡፡ ዳሩ ግን እንደገመተው ሳይሆን በመቅረቱ ለሌላ ተደራራቢ የፖለቲካ ጥያቄዎችና የኃይል እርምጃዎች ራሱን ማዘጋጀቱን ሊገፋበት ችሏል፡፡” እንዳሉት ሳይሆን መንግስት አሁን የያዘውን የማይበጅ መንገድ በመተው ሕዝብ ዕውቅና ከነፈጋቸው ሙሰኛ የመጅሊሱ አመራሮች ጋር ሳይሆን ለተቃውሞ አደባባይ ከወጣው ሙስሊም ሕዝብ ጋር በመቀራረብ ለችግሩ እውነተኛ መፍተሔ የመፈለግ ሀሳብ ካለው ጉዳዩ በአጭሩ የሚቋችበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም በዚህም እውነታው የትኛው እንደሆነ ይደረስበታል፡፡ በዚህም ፀሐፊው እንዳሉት “ይሁንና የእነዚህ ኃይሎች ፍላጎት ፈፅሞ ሃይማኖታዊ አለመሆኑን …” ሳይሆን የሙስሊሙ የተቃውሞ ሂደት ፍፁም ከፖለቲካ አካሄድ የፀዳ እና ሐይማታዊ መሆኑ በጋራ ይረጋገጣል፡፡
ከሁለት ወራት በላይ በአዲስ አበባ እና በመላ አገሪቱ በሠላም ሲካሄድ የቆየውን የ “ሶደቃ እና የአንድነት” መድረክ ቀጣይ ክፍል ሐምሌ ስምንት በአወሊያ ለማድረግ ታስቦ የተደናቀፈውን ዝግጅት ጥላሸት በመቀባት ለውንጀላ በሚያመች መልኩ ያቀረቡት ፀሐፊ እና ሌሎችም እንዲዲያውቁት የምንፈልገው እውነታ የሚከተለው ይሆናል፡፡ የተቃውሞ ሂደቱ ከተነሳ በኋላ አገራችን የመሪዎችን ስብሰባ ስታደርግ ይሄኛው የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በአወሊያ የተቃውሞ ድምፃችንን በማሰማት ላይ በነበርንበት አንድ ጁምዓ በተጓዳኝ የመሪዎች ስብሰባ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነበር፡፡የተፈጠረ ሁከት ረብሻም ሆነ የአገር መልካም ገፅታ የማበላሸት ሁኔታም አልታየም፡፡ እንዲሁም የሐምሌ ስምንቱ የፀጥታ ሐይሎች ህገ ወጥ ድርጊት በተፈፀመ ማግስት እሁድ ዕለት በሁኔታው እጅግ የተቆጣው ሙስሊም ሕዝብ ከሱብሂ ጀምሮ በአንዋር መስጂድ በመሰባሰብ ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት አካሂዷል፡፡ ይህም የሆነው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ እየተካሄደ እና ሊጠናቀቅ የአንድ ቀን ዕድሜ በቀረበት ወቅት ነው፡፡ በዚህም ህዝቡ የፈጠረው ምንም ዓይነት ሁከትም ሆነ ረብሻ እንዲሁም የአገርን መልካም ገፅታ የማበላሸት ስራ የለም፡፡ ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ የማካሄድን መርህ ተከትሎ የተፈፀመ በመሆኑ ውጤታማ የሆነ ስራ ተሰርቷል፡፡ የአንድነት ፕሮግራሙ ከሁከት፣ ብጥብጥና ረብሻ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፣ ከቶ ታይቶም አይታወቅም፡፡
እየተራገቡ ያሉትን ርካሽ ፕሮፓጋንዳዎች ወደ ጎን በመተው ሕዝበ ሙስሊሙ ሕጉ በሚፈቅደው መልኩ ሰላማዊ እና ስርዓቱን የተከተለ የተቃውሞ ሂደቱን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ የዚህ ሂደት ዓላማ ፍፁም ሐይማኖታዊ ከመሆኑ የተነሳ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ግብረ መልሶች አይመጥኑትም፡፡ የዚህ ሒደት ማሳረጊያ የሚሆነው የሚደረጉትን የሽወዳ ተግባሮች በማቆም እጅግ ከተቃውሞው ባለቤት ጋር መሆን ግልፅነት የተሞላበት ውይይት ነው፡፡ ከሕዝብ እውቅና ውጪ የጠለሸ ስብዕና ተላብሰው አመራሩን ተቆጣጥረው የሚገኙት ህገ ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ለመንግስት ከሚያቀርቡት ፍፁም የተሳሳተ መረጃ በመራቅ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ እና መንግስት ከሰፊው ሕዝብ ጋር በመቀራረብ ሁኔታውን በማርገብ ፊታችንን ወደ ጀመርነው ልማት ማዞር አማራጭ የሌለው አማራጭ እንደሆነ ይታየናል፡፡
“አወል አባ ፊጣ ከለቡ” ዒድ ሙባረክ ነው የሚባለው፡፡
ዒድ ሙባረክ

No comments:
Post a Comment