በኢህአዴግ ዘመን በፀደቀው ህገ መንግሰት እንደ እምነት ማን ተጠቃሚ ሆነ ፡-
1- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፡- ከብዙ በጥቂቱ በአሁኑ ሰኣት በስርዋ 1400 የሚጠጉ ድርጅቶችን ታስተዳድራለች ወደ 40ሺህ የሚሆኑ ቤተ ክርስቲየኖችን 5ሺህ ቀሳውስቶችን 2ሚሊየን የሰንበት ተማሪዎችን በድግሪ የምታስመርቅባቸው 6 ኮሌጆችን ታስተዳድራለች በስርዋ ከተቋቋሙ ድርጅቶች ውስጥ መህበረ ቅድሳን በ800 የሀይማኖት መምህራን 80ሺህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመዕረግ አስመርቋል በስሩ 600 ማህበራትን አቅፎዋል ፡፡ ለተከታዮቻቸው እያንዳንድዋ ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ የትምህርትና የስብከት ፕሮግራም በይፋ ታስተላልፋለች ፡፡ ይህ እምነታቸውን ለማስፋፋት ከሚጠቀሙባቸው ሰፊ መንገዶች በጥቂቱ ነው ፡፡ ቤተክርስቲያንዋ የምታደርጋቸውን ሰብኣዊ እርዳታን ብንመለከት እጅግ መጠነ ሰፊ ነው እንዲሁም የልማት አውታሮችዋም ሰፊ ናቸው እንደው ለምሳሌ ያህል በአዲስ አበባ የሉዋት ትላልቅና ጉዙፍ ህንጻዎች ግልጽ ዋቢ ናቸው (CRDA) በመባል የሚታወቀው የክርስቲያን ተራድዖ ድርጅት ወደ 222 የሚሆኑ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎዋል ፡፡
2- ፕሮቴስታንት (ጴንጤ)፡-ከብዙ በጥቂቱ በአሁኑ ሰኣት በአጭር ግዜ ውስጥ 12ሺህ ቸርቾች ገንብተዋል በበኒ ሻንጉል ክልል ብቻ በአንድ አመት አካባቢ 1311 ቸርች ገንብተዋል ፡ 30805 የስብከት ጣቢያዎችን አፍርተዋል 8 በድግሪ የሚያስመርቁበት ኮሌጅ ገንብተው እያስተዳደሩ ነው ፡፡ በስራቸው 37 አገር አቀፍ እና 16 አለም አቀፍ ድርጅቶችን ይዘዋል ፡፡ እምነታቸውን በየመንገዱ በየ አደባባዩ በየ አደራሹ በይፋ ይሰብካሉ እንዲሁም ሰፊ ሽፋን ያለቸው መጽሄቶችን ፓምፕሌቶችን በራሪ ወረቀቶችን ያሰራጫሉ ፡፡ ለተከታዮቻቸው በየ አጥብያው አብዛኛውን ሰዓት እምነታቸውን በመስተምር ያሳልፋሉ ፡፡ ሰብዓዊ እርዳታ ላይ እጅግ የገዘፈ ስራ ይሰራሉ በዚህም ድጋፍ እምነታቸውን ለማሰራጨት ይጠቀሙበታል ፡፡
3- ኢስላም ፡- ከኢህአዴግ መምጣት በፊት ከነበረበት ደራጃ ራሱን በራሱ ስናነጻጽረው ለውጦችን አሳይቶዋል ፡፡ ለውጦቹ ግን ድርጅታዊ አይደሉም ግላዊ ናቸው ማለትም አንድ ሙስሊም ለእመነቱ ካለው መቆርቆር የተነሳ በፊት ያልነበሩ ጥቂት መስጅዶች ተገንብተዋል ፡አማኙም በግል ተነሳሽነት እምነቱን ይተገብራል ፡፡ የትምህርት ተቋምን በተመለከተ ድሮ የነበረውና አሁን ኢህአዴግ ለአህባሾች ያስረከበው የአወሊያ ተቋም