Saturday, November 3, 2012

የኢህአዴግ መንግስት የስኮየር ዋን ጉዞ (1 x1 =1)


አንብቡኝ--ካልሆነ ይከፋኛል!
<የኢህአዴግ መንግስት የስኮየር ዋን ጉዞ (1 x1 =1)>

የኢህአዴግ መንግስት ህጋዊ መሰረት ያላቸውን ቀላልና ግልፅ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን 3 (ሶስት) ጥያቄዎች በበጎ ጎኑ ተመልክቶ ከጅምሩ ገና መልስ ሰጥቶ የሙስሊሙን ጥያቄ ቢፈታ ኖሮ ትልቅ የፓለቲካ ትርፍ ያጋብስ ነበር የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ። በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድም ቢሆን ሃገራችን እውነትም የድሞክራሲ ግንባታ ሂደት ውስጥ መሆኖን ጭምር ይመሰክረለት ነበር። ታዲየ ኢህአዴግ ይህን ማድርግ ሲችል ወዳልተፍለግ የ “ስኮየር ዋን ጉዞ” ውስጥ ምን አስገባው? ይህንን የፓለቲካ ትርፍ ለምን ናቀው? ለዚህ ጥያቄ የተለያዮ ታዋቂ አለም አቀፍ የፓለቲካ ተንተኞች የተለያዩ ምክናያቶችን ያነሳሉ። ከነዚህም መካከል፦

1. የኢህአዴግ የፓለቲካ ስርዓት በ “ዲሞክራሲ ቅብ” አምባገነናዊ ስርዓት መሆኑ ትልቁን ድርሻ ይይዛል የሚሉት ብዙ ናቸው። ሁልጊዜ በጠረንጴዛ ዙሪያ ተውያይቶ ለችገሮች መፍትሄ መስጠት ለአምበገነኖች እንደ ሸንፈት መገለጫ መታየቱና ሁሉም ነገር በሃይል መልስ ያገኛል ከሚለው የስራዓታቸው መንፈስ የመነጨ ነው የሚሉ በርከት ያሉ የፓለቲካ ምሁራን አሉ።
2. መንግስት የ“አህባሽን” አስተምህሮት ከውጭ ሃይሎች ጋር (በተለይም ከአሜሪካና ከፅዩወናዊት ኢስራኤል) ጋር በማበር በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ እንደሚጭን ለዚህም ትልቁ ምክናያት ኢትዮጵያ አሸባሪነትን በመዋጋቱ ረገድ ያላትን ጂኦ ፓለቲካዊ ጥቅም ከግምት በማስገባትና የኢትዩጵያን ክፍለ አህጉራዊ ተሰሚነት ከማሳደግ የመነጨ እንደሆነና ይህም ጉዳይ በጥልቀት መስራት ያሰፈለገበት ምክናያት ከአረቡ አለም ና ከሰሜን አፍሪካው የ2011/12 ማዕበል ጋር ተያይዞ እንደሆነ ብዙዎች በእርግጠኝነት ይሞግታሉ። በተለይም ከነ ሁስኒ ሙባረክ ከስልጣን መወገድ ጋር ተያይዞ እነ እስራኤል ኢትዮጵያን በጥብቅ እጃቸው ውስት ማስገባትን ይሻሉ የሚሉት ጥቂት አይደሉም።
3. አንዳንዶቸ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ያለማንም የወጭ ሃይል ጣልቃ ገብነት በአሜሪካና በአውሮፓዊያን ዘንድ ተሰሚነትን ለማግኘትና “አሻበሪነትን” በመዋጋት ስም “ደጎሰ ያለ ዶላርና ዮሮ” ለማጋበስ ካለው የ “ንዋይ ፍቅር” ነው ይላሉ። ይህንንም ለማድረግ የ “አህባሸን አስተምህሮት” የሚቃወሙትን ንፁህ ሙስሊሞች አስተምህሮቱን በሚቃወሙበት ሰዓት ወደ ሁከት ውስጥ በማስገባት ኢትዩጵያዊያን ሙስሊሞች “አሻባሪዎች” ስለሆኑ “አሸባሪነትን” እየታገልኩ ነው ብሎ ማሳየት ይፈልጋል።በዚህም ሳቢያ ረዝም ያሉ የእርዳታ እጆች ይዘረጉለታል።
4. ከፊሎቹ ደግሞ ተነሳሽነቱን ከላይ እንደተመለከትነው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያያዙትና መሰረታዊ ምክናያቱን ግን ከረዥም ግዜ “የህልም ቅዥት” ጋር ያያይዙታል። “ህልም ተፍርቶ ሳይታኛ አይታደርም...” ይሉሃል ይሄ ነው። ይህም ማለት በላፉት 21 አመታት የኢህአዴግ ስርዓት በተለይም ደግሞ ባለፉት 15 አመታት ውስጥ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ህገ መንግስታቸው ያጎናፀፋቸውን የሃይማኖት ነፃነት መብት ተጠቅመው እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሃይማኖታቸው ያላቸው ግንዛቤ በመሻሻሉና ስለሃገራቸውም ፓለቲካዊ፡ማህበራዊና የልማት እንቅሰቃሴ ጉዳይ ንቃተ ሀሊናቸው ማደጉን ተከትሎ የተፈጠረ ስገት ይህንን ችግር እንደፈጠረው ይናገራሉ። ይህ የሙስሊሙ አወንታዊ እድገት በዚሁ ከቀጠለ ኢትዩጵያ ወደፊት በሙስሊም መሪዎች የማተመረበትና የ “ሸሪአ መንግሰት” ይመስረት የሚባልበት ጊዜ ሩቅ ስለማይሆን “ሳይርቅ በቅርቡ...” አንዲሉ በ “አሸባሪነት” ስም የሙስሊሞችን እንድነት መበታተን፡ ሃይማኖታዊ ግንዛቤያቸውን ሊያሳድጉ ይችላሉ ብለው ያሰቦቸውን ኢስላማዊ የትምህርት ማዕከላት፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ኢስላማዊ ድርጅቶችንና የመገናኛ አውታሮችን ብሎም ታዋቂ ሸኸዎቸን፡ኡሰታዞችን፡ አርቲስቶችን፡ ጋዜጠኞችንና በትምህርታቸው ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸውን ታዋቂ ግለሰቦችን ሁሉ ለማዳከም ታልሞ የተጀመረ ጅማሮ እንደሆነ ብዘዎች ይናገራሉ።
5. የችግሩ መንስኤዎች ራሳቸው መጅሊስ ላይ የሚስሩት ከሙስሊም ህብረተስብ ይሁንታ ውጭ በጎሮ በር ገብተው የኢትዮጵያ ሙስሊምን እንወክላልን የሚሉ “እውቀት የነጠፈባቸው” የሚጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች የአህባሽ አስተምህሮት እቀንቃኝ መሆናቸው ይህንን ችግር ፈጥሮታል የሚሉ ደግሞ ወገኖች አሉ። ማለትም ለአህባሽ አመለካከተ ከላቸው ፍቅር የተነሳ ለመንግስት ሰለ አብዛሀኛው የአትዮጵያ ሙስሊሞች ትክክለና ገፅታ የተዛባ መረጃ ለመንግስት በመስጠት የችግሩን መሰረት ከዚሁ ከመጅሊሱ ጋርም ያገናኙታል።
የትኛውንም ምክንያት ለችግሩ መነሻነት እንስጠው ዋናው ነገር ያለው ግን መንግስት በአሁኑ ስአት የ “አህባሸን አስተምህሮት” በከፈተኛ ሁኔታ ደግፉ በሚያደረጋቸው ኢ-ህገ መንግስታዊ አካሄድ እንዳሰበው ውጤት አግኝቷል ወይ? የተነሳላቸውን አላማዎች አሳክቷል ወይ? ብሎ ጠይቆ መልስ መስጠቱ ላይ ነው ቁልፉ ነገር።

<ውጤቱ ከስኮየር ዋንም ያነሰ ነው (1x1<1)! >

እንደ እኔ ከሆነ የመንግስት አካሄድ አይደለም ያሰባቸውን አላማዎች ማሳካት ይቅርና ከስኮየር ዋን (1x1=1)ም አልፎ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል ባይ ነኝ። አዎን! ሲነሳ ከነበረበት በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ከነበረው የ “ተወሰነ ታመኝነትም” እንኳን ሳይቀር ተዋርዶ በአሁን ሰዓት ህዝቡ ኢህአዴግን ጨርሶ ወደመጥላት ተቀይሯል። በዚሁ ሂደትም ከቀጠለ ወደፊት ኢህአዴግን ሁሉም አንቅሮ መትፋቱ የማይቀር እውነታ ነው።የቆመለትን ህዝብን የማገልገል ተልዕኮ ወደጎን ትቶ “አህባሸን” መንግስታዊ ሀይማኖት እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ለማጥመቅ የሚያደርገው ሩጭ በሃገራችን ሁለንታነዊ እድገት ላይ ባለፈው አንድ አመትም ይሁን ወደፊት የሚያሳድረው ተፅዕኖ ተራውን ህዝብ ሳይቀር መንግስት ለምን ልማትን ትቶ የሃገርን ህዝብ ማሰቃየት አስፈለገው የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ የማይቀረ ነገር ነው። ለምን ብሎ የሚጥይቅ ሰው ሁሉ ደግሞ የኢህአዴግን መንግስት ታረካዊ ስህተቶችን ከማስተጋባትና ከመኮንን ውጭ ሌላ አመራጭ አይኖረውም።ይህ ጉዳይ ደግሞ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ኢህአዴግ ጠንቅቆ ያውቀዋል። አምባገነናዊ ስርዓትም ቢሆን ህዝብ የስልጣኑ መሰረት መሆኑን ሳያውቀው አይቀርም። እኛም የእናንትን “የሞኝ ምናባዊ ስዕላችሁን” ወደገሃዱ አለም ለማምጣት ስተባክኑ የከሰራችሁበትን “ሳይርቅ በቅርቡ...” ሞኝ ብሄላቸሁን ትታቸሁ ሳይመሽ በጊዜ ነፈሳችሁን በእውነት ብተናግሯት መልካም እንደሆነ ሙስሊሙ ህብረተስብ ይሰማዋል። አጥፍቶ መመለስ ብልህነት ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊም የሚፈልገው የ “ሸሪአ መንግስት” አይደለም የሚፈልገውም ስልጣን አይደለም ይልቁንስ የሚፈለገው ላነሳቸው ቀላልና ህገመንግስታዊ የመብት ጥቄዎች መልስ አግኘቶ ወደ ስራው መመለስን ነው። አራት ነጥብ። ከዚህ አልፎ በጥያቄዎቹ ላይ መፍላስፍና የተለያዩ መላምቶችን መስጠት “ተልፈስፍሶ መውደቅን” እንጅ ሌላ ትርፍ ያመጣል ብለን አንገምትም።

<ሙስሊሙ ህብረተስብ ከዚህ ሰላማዊ ትግል ምን ትርፍ አገኘ...>


ምናልባት ከላይ በቁጥር የተዘረዘሩትን መነሻ ምክናያቶች ስንመለካታቸው ኢህአዴግ አብዛሃኛዎቹን ነገሮች ሰርቷል ብለን ልናስብ እንችላለን።ለምሳሌ፦የተለያዪ ኢስላማዊ ይህትመት ስራዎች ተዘግተዋል።ታዋቂ ግለሰቦች ታስረዋል።ኢስላማዊ ድርጅቶች ተዘግተዋልና መሰል ድርጊቶች ተፈፅመዋል። ዋናው ቁምነገር ግን መንግስት ማሳየት የፈለገውን የተነሳበትን በሙስሊሞች ላይ በምናቡ ስሎ በግሃድ አለሙ ማሳየት የፈለገውን የአሸባሪነትን ስዕል መፍጠር ግን አልቻለም። ለምን አልቻለም? ምክናያቱም የኢትዩጵያ ሙስሊሞች ሁለመናችን ሰላም ስለሆነ ከሰለማዊ መንገድ ውጭ ሌሎች የሁከት መንገዶችን ስላልመረጥን። በየግዜው በመንግስት ተንኳሸነት በተፍጠሩት ግጭቶች ወቅት እንኳን የብዙ ወንድሞች ህይወት ሲያልፍ፡ ብዙዎች አካለ ጎደሉ ሲሆኑም እያየን ሙስሊሞች የመረጥነው መንገድ ሰለማዊ ብቻ መሆኑ መንግስትን አንገቱን ከማስደፍት አልፎ በዝረራ ጥሎታል። የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን እንዲያቆም መንግስትን ጠይቀዋል። የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ህገ-መንገስታዊ የመብት ጥያቄና ሰለማዊ የትግል ሂደት ድጋፍ ችረውታል። ከዚህም ሁሉ በላይ የኢህአዴግ አመራሮች እንደተመኙት ሙስሊሙን መከፋፈል ሳይቻላቸው ቀርቷል። ይልቁን በታቃራኒው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በታሪክ ባልታየ መልኩ ስለ አንደነቱ በተግባር አስመስክሯል። “ደጋን” ላይ ለሞቱት ወንደሞቹ የኦሮሚያ መስሊሞች ውስጣቸው ደምቷል።
“አሳሳ” ለይ በገፍ ለተገደሉት ንፁሃን ወንድሞች ደጋኖች አንብተዋል። አዎን! አንዳቸው ለእንዳቸው የ “ፅናት ነሽዳን ነሸደዋል”። ከዚሀ በላይ ለአንደ ሙስሊም ስኬት የለም። ከዚሀ በላይም ጠላትን የሚያወርድ ሃይል የለም። ይህ የመብት ጥያቄ የተወሰኑ ግለሰቦች ጣያቄ አለመሆኑንና መንግስት እንደሚለው በተውሰኑ ግለሰቦች የሚመራ ሂደት ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የሚመለከተውና የሚጋራው የጋራ ጉዳይ መሆኑን “እውነታ በማያመነው የኢህአደግ አይኖችም” ጭምር ተመስክሮለታል። ይህ ታላቅ ትርፍ ነው። እጅግ ውድ ስኬት!

አንብቡኝ--ካልሆነ ይከፋኛል! ስለዚህ ኢህአደጎች እስካሁንም የእኛን አንድነት መከፋፈል እንዳልቻሉት ወደፊትም ማድረግ እንዳይችሉ ደግሞ ይህ ሰለማዊ ትግላችን ሰፋ ባለና በተረጋጋ መንፈስ፡ መደማመጥና መናበብ በተሞላበት የፅናት ጎዳና መታገልን ይጠይቃል። አላህም ሁልጊዜ ለእውነት ከሚታገሉ ህዝቦች ጎን ነው።እንበርታ! ኢንሻአላሀ--አላህ ያግዘናል።

No comments:

Post a Comment