አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ እኛ በፓርላማ!
ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈተ ህይወት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረጉን የተረከቡት የተከበሩት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጥቅምት 6/2005 በፓርላማ ተገኝተው በሚያደርጉት ንግግር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጉዳይ እንደሚያነሱ በሁሉም ዘንድ ተጠብቆ ነበር፡፡ እንደተጠበቀውም ሙስሊሞችና የምናደርገውን ትግል አስመልክቶ ከአንድ የፓርላማ አባል በቀረበላቸው ጥያቄ የጥቂት ደቂቃዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚሁ ንግግራቸውም የሃይማኖት እኩልነት በኢትዮጵያ እንደሰፈነና መንግስትም በሃይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጭራሽ እጁን እንደማያስገባ በህገመንግስቱ መደንገጉን በመጥቀስ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የተደረገው ‹‹ምርጫ›› በመጠናቀቁ ሕዝበ ሙስሊሙን ‹‹እንኳን ደስ አለህ!›› ብለዋል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነት በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ያለ ችግር መሆኑንም ለመጠቃቀስ ሞክረዋል፡፡ እኛም በንግግራቸው ዙሪያ የተወሰኑ ነጥቦችንና ግንዛቤዎችን ለማስቀመጥ ወደድን፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም! አልገባምም!›› ሲሉ ያደረጉት ንግግር በእውነቱ እጅግ ከእውነታ የራቀ ሀሰት መሆኑን ሚሊዮኖች ያለጥርጥር ይናገራሉ፡፡ አመት የተጠጋው የሙስሊሞች ተቃውሞ የተቀሰቀሰውም የመንግስት ጣልቃ ገብነት እጅግ ድንበር አልፎ ‹‹ሃይማኖትህንም እኛ ካልመረጥንልህ›› የሚል ደረጃ ላይ ስለደረሰ መሆኑን ሁላችንም እንረዳለን፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ሀይማኖቱ ላይ የታወጀበትን ጦርነት ለመመከት ቆርጦ ከተነሳበት ወቅት ጀምሮም ሲፈጸሙበት የነበሩት በደሎች ጣልቃ ገብነቱ ድንበር ማለፉን አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ እስቲ እንጠያየቅ! መስጊድ ገብተው ማሰገድ ብቻ የቀራቸው ይመስሉ የነበሩት ዶክተር ሽፈራውን የመሳሰሉ ሚኒስትሮች ‹‹ኢስላማዊ ትንተና›› ሲሰጡና ሕዝበ ሙስሊሙን ሲያስቆጡ የነበሩበት ሁኔታ እንደጣልቃ ገብነት አይቆጠር ይሆንን? መሳጂዶቻችንን እየሾፈሩና ያሻቸውን እየሰሩ ያሉት እነማን ናቸው? የኢህዴግ ካድሬዎች አይደሉምን? ኢማሞችን እየሻሩ እና እየሾሙ ያሉትስ? የኢህአዴግ ደህንነቶች አይደሉምን? የተተኮሱበት መስመር ገና ያልጠፋላቸውን አዳዲስ ጀለቢያዎችና ኮፍያዎች እየለበሱ ጁሙዓ ሶላት ላይ መስጊድ ውስጥ አብረውን ሊሰልሉ የሚሰግዱት በየሰፈራችን የምናውቃቸው ሙስሊም ያልሆኑ ወጣቶችስ ማናቸው? የኢህአዴግ ወጣት ሊግ አባላት አይደሉምን? በየመንገዱ የሚያልፉ ሙስሊሞችን እያገቱ ወደመጅሊስ ቅርጫ ጣቢያዎች ሲያግዙ የነበሩትስ እነማን ይሆኑ? መንግስት ያሰማራቸው ደህንነቶች አይደሉምን? ‹‹የፈለገ ቢሆን ምርጫ ከቀበሌ ውጭ አይካሄድም!›› እያሉ በየስብሰባ አዳራሹ መርዶ ሲግቱን የነበሩት ሰብሳቢዎችስ - የኢህአዴግ አመራር አባላትና ጭቃ ሹሞች አይደሉምን?
እውነት እርስዎ እንደሚሉት መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ የማይገባ ከሆነ ስለምን ይሆን ፌዴራል ፖሊሶች ሌሊት በየመስጊዱ ሰብረው እየገቡ ለአምልኮ የተሰበሰቡ ምእመናንን በጭስ እና በጥይት የሚቆሉት? መስጊዶች የጦር አውድማ አልያም የልምምድ ቦታ መስለዋቸው ይሆንን? በእውነቱ ባለፈው አመት መንግስት ሲፈጽማቸው የቆዩት ሃይማኖታዊ በደሎች መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ሃይማኖትን ተቆጣጥሮ የመሾፈር ጠንካራ ፍላጎት ያለው መሆኑን ነው የሚያሳዩት፡፡ ይህ እውነታ ለሙስሊሙም፣ ለኦርቶዶክሱም፣ ለፕሮቴስታንቱም እጅግ ግልጽ ከመውጣቱ የተነሳ ሊካድ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል - የመንግስት ባለስልጣናት እንኳ በግልጽ ከአፋቸው እስኪያወጡት ድረስ! መንግስት ከ‹‹ሀ›› እስከ ‹‹ፐ›› በእጁ ስር ጨምድዶ ሲያስፈጽመው የነበረው የመጅሊስ ምርጫ ድራማ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብለው ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ‹‹ልማት በሙሉ እስኪስተጓጎል ድረስ በሙስሊሞች ጉዳይ ተጠምደናልና መገላገል እንፈልጋለን›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የት ነበሩ ይሆን? አንድ የመንግስት ባለስልጣን ‹‹ልማት አቁሜ በየመስጊዱ መዋል ጀምሬያለሁ! ሙስሊሞች በስራ ጠምደውኛል›› እያለ በአደባባይ እየተናገረ በፓርላማ ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አልገባም›› ብሎ ህዝብን ለማታለል መሞከርስ እንደምን ከአገር መሪ ይጠበቃል?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክራሪነት በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ያለና ልንዋጋው የሚገባው ችግር እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ በእርግጥ አክራሪነትን የሚደግፍ ሃይማኖት እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹አክራሪነትን ለመዋጋት›› በሚል አገር አቀፍ ዘመቻ እየተደረገ ያለው ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ብቻ ነው፡፡ ‹‹አክራሪነትን ለመግታት›› እየተባሉ የሚሰጡት ስልጠናዎችና የሚደረጉት ስብሰባዎች በሙሉ ሙስሊሙን ብቻ የተመለከቱ ናቸው፡፡ ‹‹ከሃይማኖት አክራሪነት›› ጋር በተያያዘ ችግር እየደረሰባቸው ያሉት ሙስሊሞች ብቻ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየጠቀሱ ያሉት ‹‹የሃይማኖት አክራሪነት›› እሳቤ ግን ሙስሊሞችን ብቻ ለይቶ ለማጥቃትና የፈለጉትን አጀንዳ እንደልብ ለማስፈጸም መሳሪያ እየሆነ ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡ መንግስት የመስጊድ ኢማሞችን በካድሬዎቹ እያስፈራራና በፌደራሎች ቤታቸው ድረስ መጥቶ እያሳፈሰ በየዩኒቨርሲቲ ግቢዎች ‹‹አክራሪነትን በመግታት›› ስም ሲሰጣቸው የነበሩት ስልጠናዎች ሌሎች ሃይማኖቶች ላይ ተፈጽመው አያውቁም፡፡ ስለዚህ ‹‹አክራሪነት የሁሉም ችግር ነው›› እያሉ እውነተኛን ንግግር ለሀሰት አላማ በማዋል ለማታለል ከመሞከር ይልቅ ‹‹ሙስሊሞች በሙሉ አክራሪ ስለሆኑ ዘመቻ ያስፈልጋቸዋል!