በደቡብ ወሎ ሙስሊም መሆን ወንጀል ሆኗል!
መንግስት ምን እየሰራ ነው?
የኢህአዴግ መንግስት ‹‹አክራሪነትን ለመግታት›› በሚል የሀሰት ምክንያት የአህባሽን አንጃ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ለመጫን ሙከራ ማድረግ ከጀመረበት ካለፈው አመት ጀምሮ ታላቅ ብሄራዊ ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወቃል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ዲኔን አላስነካም›› በሚል ስሜት የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከት ባደረገው እጅግ ሰላማዊ ትግልም በርካታ ድሎችን ሲጎናጸፍ ቆይቷል፤ መንግስትም በበኩሉ ሰላማዊውን ትግል ለማስቆም በወሰዳቸው ኢሰብአዊ እርምጃዎች ህዝበ ሙስሊሙ ይህ ነው የማይባል መስዋእትነትን ለመክፈል እንደተገደደው ሁሉ!
በዚሁ ታሪካዊ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ የተቆርቋሪነት ስሜት የመንግስትን ውስብስብ ሴራ መና ሲያስቀሩ ከነበሩ ጠንካራ ክልላዊ ተቃውሞዎች አንዱ በወሎ ክልል የነበረው ተጠቃሽ ነው፡፡ በተለይ በደቡብ ወሎ ክልል በሰደቃና በአንድነት ፕሮግራሞች የተደረገው ህዝባዊ ንቅናቄ እና የመጅሊሱን ምርጫ መና ያስቀረው የህዝብ አንድነት ያበሳጨው መንግስት የጭካኔ እርምጃዎችን ጭምር በመውሰድ ለማስቆም ጥረት አድርጓል፡፡ የደቡብ ወሎ እምብርት በሆነችው በደሴ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው የፈደራል ፖሊሶች ጥቃት ሳይሽር የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ባሉ ከተሞች ላይ የሚፈጽሙትን ህገ ወጥ ጥቃት ቀጥለዋል፡፡ ይህ የመንግስት ህገ ወጥ አካሄድ ከሞላ ጎደል ምን ይመስል እንደነበር በመጠኑ ለማየት እንሞክር፡፡ ገርባ
ህዝበ ሙስሊሙ ላይ በጅምላ ወንጀል እየፈጸመ ያለው የኢህአዴግ መንግስት በደቡብ ወሎ ክልል ሲፈጽም የቆየው በደል እና ግፍ አሁንም አልበረደም፡፡ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ህገ ወጥ እስራት በመፈጸምና ሙስሊሙን ህብረተሰብ ባደራጃቸው የራሱ ሰዎች በመተንኮስ በፈጠረው ግርግር የክልሉን ህብረተሰብ ህይወት የማመሰቃቀል ተግባሩን አፋፍሞ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ ግርግር የአምስት ግለሰቦች ህይወት የጠፋ መሆኑ እና ከነዚህ መካከል ሁለቱ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በርሸና የተገደሉ መሆኑ በአይን ምስክሮች መረጋገጡ ብዙዎችን ያደነገጠ ነበር፡፡ በየትኛውም አገር ተሰምቶ በማያውቅ ሁኔታ ቆስለው ሆስፒታል የገቡ ሙስሊሞችን ህክምና የመከልከል እና የማሰቃየት ተግባር መፈጸሙ ደግሞ የውዲቷን አገራችንን ስም በእጅጉ የሚያጎድፍ ክስተት ነው፡፡
ከዚህ አሳዛኝ ክስተት በኋላም ቢሆን የከተማይቱ ሙስሊሞች ሰላም አላገኙም፡፡ ‹‹መሳሪያ ፍተሻ›› በሚል ሰበብ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የግለሰቦች ቤት ሲፈተሸ ቆይቷል፡፡ ተፈትሾ መሳሪያ ያልተገኘበት ደግሞ ነጻ በመሆን ፋንታ ‹‹መሳሪያ ውለድ›› እየተባለ አሰቃቂ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ በየምሽቱ ታፍነው የሚወሰዱ ሰዎች ቁጥር የትየለሌ ሲሆን ከተወሰዱት ውስጥ ሁለቱ እስካሁን ያሉበት ቦታ እንኳን አልታወቀም፡፡ የከተማይቱ ዋልታና ማገር የሆኑት ወጣቶች ከመንግስታዊው ሽብር ለመዳን በአቅራቢያ ወደሚገኙ ጫካዎች እና አጎራባች ከተሞች ተሰደዋል፤ አሁንም እየተሰደዱ ይገኛሉ፡፡
ደጋን
የደጋን ከተማ ሌላዋ ተረኛ ገፈት ቀማሽ ነበረች፡፡ ወጣት ሙስሊሞች እንደአውሬ እየታደኑ ታፍነው ተወስደዋል፡፡ የመስጊድ ኢማሞች ከቦታቸው ተነስተው በአህባሾች መተካታቸውም በራሱ ሌላው የደጋን ከተማ ቀውስ ነበር፡፡ ኹጥባ እንኳን ማድረግ የተሳናቸው የአህባሽ ‹‹ኢማሞች›› ህዝበ ሙስሊሙ ያለኹጥባ እንዲሰግድ አስገድደውታል፡፡
ኮምቦልቻ
ኮምቦልቻ ከተማ ላይ ከሌሎቹ ከተሞች አንጻር የተወሰደው እርምጃ ከሞላ ጎደል አናሳ ቢሆንም የመባባስ እድሉ ግን ከፍተኛ እንደሆነ የሚጠቁሙ ክሰተቶች መታየት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ‹‹የሚያሰግዳችሁን ኢማም እኔ ካልመረጥኩላችሁ!›› እስከማለት እየደረሰ ያለው የኢህአዴግ መንግስትና ህገ መንግስቱን ሙሉ በሙሉ የረሱ አንዳንድ ባለስልጣናት ከኮሞቦልቻ የመስጊድ ኢማሞች ሁለቱን በአህባሽ ኢማም ለመቀየር መወሰናቸውን በስብሰባ አሳውቀዋል፡፡ ከአህባሽ ደጋፊዎች ጋር ‹‹ውይይት›› ሲደረግም ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ በሌሎች አጎራባች ከተሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ለመድገም የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ሀርቡ
በመልክአ ምድራዊ አቀማመጧ ከኮምቦልቻ ጋር የምትዋሰነው ሀርቡ ከተማ ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ ቀጣናዎች ዋነኛዋ ሆናለች፡፡ አራት የመስጊድ ኢማሞች የአህባሽን አስተምህሮ ሊያስፈጽሙ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከስራቸው የታገዱ ሲሆን የተተኩትም በአህባሽ ኢማሞች ነው፡፡ ሰላማዊነትን የተጎናጸፉት የሀርቡ ሙስሊሞች ግን በእነዚህ ‹‹መንግስት ሰራሽ›› ኢማሞች ለመስገድ ባለመፈለጋቸው ‹‹በግድ አህባሾቹን ተከትላችሁ ስገዱ›› እየተባሉ ጫና ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡ የሶላት ሰአት ሲደርስ መስጊዶች በታጣቂ ይከበባሉ፤ ኢማሞች በመሳሪያ ይታጀባሉ፤ ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹በግድ አህባሾቹን ተከትለህ መስገድ አለብህ›› እየተባለ በጸጥታ ሀይሎች ይገደዳል፤ ይባስ ብሎም በማይሰግዱ ሰዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እስከመጣል ተደርሷል፡፡ ህዳር 6 ቀን እየሰገዱ የነበሩ ሙስሊሞች ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪ መተንፈሻ የለውም፡፡ ከቤት መውጣት እና መግባት፣ ገበያ ቦታ መገኘት ለአፈና እና ለድብደባ የሚያጋልጥ ተግባር ከሆነ ቆይቷል፡፡ ታፍሰው የተወሰዱ ወጣቶች፣ ህጻናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ሳይቀሩ በየፖሊስ ጣቢያው ቶርቸር ተደርገዋል፡፡ ህግ ማስጠበቂያ በሆኑ ጣቢያዎች ውስጥ በሙስሊም ግለሰቦች ላይ መሳሪያ እየተደገነ የማስፈራራት እና የማሸማቀቅ ተግባር ይፈጸማል፡፡ በተለይ ደግሞ በሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ እየተፈጸመ ያለው በደል አገሪቱ ውስጥ መንግስት ጨርሶ የሌለና በወንበዴዎች የምንተዳደር አስመስሎታል፡፡
ለከተማይቱ እንቅስቃሴ ካስማ የሆኑት ወጣት ሙስሊሞች መንግስታዊውን ሽብር ለማምለጥ ቤታቸው ማደር ካቆሙ ቆይተዋል፡፡ በርካቶች በየጉራንጉሩ መበታተናቸው ያልጣመው የክልሉ ባለስልጣናት ስብስብ ደግሞ በፊናው ‹‹ወጣቶቹ በእርቅ ይመለሱ›› በሚል ነዋሪውን በግድ ስብሰባ እየጠራ እና ረግጠው እንዳይወጡ በጸጥታ ሀይሎች እያስጠበቀ ይገኛል፡፡ ዘንድሮ ነዋሪዎች ስብሰባ የሚጠሩት አስፈሪ መሳሪያ የታጠቁ ሰው በላ ‹‹የጸጥታ›› ሀይሎች በር እያንኳኩ መጥተው በመሆኑ ብዙዎች ‹‹እዚህ አገር ላይ ምን እየተሰራ ነው?›› ሲሉ እንዲጠቅቁ ተገድደዋል፡፡ በመንግስት ላይ አንዳችም እምነት ያጣው ህዝብ ይህ ሁሉ ሲሆን ተቃውሞውን በዝምታ ከመግለጽ እና እየተሰራ ያለውን ታሪካዊ ስህተት ከመታዘብ ውጭ አንዳችም ስንዝር ፈቀቅ አላለም፡፡
ከሚሴ
እጅግ ጠንካራ እና ተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲደረግባት የቆየችው የከሚሴ ከተማም በበኩሏ በርካታ ችግሮችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ከታላቁ የኢድ እና አረፋ የተቃውሞ ትእይንተ ህዝብ በኋላ በክልሉ ከደሴ ወደታችኛዎቹ ከተሞች እየተዛመተ ያለው እርምጃ እነሱንም እንደማይስታቸው የተገነዘቡት የከተማዋ ሙስሊሞች ከተማዋ በታጣቂዎች በመከበቧ ለቅቀው በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡ ያሉትም ሙስሊሞች በየቀኑ መንገድ ላይ እንኳ ሳይቀር ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ መስጊድ ውስጥ የተሰቀሉ ባነሮችን ለማውረድ ፖሊሶች መሳጂዶቹን በማራከስ ከነጫማቸው እየገቡ አውርደዋል፡፡ ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ‹‹በደህንነቶች›› ግላዊ ፍላጎት እየተካሄዱ ያሉት የቤት ለቤት ፍተሻዎች ተጠናክረው ሺዎችን እያስለቀሱ ነው፡፡ ፍተሻው የሚፈልጉትን ሳያስገኝላቸው ሲቀርም ትተው በመሄድ ፋንታ የከፋ ድብደባ በመፈጸምና ቤት ውስጥ የተቀመጡ ወርቅን የመሳሰሉ ውድ ንብረቶችን በመዝረፍ ላይ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ የሚፈጽመው ደግሞ የክልሉ የፌደራል፣ የመደበኛ ፖሊስና የልዩ ኃይሎች ጥምረት መሆኑ ከምንም በላይ መንግስት በጉልበት ብቻ የሚያምን መሆኑን ለሕዝቡ እያሳየበት ነው፡፡
በጥቅሉ ሲታይ ባለፈው አመት በአሳሳ ሙስሊሞች ላይ የግድያ እና የርሸና እርምጃ በመውሰድ የሃይል እርምጃውን የጀመረው መንግስት ባሳለፍነው ረመዳን መግቢያ የአወሊያውን የሰደቃ ፕሮግራም በማደናቀፍ ጭልጥ ወዳለ የአፈና እና የጅምላ እስር፣ እንዲሁም የግድያ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ጠንካራ እንቅስቃሴ የተስተዋለባቸው የገርባ፣ የደጋን፣ የኮምቦልቻ፣ የሀርቡና ከሚሴ ከተሞች ደግሞ ዋነኛ ኢላማዎቹ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ደቡብ ወሎ ላይ ሙስሊም መሆን ወንጀል የሆነ እስኪመስል ድረስ እየተፈጸመ ያለው በደል የከተሞቹን ወጣቶች እና ጎልማሶች ወደጫካና ስደት ኑሮ እየመራቸው ነው፡፡ በአካባቢው ኗሪ የሆኑ ሙስሊሞች ሱዳንና ጅቡቲን ወደመሳሰሉ ጎረቤት አገራት አየተሰደዱም ይገኛሉ፡፡ በከተሞቹ የቀሩትን ሙስሊሞች ያለገደብ እንዳሻቸው የሚያሰቃዩት፣ የሚደበድቡትና የሚዘርፉት የመንግስት የሽብር ሀይሎች ደግሞ መስጊድ ገብተው ኢማሞችን በመመደብ እና በአፈሙዝ ሃይል በሚፈልጉት ኢማም እስከማስሰገድ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ግለሰቦችን በመዝረፍ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው የተነሳውን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝና ለማቆም፣ ሙስሊም ወጣቶችንም ሙሉ በሙሉ ከዲን ለማራቅ መሆኑ እርግጥ ነው፤ ሊሳካ የሚችል ባይሆንም፡፡ ሃይማኖታዊ ጭቆና መንፈሳዊነትን የሚጨምር እና ትግልንም የሚያፋፍም እንጂ ሰዎችን ከሃይማኖት የሚያርቅ ላለመሆኑ ታሪክ ራሱ በቂ ምስክር ነው፡፡ በእነዚህ የደቡብ ወሎ ከተማዎችም ቢሆን ህዝበ ሙስሊሙ ትግሉን ለመቀጠል ተጨማሪ ምክንያቶችን ከማግኘቱ በስተቀር የቀነሰ ነገር የለም፡፡ በትግል መሃል በደል በበዛ ቁጥር የትግሉን ወኔ እና ቁርጠኝነት የበለጠ እንደሚያጋግለው የሚያውቀው ህዝበ ሙስሊም አሁንም በትእግስት ተቃውሞውን ቀጥሏል፡፡
ይህ ሁሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ በአገቱ ያሉ ‹‹ለሰብአዊ መብት እንታገላለን›› የሚሉ ተቋማት በዝምታ ተለጉመዋል፡፡ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ እንዲሁም የእምባ ጠባቂ ተቋም የት ነው ያሉት? ይህን በአደባባይ እየተፈጸመ ያለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመቃወምኮ ሙስሊም መሆን አያስፈልግም! ዜጎች በአደባባይ እየተደበደቡ እና እየተገደሉ፣ የማይፈልጉትን እምነት በግድ እንዲከተሉ እየተጠየቁ አይቶ ለመቃወም አንዳችም መስፈርት አይጠይቅም! የየትኛውም ሐይማኖት ተከታይ፣ የየትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ አራማጅ ሊቃወመው የሚገባው ድርጊት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ በዝምታ መዋጥ ከታሪክም ከትውልድም ተወቃሽነት አያድንም!
የተፈጸሙት ጥቃቶች የመንግስት ሀሳብ ከደሴ ጀምሮ በሚገኙ ከተሞች የአፈና እርምጃውን አፋፍሞ በመቀጠል ወደ መሀል አገር አዲስ አበባ ለመምጣት መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ግን በፍጹም የሚሳካ አይደለም፤ አላህ ከጎናችን አለና! በሃይማኖታችን ምክንያት የሚፈጸምብንን የመብት ጥሰት ለማስቆም የምናደርገው ትግል በህገ ወጥ የሃይል እርምጃ አይቀለበስም፡፡ ትግላችን በተባበረ ክንድ ድል ይነሳል፤ ኢንሻአላህ!
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment