አንድ አንድ መረጃዎች
የኮሚቴዎቻችንና የሌሎችም ታሳሪዎቻችን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለትላንት ጥቅምት 14 እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የትላንቱ ቀጠሮ የመጨረሻቸው የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት መሪዎቻችን ትላንት ፍርድ ቤት ሳቀርቡ ቀርተዋል፡፡ ከመሪዎቻችን ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት አጭር ቃለ መጠይቅ የምርመራ ፋይሉ መዘጋቱን ገልጸው ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎም በመላው ዓለም መሪዎቻችን መፈታታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች ተናፍሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ መረጃዎች ኮሚቴዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን የሚገልጹ የነበረ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ዛሬ በእርግጠኝነት እንደሚፈቱ የሚያሳዩ ነበሩ፡፡
የመሪዎቻችን መፈታት አለመፈታትን አስመልክቶ መንግስት ምንም ያለው ባይኖርም የመሪዎቻችን ቤተሰቦች ኮሚቴዎቻችን ይፈታሉ በሚል ተስፋ ከትላንት ቀትር ጀምሮ እስከምሽት ድረስ በማዕከላዊ ወህኒ ቤት ደጃፍ በመኮልኮል የመሪዎቻችንን መፈታት ሲጠባበቁ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ አንድ አንድ ወገኖች እስከትላንት ሱብሂ ሶላት ብሎም እስከ ዛሬ ዙሁር ድረስ መሪዎቻችን ይፈታሉ ብለው ተስፋ ቢያደርጉም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ዛሬ ከ9 ሰዓት በኋላ ኮሚቴዎቻችን ዘወትር ከሚቀርቡበት አራዳ ፍርድ ቤት ችሎታቸው ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋውሮ ጉዳያቸው መታየት ጀምሯል ቢባልም ይህም ያልተጣራ ዘገባ ነበር፡፡ ድምጻችን ይሰማ አሁን ከደቂቃዎች በፊት ባደረገችው ማጣራት መሪዎቻችን አስከአሁን የትም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ማረጋገጥ ችላለች፡፡ ሆኖም የመሪዎቻችን ጠበቆች ‹‹ደንበኞቻችን የምመራመራ ፋይላቸው ከተዘጋ በኃላ ሊፈቱልን አልቻሉም›› በማለት በዛሬው እለት ፖሊስ ላይ ክስ መመስረታቸውንና ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለማየት ለሰኞ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱን አረጋግጠናል፡፡
የመሪዎቻችን ቤተሰቦችና መላው ሙስሊም ኅብረተሰብ ሊፈቱ ነው የሚለው ወረጃ ከተሰራጨበት ደቂቃ አንስቶ ጉዳዩ እውነት ከሆነ በመንግስት በኩል የታየ አውንታዊ ምላሽ ሆኗል በሚል ስሜት ሐሳቡን ሲገልጽ ነበር፡፡ በእርግጥም መንግስት ይህ አይነቱን እርምጃ ሊወስድ ከሆነ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በታላቅ ደስታ የሚቀበለው እና ለቀጣይም በመንግስትና በሙስሊሙ ማኅበረሰብ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት በአንድ ደረጃ የሚፈታ መሆኑን መናገር ይቻላል፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብም ይህ መረጃ እውን እንዲሆን በዱዓእ እንዲበረታ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment