ከቀናቶች ሁሉ በላጭ በሆኑት ቀናቶች በላጭ የሆነ ዒባዳ!
የዙልሒጃ ወር አስሩ የመጀመሪያ ቀናት ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ በነዚሁ ቀናት የሚሰሩ የአምልኮ ተግባራት (ዒባዳዎች) በሌሎች ቀናት ከሚሰሩት ሁሉ በላጭ መሆናቸውን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናግረዋል፡፡ አቅሙ ለቻለ ሰው ሐጅና ዑምራ ማድረግ በነዚህ ቀናት ውስጥ ሊሰሩ ከሚችሉ የአምልኮ ተግባራት ሁሉ በላጩ ነው፡፡ ጾም መጾም፣ አላህን በብዛት ማወደስ፣ ተክቢራ ማለት፣ ቁርአንን ማንበብ፣ በጥቅሉ መልካም የተባሉ ተግባራትን ሁሉ በነዚህ ቀናት መፈጸም እጥፍ ድርብ ምንዳ ያስገኛል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘጠነኛውን ቀን (የፊታችን ሐሙስ) መጾምን አስመልክተው ‹‹ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል›› ብለዋል፡፡ በላጭ የሆኑ ዒባዳዎችን መርጦ በነዚህ በላጭ በሆኑ ቀናት መፈጸም ብልህነት ነው፡፡
‹‹ከአምልኮ ተግባራት ሁሉ የትኛው ይበልጣል?›› የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ዑለማዎች ወቅቱ የሚጠይቀውን አምልኮ ከመፈጸም የላቀ በላጭ የአምልኮ ተግባር እንደሌለ ይስማማሉ፡፡ አዛን ሲል በላጩ አምልኮ ሰላት መስገድ ነው፡፡ ቁርአን እያነበበ ለነበረ ሰው ወላጆቹ ቢጠሩት ቁርአኑን ከመቀጠል ይልቅ ለወላጆቹ ምላሽ መስጠት በላጭ የአምልኮ ተግባር ነው፡፡ አላህን እያወደሰ ለነበረ ሰው ተጣልተው የነበሩ ሰዎችን እንዲያስታርቅ ቢጠየቅ ማስታረቅ ለሱ በላጭ ኢባዳ ነው፡፡ ‹‹ይበልጥ አንገብጋቢ የሆኑ አላህ የሚወዳቸው ተግባራትን መፈጸም ከአምልኮ ተግባራት ሁሉ በላጭ አምልኮ ነው›› በሚለው ሃሳብ ከተስማማን ‹‹በአሁኑ ሰዓት ይበልጥ አሳሳቢ የሆነው ኢስላማዊ ግዴታችን ምንድነው?›› የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ግድ ይለናል፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ህልውናውን በሚፈታተንና ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የተቀነባበረ ዘመቻ እየተጠቃ ይገኛል፡፡ ኢስላምን እምነቱ በሚያዘው መልኩ ሳይሆን ጠላቶቹ በሚፈልጉት መንገድ እንዲረዳውና እንዲተገብረው ከፍተኛ ጫና እተደረገ ይገኛል፡፡ በብዙ ጥረት ያቋቋማቸው ጥቂት ተቋማት እየተዘጉ ወይም አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ ሽባ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከትምህርት ተቋማትና ከኢኮኖሚው ዘርፍ በተጠኑ መንገዶች እንዲርቅ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ዑለማዎችና ዳኢዎች እስር ቤት እየታጎሩ ይገኛሉ፡፡ ሸኾች ደረሳዎቻቸውን በትነው ማቅራት እንዲያቆሙ እየተደረገ ነው፡፡ የእውቀት ምንጮችን ለማድረቅ መጽሄቶችና ጋዜጦች እንዳይወጡ ታግደዋል፡፡ … ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመ ባለበት ተጨባጭ አንድ ሙስሊም ዲኑን ለማስጠበቅ ከሚያደርገው ትግል የበለጠ አላህ ዘንድ የሚያቃርበው ተግባር ከቶ ምን ሊኖር ይችላል? አዎ! ከምንም ነገር በላይ ያለንበት ወቅት የሚጠይቀው አንገብጋቢ አምልኮ እምነታችንን ለማስጠበቅ ሁላችንም አቅማችን የሚችለውን ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹የሙስሊሞች ጉዳይ የማያሳሰበው ሰው ከኛ አይደለም›› ሲሉ ከግል አምልኮ ተግባራት ባለፈ ለኡማው የመጨነቅንና የመስራትን አሳሳቢነት ከበድ ባለ ሁኔታ ገልጸውታል፡፡ በዙልሂጃ አስሩ ምርጥ ቀናት ዲናችንን ለማስከበር የምናደርገው ጥረት ግዴታን ከመወጣት ባለፈ እጥፍ ድርብ ምንዳ ያስገኝልናል፡፡ ይህን ከተገነዘብን ቀጣይ የሚሆነው ‹‹ዲናችንን ለመጠበቅ በነዚህ ቀናት ምን ምን ስራዎች ልንሰራ እንችላለን?›› የሚለው ይሆናል፡፡ የሚከተሉት ስራዎች ለአብነት ያህል ተቀምጠዋል፡-
• በመንግስት የተደረገው የመጅሊስ ምርጫ እንደማይወክለንና ለተመራጮችም እውቅና እንደማንሰጥ በማያዳግም ሁኔታ ሚሊዮኖች ሆነን ለመግለጽ ከፊት ለፊታችን የሚገኘው የዒድ አልአድሀ በዓል ወርቃማ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህን ወርቃማ ዕድል ለመጠቀም ደግሞ ጠንካራ ዝግጅት ያስፈልጋልና ሁላችንም በየመስጂዳችን እራሳችንን የማደራጀት ስራ በመስራት የሚወጣውን ፕሮግራም ለማስፈጸም እንዘጋጅ፡፡
• በየመስጂዱ የምናደራጃቸውን ስብስቦች በመጠቀም የዒድ ቀን ሁሉም ህብረተሰብ በነቂስ ወደ ስታዲየም እንዲመጣ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማድረግ፡፡
• ለኢድ ወደ ክልል የምንሄድ ሰዎች በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁትን የግንዛቤ ማስጨበጫ በራሪ ወረቀቶች በመውሰድ የምንሄድበት አካባቢ ሰዎችን የማንቃትና በዒድ ቀን ጠንካራ ተቃውሞ እንዲያደርጉ የመቀስቀስ ስራ መስራት፡፡
• አላህ ወፍቆን ሃጅ የሄድን ሰዎች አላህ ለመላኢኮቹ ‹‹ባሮቼን ተመልከቱ›› እያለ በባሮቹ ደስ መሰኘቱን የሚገልጽበት ታላቅ ክብር ያለው ኢባዳ ነውና በዐረፋ ተራራ ወደ አላህ በመዋደቅና በማልቀስ ብሶታችንን እናሰማለን፡፡ በዳዮችን እንዲይዝልን እንለምነዋለን፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ‹‹ከዱዓ ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው፡፡››
• ዘጠነኛውን ቀን (የፊታችን ሐሙስ) ሁላችንም በመጾም ዕለቱን በዱዓ ተጠናክረን ማሳለፍ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘጠነኛውን ቀን መጾምን አስመልክተው ‹‹ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል›› ብለዋል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ ክበር!

No comments:
Post a Comment