Sunday, October 21, 2012

ድምፃችን ይሰማ


በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በጉባ ላፍቶ ወረዳ በተካሄደው “የመንግጀሊሰ” ምርጫ ፣ በሳንቃ ቀበሌ የተመረጡት የቀበሌው የመጅሊሰ ሰብሳቢ፣ ዋና ጸሀፊውና ሌሎች ተመራጮች የአህባሽን አስተምህሮ ይቃወማሉ፣ አህባሽን አይቀበሉም እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ተቃውሞ ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል ምክንያት አሸናፊነታቸው ተሰርዞ በምትኩ ሌላ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን ምንጮች አስታወቁ፡፡ የምርጫው ውጤት እንዲታገድ ትእዛዙን ያስተላለፉት የወረዳው አስተዳዳሪ ሲሆኑ፣ እንዲታገዱ የተደረጉትም የሳንቃ ቀበሌ መጅሊስ ሰብሳቢ ሼክ አህመድ ያሲን፣ ዋና ጸሀፊው አቶ ሙሀመድ ሞላ፣ የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አቶ ኢብራሂም ሁሴንና ሼህ አሰፋ ይማም ናቸው። በአካባቢው 25 ሰዎች ተመርጠው አምስቱ ስራ አስፈጻሚ፣ 20 ዎቹ ደግሞ የምክር ቤት አባላት የሆኑ ሲሆን፣ለወረዳ ምርጫ እርሳቸውና ጸሀፊያቸው ተመርጠው እንደተላኩ ታውቋል። በተሰረዙት ሰዎች ምትክ በቀበሌው አዲስ ምርጫ ሊደረግ እንደሆነም ታውቋል፡፡

ድምፃችን ይሰማ

ማሳሰቢያ
በአማራ ክልል አንድ አንድ አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂ ሐይሎች በሙስሊሙ ላይ እየወሰዱት ያለውን ሕገ ወጥ እርምጃ በተለይም በርካታ ሙስሊም ወጣቶችን ወደ ወህኒ በመጋዝ የአካባቢውን ሙስሊም ኅብረተሰብ ወደ ሐይል እርምጃ እንዲገባ ግፊት እያደረጉበት ይገኛል፡፡ ገርባን በመሳሰሉ አካባቢዎችም ግጭቶች እየተከሰቱ እንደሆነና ይህም ወደሌሎች አጎራባች ክልልች እየተዛመተ እንደሆነ ከአካባቢው የሚወጡት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ከመሰል የጸጥታ ችግሮች በመራቅ ሁኔታውን በትእግስትና እስከአሁን ሲያሳይ በነበረው ኢስላማዊ አደብ እንዲያሳልፈው እየጠየቅን እነዚህ የመንግስት የጸጥታ ሐይሎች እየወሰዱት ያለው እርምጃም አገሪቷን ወደ ከፋ ብጥብጥ የሚከታት መሆኑን አውቀው ከየትኛውም የሐይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አበክረን እንገልጻለን፡፡

ድምፃችን ይሰማ
ሰበር ዜና!!
በዛሬዉ እለት እሁድ በአማራ ክልል በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያሰሙይገኛሉ፡፡ የዚህ ምክንያትም አብዱ አህመድ የተባለ መምህርን የመንግስት ሃይሎች በማፈን ሊወስዱት ስላሉ እንደሆነ በቦታው ያሉ ሰዎች ገልፀዋል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ባሳየው ቆራጥ አቋም ወንድማችን ሊለቀቅ ችሏል፡፡ የታላቁ መስጂድ ኢማም የሆኑት የሸኽ አሊ ቤትም ያለፍርድ ቤት ማዘዣ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡ ይህን በመቃዎም ሴት ወንዱ ወጣት ሽማግሌ ሳይል ሁሉም ህብረተሰብ በከተማይቱ መንገዶች ላይ የተቃውሞ ድምፁን በማሰማት ላይ ነው፡፡

ድምፃችን ይሰማ

ተጨማሪ ማሳሰቢያ

ከደሴና ከሌሎችም አካባቢዎች የመንግስት አድማ በታኞችና የጸጥታ ኋይሎች ከፍተኛ ተቃውሞ ወደተነሳባቸው ገርባና ደጋን ከተሞችና አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች በማቅናት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ገርባ በከፍተኛ ውጥረት ላይ የምትገኝ ሲሆን ከተማዋም በታጣቂ ኋይሎች ከበባ (siege) ላይ ናት፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በከተማዋ መስጊዶች አሁንም ተክቢራ እያደረገ እንደሆነና አድማ በታኞቸም አስለቃሽ ጋዝ በሰላማዊው ሕዘብ ላይ በመተኮስ ላይ መሆናቸውን የዓይን እማኞች እየገለጹ ነው፡፡ መንግስት ለሁሉም የሕዝብ ጥያቄ የኋይል እርምጃን እንደ ብቸኛ አማራጭ እየተመለከተ መሆኑ በጣም አሰሳቢ ነው፡፡ ይህ ለዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የማይመጥን እና እጅግ የወረደ ኋይል ተኮር አጸፋ አገሪቷን ወደ አፋኝ ሥርዓት (ፖሊስ ስቴትነት) እየለወጣት መሆኑን በትክክል እያስተዋልን ነው፡፡ መንግስት ከሕዝብ ጋር እልህ በመያያዝ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶችን ለእንግልትና ስቃይ አየዳረገ ነው፡፡ ይህን ከአንድ አገር አስተዳዳሪ የማይጠበቅ የመንግስት ባሕሪ በበርካታ ክስተቶች ላይ ደጋግመን እያየነው ነው፡፡ አሁንም በድጋሚ እንገልጻለን ማንኛውም ዓይነት በመንግስት በኩል የሚወሰድ የኋይል እርምጃ የአገሪቷን ሰላም ወደ ብጥብጥና ኹከት አቅጣጫ ይመራዋል፡፡ ይህን ስንል ስለ ጥቂት ዜጎች ሳይሆን ስለ ሚሊዮኖች እያወራን በመሆኑ ሁኔታዎች ወደተለመደው ሰላማዊ ከባቢ እንዲለወጡ ጥብቀን እንጠይቃለን፡፡


 

 
 

No comments:

Post a Comment