6፡17
አሁን መሪዎቻችንን የመጠየቂያ ሠዓት በመጠናቀቁ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በር ተዘግቷል፡፡ በመርሐ ግብራችን መሰረት ዚያራችን ያበቃ በመሆኑም በሰላም ከአሁን ጀምሮ ሁላችንም (መሪዎቻችንን የዘየርንም ሆነ ያልዘየርን) ወደየቤታችን እንመለስ፡፡ የዚያራ መርሐ ግብሩን ሪፖርታዥ አጠናቅረን ከአፍታ ቆይታ በኋላ እናቀርባለን፤ አብራችሁን ቆዩ፡፡

ከቀኑ 6፡03
እሰከ አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከማለዳው 1:30 ቃሊቲ የደረሱ ሰዎች ከሕዝቡ ብዛት አንጻር ቃሊቲ ገብተው መሪዎቻችንን መጎብኘት አልቻሉም፡፡ የሕዝቡ ቁጥር ከተገመተውም በላይ ነው፡፡ አላሁ አክበር፡፡
እሰከ አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከማለዳው 1:30 ቃሊቲ የደረሱ ሰዎች ከሕዝቡ ብዛት አንጻር ቃሊቲ ገብተው መሪዎቻችንን መጎብኘት አልቻሉም፡፡ የሕዝቡ ቁጥር ከተገመተውም በላይ ነው፡፡ አላሁ አክበር፡፡
ከቃሊቲ የመልስ ጉዞ ወደ ቤት
5፡54
በቃሊቲ ታሪክ እንደ አዲስ እየተጻፈ ነው፡፡ የታሪኩ ፈጻሚም ጸሐፊም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ላይ ያልታየ የኅሊና እስረኞችን የመጎብኘት ሕዝባዊ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬም አንናገራለን ሕዝብ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር የአላህ እርዳታ እየተከተለን ነው፡፡
በቃሊቲ ታሪክ እንደ አዲስ እየተጻፈ ነው፡፡ የታሪኩ ፈጻሚም ጸሐፊም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ላይ ያልታየ የኅሊና እስረኞችን የመጎብኘት ሕዝባዊ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬም አንናገራለን ሕዝብ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር የአላህ እርዳታ እየተከተለን ነው፡፡
ወደ ቤታችን ስንመለስ የሚገጥሙን ትንኮሳዎች ስለሚኖሩ ሁሉንም ለሰላም ስንል በመታገስ ወደ ትልቁ ዓላማችን እንገስግስ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!!
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!!
የቃሊቲ አካባቢ የረፋድ ጸሐይ ብርቱ ቢሆንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ጸሐዩ ሳይበግረው ወረፋው ላይ ቋሟል፡፡ የሕዝቡ ትእግስትና ጽናት የምርም ያስደንቃል፡፡
5፡25
በቃሊቲና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሌሎች ሕዝባዊ ትዕንቶቻችን እንደታየው ወረፋ ላይ ለሚገኙ ሙስሊም ዚያራ አድራጊዎች መብል እና ውሃ በመስጠት አጋርነታቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡
በቃሊቲና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሌሎች ሕዝባዊ ትዕንቶቻችን እንደታየው ወረፋ ላይ ለሚገኙ ሙስሊም ዚያራ አድራጊዎች መብል እና ውሃ በመስጠት አጋርነታቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከረፋዱ 4፡46
ወደ ቃሊቲ ከማለዳው ጀምሮ የሚደረገው ጉዞ እንደቀጠለ ነው፡፡ በቃሊቲና አካባቢዋ ያለው ሕዝብ ብዛት እንዳይታወቅና ሰልፉ ወደ ዋናው ጎዳና እንዳይወጣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሕዝቡን በመንደሮቹ ውስጥ ቢያሰልፉትም የሕዝቡ ብዛት የቃሊቲ ዋና መንገድ ላይ ከመድረስ አልተገታም፡፡ አሁን ሕዝቡ ዋናው አውራ ጎዳና ላይ ወለል ብሎ ይታያል፡፡ አሁንም ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ ቃሊቲ በመትመም ላይ ነው፡፡

ረጃጅም ሰልፎች በቃሊቲ
5፡42
የዚያራ ሰዓቱ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የቀሩት ቢሆንም ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መግባት የቻለው ሕዝብ ከሄደውና ወረፋ ከያዘው ሕዝብ አንጻር እጅግ በጣም ጥቂት ነው፡፡ የዚያራ ሰዓቱ ሲጠናቀቅ መሪዎቻችንን የማየት እድሉን ባናገኝ እንኳ አላህ ኒያችንን እንዲቀበለን ዱዓ በማድረግና በድል አድራጊነት ስሜት ወደየመጣንበት እንመለሳለን፤ ኢንሻአላህ፡፡

ሕዝቡ ወደ ቃሊቲ ውስጥ የመግባት እድል እንደሌለው እያወቀም በትዕግስት ቆሟል፡፡
ከረፋዱ 5:02
አዲስ አበባ ለሚኖሩና ዛሬ ቃሊቲ ለዚያራ ለሄዱ ሙስሊሞች የመልካም ምኞት መግለጫዎች እየመጡ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች መልእክታቸውን ያደረሱ ሙስሊሞች ‹‹መሪዎቻችንን የመዘየር እድል ባናገኝም በሐሳብ ግን ከእናንተ ጋር ነን›› የሚል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእሲያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ተመሳሳይ መልእክት ያዘለ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ልከዋል፡፡ የሁሉም መልእክቶች ጭብጥ በዚህ ታሪካዊ ትእይንተ ዚያራ የተገኙ ሙሊሞችን ታሪካዊ እድለኝነት ይመሰክራሉ፡፡