ብቻ ነበር ፡፡እሱም አሁን ኢህአዴግ ወስዶት ለካድሬዎች አስረክቦታል ፡፡ ኢስላም ከሌሎች ሀይማኖቶች አንጻር በኢህአዴግ ዘመን ሲታይ በሁሉም ዘርፍ ማለትም እምነትን ከማስፋፋት አንጻር ፤ ድርጅት ከመመስረት ፡ የትምህርት ተቋም ከመገንባት ፤ በተቋም ደረጃ በሀገሪትዋ ልማት ከመሳተፍ ፡ ሰብኣዊ እርዳተ ከመስጠት ‹ ‹ ‹ ወዘተ አንጻር ፡በነገቲቭ ደረጃ ሚቀመጥ እንጂ ይህ ነው ተብሎ ሚነገር ነገር የለውም ፡፡ እንደ ድርጅት ብንወስድ በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች በግለሰቦች ተነሳሽነት ቢቋቋሙም ከኢህአዴግ ባለስልጣናት በሚደርስባቸው ጫና ምንም ለአይን የሚገባ ነገር ሳይሰሩ አንደንዶች ፍቃዳቸው ሲነጠቅ አንዳንዶቹ የባንክ ሂሳባቸው ሲዘጋ አንደንዶቹ በደህንነቶች በኩል በሚደርስባቸው ማስፈራራት በራሳቸው ግዜ ድርጅታቸውን ሲዘጉ ነው ሚታየው ፡፡ በጣም የሚገርመው በአደረጃጀት ከሌሎች የሀይማኖት ተቋሞች ጋር ሊቀራረብ ይችላል ተብሎ ሚታሰበው መጅሊሰ ለሙስሊሙ ምንም ያበረከተው ነገር የለም እንዲያውም እምነቱን ለማጥፋት ጥቂቶቹን የእምነቱ ተቋማትን ለማዘጋት ነው ቀን ማታ ሚደክመው ፡፡ ለዚህ ትልቁ ምክንያት ኢህአዴግ ነው ይሀውም የመጅሊሱ አመራሮች በሙሉ የኢህአዴግ ካድሮዎች ናቸው ለዛዉም በሙስና የተጨማለቁና በስብዕና የወረዱ ናቸው በጥቅሉ መጅሊስ ማለት ኢህአዴግ ቆሻሻ ባህሪ ያላቸውን ካድሮዎቹን የሚወረውርበት የቆሻሻ ቅርጫት ነው ፡፡ በዚህ የኢህአዴግ ባለስልጣነት ጣልቃ ገብነት የተነሳ ህገመንግሰቱ የሰጠንን መብት መጠቀም አልቻልንም ፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎዋቸው የኢትዮጵያን ሙስሊም ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ እናጥፋው ብለው እመነቱን በሀይል እንዲቀይር ባጀት መድበው አስጠማቂ ከሊባኖስ አስመጥተው በፌደራል ጉደዮች ሚኒስተር ፊት መሪነትና መጅሊስ ውስጥ ባሉ ካድሬዎቻቸው የ24 ሰዓት የጥቃት ዘመቻ በማድረግ ላይ ናቸው ይህን ዲስ እምነት አልቀበልም ብሎ የተከራከራቸውን ወደ እስርብት በመወርወር ላይ ናቸው ፡፡ ሰብኣዊ አመለካከት ያላቸው የሌላ እምነት ተከታዮች እንዳይቃወሙዋቸው አሽባሪዎችን ነው ያሰርነው የጸረ አሸባሪ ስልጠና ነው ምንሰጠው እያሉ ለማስመሰል ይሞክራሉ ይሁን እንጅ እነዚሁ የሌላ እምነት ተከታዮች ነገሩን በቅርበት የሚያዉቁት በመሆኑ በኢህአዴግ ማስመሰያ ባለመታለል ከሙስሊሙ ጎን በመሆን ህጋዊ መብታቸው ይከበር እያሉ ይገኛሉ ፡፡
ታዲያ የቱ ጋ ነው ኢህአዴግ ለሙሰሊሙ መብት ሰጥቶዋል ሚባለው ?
No comments:
Post a Comment