›› ብለው ድርጊታቸው የሚመሰክረውን በአንደበታቸው ቢያምኑ ይሻል ነበር፡፡ በመሠረቱ ይህንን የምንለው ባለፈው አመት ሙሉ እኛ ሙስሊሞች ላይ በመንግስት ሲፈጸም የነበረው እምነትን በግድ የማስቀየር ዘመቻ በሌሎች ወንድሞቻችን ላይ የምንመኘው ሆኖ አይደለም፡፡ ይህን አይነቱን በደል እንኳን አጋሮቻችን ሆነው በቆዩት የክርስትና እና ሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን ላይ ይቅርና በጠላቶቻችንም ላይ አንመኘውም! እኛ ከደረሰብን በደል ነጻ መሆናቸውም አጋርነታቸውን እንደምንጠይቅ ሁሉ የሚያስደስተን እንጂ የሚያስከፋን አለመሆኑን በአጽንኦት እንገልጻለን፡፡ እስካሁን ላደረጉልን የሞራል ድጋፍም እናመሰግናቸዋለን፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጅሊሱን ምርጫ አስመልክተው የተናገሩትም ነገር እንዲሁ በጣም የብዙዎችን ቀልብ የሰበረ ነበር፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ሳይደግፈው በመንግስት አስገዳጅነት የተፈጸመውን እና ህዝቡ በሙሉ ባዶ ያስቀረውን ምርጫ አይሉት ቅርጫ አንስተው ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ!›› ማለታቸው በጣም ያስገርማል፡፡ ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለምርጫው የደረሳቸው ሪፖርት ምንጩ ከየት ይሆን? ቦሌ ክፍለ ከተማ ላይ 26 ሰው ብቻ መገኘቱን አልሰሙ ይሆን? ቁጥራቸው 9 ሺህ ነው በተባሉት የምርጫ ጣቢያዎች ሰው ጠፍቶ ቀብር የሚሄዱ ሙስሊሞችን እያጋዙ ለማስመረጥ መሞከራቸውን አልሰሙ ይሆን? በአዲስ አበባ፣ በጅማ፣ በሰበታ፣ በሱሉልታ፣ በደንቢ፣ በቢቸና፣ በቻግኒ፣ በደሴ፣ በገርባ፣ በደጋን፣ በጉራራ፣ በዱከም፣ በሞጆ፣ በከፋ፣ በቦንጋ፣ በዲላ፣ በጉራጌ ዞን፣ በወልቂጤና ዙሪያዋ፣ በሎጊያ፣ በአይሳይታ፣ በጭሮ፣ በሰንበቴ፣ በመቀሌ፣ በአድዋ፣ በአላማጣ እና በሌሎችም ቦታዎች ከ 50 እና 100 ያልበለጡ ካድሬዎች እና አህባሾች ብቻቸውን ‹‹ምርጫ›› ማካሄዳቸውን አልሰሙ ይሆን? በብዙ የኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል እና ደቡብ ክልል ወረዳዎች ከናካቴው ምርጫ አለመደረጉን አልሰሙ ይሆን? በአማራ እና በአፋር ክልል የምርጫ ጣቢያዎች ከነጭራሹ ከምርጫ አስፈጻሚዎቹ በቀር ሰው ብቅ አለማለቱን አልሰሙ ይሆን? ነው ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለማዋል ጀለቢያ የለበሱ ሙስሊም ያልሆኑ ካድሬዎች የተሰባሰቡባቸውን 11 የምርጫ ጣቢያዎች ቆጥረው ነው ህዝበ ሙስሊሙ የመረጠ የመሰላቸው? ሃይማኖታዊ ጉዳያችንን እንዳሰኛቸው የሚሾፍሩልን የኢህአዴግ ደህንነቶች ምን ሲሰሩ እንደሚውሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያውቁም ብለን እንደምድም ይሆን እንዴ?
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ላይ ሲወጡ አንዳንድ ለውጦች ሊኖሩና ችግሮችም ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ተጠብቆ ነበር፡፡ ያንንም ለማመቻቸት ሕዝበ ሙስሊሙ ሲያደርገው የነበረውን ተቃውሞ ጋብ በማድረግ ከአዲሱ መንግስት ጋር ለመደማመጥ ፍቃደኛ መሆኑን አሳይቶ ነበር፡፡ ተቃውሞውን ጋብ ማድረጉ በሌላ በተተረጎመበት ጊዜም ተቃውሞውን ዳግም በማጧጧፍ ጥያቄዎቹ ሳይመለሱለት ቤቱ የማይገባ መሆኑን በኢዱ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አሳይቷል፡፡ የህዝቡን ድምጽ ያለጥርጥር የሚያሳየው ይኸው መሆኑ እንደረፋድ ጸሐይ ግልጽ ሆኖ ሳለ ግን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝብ ያስቆጣ የፓርላማ ንግግር ድጋሚ መናገራቸው የለውጥ ፍላጎት አደባባይ ባዋለው ህዝብ ላይ የሚያሳድረው ቅያሜ አመታት የሚፈቱት እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ‹‹ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳን ኢህአዴግ ጥረት ሊያደርግ ይገባዋል!›› የምንለውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም! አሁንም ደጋግመን እንናገራለን፡- ‹‹ጥያቄዎቻችን ቀላልና ግልጽ ናቸው! ለመመለስም ጊዜው አሁንም አልረፈደም! ድምጻችን ይሰማ! ከህዝብ ድምጽ የበለጠ ሊሰማ የሚገባው ሌላ ድምጽ የለም!!!››
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment