Tuesday, September 25, 2012

ህገ-መንግስቱ ሲናድ ቁጭ ብለን አናይም!!!

ህገ-መንግስቱ ሲናድ ቁጭ ብለን አናይም!!!
“ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለስልጣኖቻቸው ህገ መንግስቱን የማስከበርና ለህገ መንግስቱ ተገዢ የመሆን ሀላፊነት አለባቸው።” የኢፌድሪ ህገ-መንግስት ምእራፍ ፪ አንቀፅ ፱ ንዑስ አንቀፅ ፪
ከዚህ የህገ-መንግስት አንቀፅ በቀላሉ መረዳት እንደሚቻለው ህገ-መንግስቱን ማስከበር የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው። አሁን ባለንበት ተጨባጭ ደግሞ በየመንደሩበመንግስት ትእዛዝ እና መንግስት ባበራውአረንጓዴ መብራት በመታገዝ ከየአቅጣጫው ግልፅ ህገ-መንግስቱን የሚፃረሩ እና የሚንዱ ተግባራት የእለት ከእለት ተግባራት ሆነዋል። በየመንደሩ የተለያዩ ካድሬ
ዎች ሊያውም ያለ ሀይማኖታቸው (ሙስሊም ሳይሆኑ) በሙስሊሙ ጉዳይ ተዘፍቆበመግባት የምርጫ ካርድ ካልወሰዳቹ እያሉህብረተሰቡን በማሸበር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በመሰረቱ ዜጎች የመጅሊስን አይደለም የመንግስትንም ምርጫ ያለመምረጥ ሙሉ መብት አላቸው!! ነገር ግን በየመንደሩ እየተስተዋለ ያለው እንቅስቃሴ የዜጎችን መብት የሚጥስና በብዙ መስእዋትነት የተገኘውን ህገ-መንግስት የሚንድ መሆኑን ማስተዋል ተችሏል። በመሆኑም እኛም ህገ-መንግስቱን የማክበር እና የማስከበር ሀላፊነት የተሸከምን በመሆኑ ህገ-መንግስቱ ሲናድ ቁጭ ብለን የማንመለከት መሆኑን ትግላችንን እየተከታተሉ ላሉ አካላት እና ለመንግስትም ጭምር ልናሳውቅ እንወዳለን!!!።

በአሁኑ ሰዓት በየአቅጣጫው እየተፈፀሙ ካሉ የህገ-መንግስት ጥሰቶች መካከል ሙስሊም ያልሆኑ አካላት አበል እየተከፈላቸው ለመራጭነት መመዝገብ፣ የተመራጮቹ ማንነት አለመታወቅ (በህዝብ ያልታጩ መሆናቸው)፣ ከምዝገባ አንስቶ በየቦታው እንደሚታየው ሙስሊም ያልሆኑ አካላት (የመንግስት ስራ አስፈፅሚዎች) ግልፅ ጣልቃገብነት እና አስተዋጽዖ መኖሩ፣ የምርጫ ስርዓቱም ይሁን አስፈፃሚዎቹ በሙስሊሙ ህብረተሰብ እውቅና ያልተቸራቸው መሆን እና የመሳሰሉት… ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ ያለ ግልፅ ህገ-መንግስትንየመናድ እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይህንን የህግ ጥሰት ቁጭ ብሎ ይመለከታል ብሎ መገመት ፍፁም የዋህነት ነው። በመሆኑም “የድምፃችን ይሰማ ገፅ” ይህንን ህገ-መንግስትን የመናድ እርምጃ አጥብቃ የምትኮንን ሲሆን ህገ-መንግስቱን የሚንድ የሆነው “የምርጫ ድራማ” ሊሰራ በሚቃረብበት ወቅትም ህብረተሰቡ ህገ-መንግስቱን የሚያስከብርበትን እና የምርጫውን ከንቱነት የሚያረጋግጥበት ልዩ የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂ ለማስተዋወቅ ውይይት በመደረግ ላይ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

No comments:

Post a Comment