ቃሊቲ ወህኒ ቤት ለዚያራ ለመግባት የሚጠባበቁ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በፍጽም እርጋታ ወረፋቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ሰልፈኛ እርስ በእርስ በመተዛዘንና ያለውን ምግብና መጠጥ እየተካፈለ ፍቅሩንም ጭምር በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡
ወደ ቃሊቲ ውስጥ መገባት ተጀምሯል፡፡ በተለመደው እርጋታችን ወደ መሪዎቻችን እንግባ፡፡
ወደ ጊቢ ከመገባቱ በፊትም ሆነ በኋላ ምንም ዓይነት መገፋፋት እና መሯሯጥ እንዳይኖር ጥንቃቄ እናድርግ፡፡
አሁን ከማለዳው 2፡45
እስከ አሁን ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር የለም፡፡ መንገዱ ሁሉ ሰላም ነው፡፡ ጉዞ ያልጀመርን በተጠቀሱት የትራንስፖርት መስመሮች በመጠቀም ጉዞ እንጀምር፡፡
እስከ አሁን ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር የለም፡፡ መንገዱ ሁሉ ሰላም ነው፡፡ ጉዞ ያልጀመርን በተጠቀሱት የትራንስፖርት መስመሮች በመጠቀም ጉዞ እንጀምር፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ማረሚያ ቤቱ አስከ አሁን አልተከፈተም፡፡ ሕዝቡ በተለመደው ታጋሽነት የማረሚያ ቤቱን መከፈት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው፡፡
ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለምንመጣ ሁሉ የትራንስፖርት አጠቃቀም
1. ከመርካቶና አካባቢዋ የምንመጣ ከአውቶቢስ ተራ ቃሊቲ ድረስ አዲስ ከተማ ት/
ቤት ፊት ለፊት ታክሲና ሎንችን እናገኛለን::
ይህንን ካጣን እስከ ሳሪስ ታክሲ በመያዝ ከሳሪስ ቃሊቲ መሳፈር እንችላለን::
እንደ አማራጭ መርካቶ ውስጥ ሲኒማራስ ጀርባ ቃሊቲ ድረስ ታክሲ ያለ ሲሆን ካሳጠሩት ሳሪስ ድረስ መሳፈር፤ ሌላው አማራጭ የከተማ አውቶቢስ ከመርካቶ ቃሊቲ 4
ቁጥርን መጠቀም እንችላለን፡፡ እሷን ካጣንና አማራጭ
29 ን አስከ ሳሪስ መጠቀም እንችላለን
2. ከአየር ጤና ዓለም ባንክ ካራቆሬና አካባቢዋ የምንመጣ ከአየርጤና አደባባይ ወደቆሼ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ሳሪስ አቦ ድረስ ሎንቺን በብዛት አለ፡፡ ማሰልጠኛ በመውረድ በእግር ቅርብ ሲሆን አማራጭ ታክሲም እናገኛለን ቆሞ ከመጠበቅ
እየሄዱ መጠበቅ ይመከራል አየርጤና አደባባይ ተሻግሮ በቄራ በኩል እስከ ሳሪስ የሎንችን መስመር እናገኛለን፡፡ከሳሪስ ቃሊቲ ታክሲ፣ ሃይገር እና ሎንችን መጠቀም እንችላለን፡፡ እንደ አማራጭ ከአየር ጤና በቆሼ በኩል 86 ቁጥር ባስ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ድረስ
መጠቀም እንችላለን
3. ከፒያሳና አካባቢው የምንመጣ ሰዎች እስከ ሳሪስ ታክሲ፣ ሀይገር ወይም 14
ቁጥር ባስን መጠቀም እንችላለን፤ ከዚያ ከሳሪስ ቃሊቲ፡፡
4 ከአራት ኪሎና አካባቢው የምንመጣ ወደ ለገሃር በመምጣት የተሻለ
የትራንስፖርት አማራጭ አለ እስከ፡፡ ሳሪስ ካራዘሙት ቃሊቲ ድረስ ታክሲ እስታድየም
ጋር ለገሃር ውስጥ ሃይገር ቃሊቲ ድረስ በሽ ነው፡፡ እንደ አማራጭ 27 እና 25 ቁጥር
ባሶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ ከተገኘ 56 ቁጥር ባስ እስከ ሳሪስ ወይም 25 ቁጥር ልዩ 110 ቁጥርም እስከ ቃሊቲ መጠቀም እንችላለን::
5. ከመገናኛና አካባቢዋ የምንመጣ ከውስጥ መገናኛ ሃይገር ሳሪስ አቦ ድረስ
በብዛት ያለ ሲሆን፤ ስንወርድ ዘንባባ ብለን በመውረድ ሳሪስ በዘንባባ ሆስፒታል
በማቋረጥ ከሳሪስ እንሳፈራለን፡፡ ሳሪስ አቦ ከሳሪስ እየሞላ ስለሚመጣ የታክሲ
እጥረት አለ፡፡
6.ከውስጥ መገናኛ 76 ቁጥር ባስ ቃሊቲ ድረስ ትሄዳለች፡፡ ከመገናኛ ቦሌ፣ ከቦሌ ሳሪስ ታክሲ ቦሌ ድልድይ ስር እናገኛለን፡፡
የተሰጡትን የመርሐ ግብሩ ማሳሰቢያዎች በአግባቡ ለመፈጸም ሁላችንም እንጣር፡፡ የዚያራ መርሐግብሩ የቀጥታ ዘገባ (live blog) አሁን ተጀሯል፡፡
ከሱብሂ ሶላት ጀምሮ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚተምመው ሕዝብ ብዛት ለማመን የሚቸግር ሆኗል፡፡ ከማለዳው 12፡30 የቃሊቲ ዋናው አውራ ጎዳና ደርሷል፡፡
No comments:
Post a Comment