Tuesday, October 30, 2012

ታላቅ የዳዕዋ እና የግብዣ ፕሮግራም በጂማ ዩቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ተካሄደ!!


ታላቅ የዳዕዋ እና የግብዣ ፕሮግራም በጂማ ዩቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ተካሄደ!!

እሁድ ማለትም ጥቅምት 18-02-2005 በግዙፉ የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ (JUMJ) Main Campus አንድ ታሪካዊና አስገራሚ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ጀማዓው አራት ቅርንጫፎች አሉት፡፡ የዓረፋ በዓል ጥቂት ቀናት እንደቀሩት ነበር ‹‹ለምን አራቱንም ቅርንጫፎች የሚያገናኝ የጀመዓዎቹን መሰረታዊ የዓላማ አንድነት የሚያሳይ የዳዕዋና የምሳ ፕሮግራም አይዘጋጅም?›› የሚለው ሀሳብ የተፀነሰው፡፡ በዓረፋ በዓል ቀን ጀመዓው ሌላ ዝግጅት የነበረው በመሆኑ የምሳ ፕሮግራሙ እሁድ ተደረገ፡፡ ግብዣው የአራቱ ግቢ ጀማዓዎች (ማለትም Main campus, Business and Economics College, Agricultural And Veterinary Medicine, and Institute of technology(JiT)) ተማሪዎች፣ የጂማ ከተማ ወጣት ጀመዓዎችና ተጋባዥ እንግዶችን ያካተተ ነበር፡፡

ከ40,000.00 ብር (አርባ ሺህ ብር) በላይ እንደወጣበት እና 20 በጎች እንደታረዱበት የተነገረለት ይህ ዝግጅት በጀመዓው ድንቅና ብርቅዬ ወንድምና እህት አባላት ንቁ ተሳትፎ ያለ ምንም ቅሬታ ተካሂዷል፡፡ በእለቱ ሙስሊሙ ተማሪ አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበትና የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመዓዎች ዓላማ ትምህርትንና ሀይማኖትን ጎን ለጎን በማስኬድ ጥሩ ዓለማዊ ዕውቀት ያለው ሀይማኖተኛ ሙስሊም ዜጋ ማምረት በመሆኑ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ሲመረቁ እንደ ዓለማዊ ትምህርቱ ሁሉ ዲናቸውን ጠበቅ ማድረግ እንዳለባቸው የተነገረ ሲሆን ፕሮግራሙ ላይ በአንድ ወንድም የተነበበው ግጥም ታዳሚውን ለለቅሶ የጋበዘና ያስለቀሰም ጭምር ነበር፡፡

ከ2500-3000 ታዳሚዎች የተገኙበት ይህ ፕሮግራም የጀመዓውን ታላቅነት በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን ጀመዓው በበርካታ ጀግናና ከፍተኛ የመስራት ብቃት(Potential) ያላቸው ወንድሞችና እህቶች የታጨቀ(የተሞላ) መሆኑ ፍንትው ብሎ የታየበት ነበር፡፡ ታዳሚዎች ፕሮግራሙ በጀመዓው ዓባላት መካከል ከፍተኛ የመዋደድ፣የመተሳሰብና የመፈቃቀር ስሜት የፈጠረ በመሆኑ ከተማሪው ብዛት የተነሳ ጥቂት የመስተንግዶ መዘግየት የነበረ ቢሆንም ፍፁም እንደተደሰቱበት የገለፁ ሲሆን እንዲህ ዓይነት መድረኮች በየዓመቱ መደጋገም እንዳለባቸው ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

በኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገውና የጀመዓውን ፍፁም አይበገሬ ጥንካሬ ፣ጀግንነት ፣ ውበትና ውስብስብነት እንዲሁም ንቁና ጠንቃቃ የሰው ሀይል ባለቤትነት ያሳየው ይህ ፕሮግራም በአላህ ፈቃድ ያለምንም ችግር በሰላም ተጠናቅቆ ሙሉ የጀመዓውን አባላት በተለይ ደግሞ የፕሮግራሙን አዘጋጆች በደስታ ጮቤ አስረግጧል፡፡ በመሆኑም ጀመዓው እንዲህ ዓይነት መድረኮች በሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች ቢለመዱ በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበቡ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ችግር የማይፈጥር እስከሆነ ድረስ ሁሉም ተግባራዊ እንዲያደርጉት አሳስቧል፡፡

አሏሁ አክበር!!!

No comments:

Post a Comment