በቃሊቲ
ማረሚያ ቤት በሀሰት ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ተወዳጅ
ዳኢያን፣ኡለሞች እና ጋዘጠኞችን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊም እየዘየራቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ እስረኞችን መጠየቅ በሚፈቀድበት ሰአት በሙላ ረጃጅም ሰልፎች ሳይበግሩት በትዕግስት በመሰለፍ ተራውን
በመጠበቅ ኮሚቶዎቻችንን እየዘየረ እንደሚገኝ ታውቆል፡፡ኮሚቴዎቻችንም እጅግ ደስ በሚያሰኝ ፅናት ላይ እንደሚገኙና
የጤናቸው ሁኔታም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎል፡፡ ሊዘይራቸው ለሚመጣው ህዝበ ሙስሊም በሙላ በፈገግታ
የተሞላ ፊታቸውን የሚሳዩ ሲሆን በውስጣቸው ያለው ደስታና ፅናትም በፊታቸው ላይ እንደሚነበብ ለማየት
ተችሎል፡፡ ሊዘይራቸው ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሚመጣ በብዙ ሺህ ለሚቆጠረው ህዝበ ሙስሊምም መላው የኢትዬጲያ
ሙስሊም ህብረተሰብ ወደ አላህ ብቻ በመመለስ በዱዐ እንዲበረታና እንዲያግዛቸው አደራ ማለታቸውን ምንጮቻችን
ገልፀዋል፡፡ ኮሚቴዎቻችን፣ ኡለሞቻችን እና ጋዜጠኞቻችን የፊታችን ህዳር 13 ልደታ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ
ቤት በመቅረብ ለቀረበባቸው የሃሰት ክስ ምላሻቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርቡ በተጠየቁት መሰረት በጠበቆቻቸው
አማካኝነት ለክሱ ያላቸውን ምላሽ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ሁላችንም ሁሌም በምናደርገው ልዩ ዱዐ በግፍ የታሰሩትን
ወንድሞችችንን እንድናስታውሳቸው ዳግም አደራ እንላለን፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሙስሊም!!!!
አላሁ አክበር!!!!
ድል ለኢትዮጲያ ሙስሊም!!!!
አላሁ አክበር!!!!
No comments:
Post a Comment