Thursday, November 22, 2012

የዛሬው ይፍርድ ቤት ውሎ የእኔ እይታ

የዛሬው ይፍርድ ቤት ውሎ የእኔ እይታ
ፍርድ ቤት የደረስኩት ከጧቱ አራት ሰዓት ላይ ነበር እኔ ስደርስ ፖሊስ ሙስሊሙን በሁለት ቦታዎች ከፍሎ ነበር (ፍርድ ቤቱ ውስጥ በረካታ ሙስሊም እነደነበረ የተጠበቀ ሆኖ) ከፍርድቤቱ በላይ በኩል ወደ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ እንዲሁም በሌላው አቅጣጫ ወደ ህንፃ ኩሌጁ ….በሁለቱም ሙስሊም ስብስቦች መሃከል ፍርድቤቱ (ፍርድ ቤት ውስጥ በርካታ ሙስሊሞች እንደነበሩ ለመመልከት ችያለሁኝ) እንዲሁም በርካታ ፖሊሶች ይገኛሉ በፍርድቤቱ አከባቢ የሚገኙ ካፌና ሱቆች ግማሹን ሲያዘጉ እንዲሁም ክፍት የሆኑትን በር ላይ በመቆም ሙስሊም የሚመስለው እንዳይገባ ሲከለክሉ ተመልክቻለሁኝ፣ እኔም ሁለተኛውን ስብስብ ተቀላቀልኩኝ፣ ጥቂትም ሳልቆይ ህዝበ ሙስሊሙን ሲገፉ እና ሲያባርሩ የነበሩ ህግ አስከባሪ ተብይዎች ነገር ግን ህጉን በአግባቡ ያማያውቁት ፖሊሶች ተሰባስበን ካለንበት ቦታ አሁንም ወደ ኃላ እንድናፈገፍግ ጫና መፍጠራቸውን አላቆሙም ህዝበ ሙስሊሙ ግን በተረጋጋ ሁኔታ ከፖሊሶች ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል.. ለምንድን ነው ቦታችንን ትተን እንድንሄድ የምታደርጉን የሚል ጥያቄውን እያቀረበ ቢሆንም ፖሊሶቹ ሊሰሙ አልፈለጉም በዚህ ግዜ ሙስሊሙ አሁንም በተረጋጋ ሁኔታ መንገድ ዘጋቹ ካላችሁን ይሄው መንገድ እንክፈት ከዚህ ውጭ ግን አንበተንም የመጣነው የኮሚቴዎቻችንን የፍርድ ሂደት ለመከታተል ነው ስለዚህ እዝህ ቆመን እንጠብቃለን በማለት መልስ ሰጠ፣ ሆኖም አሁንም ግን ፖሊሶች እንደውም ቆጣ ባለ መልኩ በቃ እናንተ አታስፈልጉም ይሄን ቦታ ለቃችሁ ተበተኑ ስብስባችሁን አንፈልግም በማለት በዱላ ለመማታት ይቃጣቸው ገባ በዚህ ወቅት አንዲት እህታችን እንባዋን እየዘረገፈች የሚከተለውን ንግግር ተናገረች “ለምንድን ነው እንደዚህ የምታመናጭቁን እኛ ኢትዮፕያዊ አይደለንም? ዜጋ አይደለንም? ብላ አምርራ አለቀሰች ይህን ግዜ የተወሰኑ ፖሊሶች ደንገጥ አሉ እና ውጥረቱን ረገብ አደረጉት ሆኖም ከፖሊሶች መሃከል አንድ ወጣት እና ቀጠን ያለ ቆጣ በተሞላበት ንግግር ተበተኑ ብሎ ለማስፈራራት ሙከራ አድርጓል ይህ ፖሊስ በጣም በሚገርም ሁኔታ ረመዳን 2 ላይ በአንዋር መስጂድ ላይ ፖሊስ ጥቃት በፈፀመ ግዜ ግንባር ቀደም በመሆን ሙስሊሙን በዱላ ሲቀጠቅጥ የነበረ ከመሆኑ በላይ በወቅቱ እኔም በጥላቻ የተሞላውን ዱላውን ቀምሻለሁኝ አላህ ያዋርደውና የተረገመ ሰው ነው ሆኖም ቁጭቴን በውስጤ ዋጥ አደረኩኝ፣ በዚህ ሁኔታ ባለንበት ወቅት ፖሊሶች ላይ መሰላቸት የተፈጠረ መሰለኝ ካስቆሙን ቦታ እንዳናልፍ ከፊት ለፊታችን ሆነው መከላከሉን ብቻ ማከናወን ያዙ እንዲሁም ከጦርሃይሎች አከባቢ የሚመጡ መኪኖች ወደፍርድ ቤቱ መንገድ እንዳይጠቀሙ ከለከሉ ሆኖም ግን ከላይ ከሜክሲኩ የሚመጡ መኪኖች ግን ያልፉ ነበር ብዙዎች ግራ በመጋባት በመስኮት ሲመለከቱ አስተውያለሁኝ፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፍርድቤቱ በር አከባቢ አንድ አውቶቢስ በሩ ተከፍቶ ሰዎች ሲገቡ ተመለከትን ግማሹ በአውቶቢሱ እየገቡ ያሉት ኩሜቴዎቻችን ሳይሆኑ አይቀርም የሚል ግምት ሳይወሰድ አልቀርም ፣ሁሉም በርቀት ለመመልከት መንጠራራት ጀመረ ይህ ሁኔታም ሁሉም በአንድነት አውቶቢሱን መመልከቱን ተያያዘ መኪናው ከእኛ ትንሽ ራቅ ያለ መሆኑና መኪናው ወደ ፍርድ ቤቱ በር የተጠጋ በመሆኑ የሚገቡትን ሰዎች መለየት አልተቻለም ሆኖም ግን በዚህ ወቅት ሁሉም ኮሚቴዎቻችን ናቸው በሚል እጅን ማውለብለቡን ተያይዞታል ቀስ በቀስ ሰው ስሜት ውስጥ ገባ በድንገት ሳይታወቅ ፌት ለፊት የነበሩትን ፖሊሶች በማለፍ ወደ ፊት መጠጋጋት ጀመረ ሁሉም ስሜት ውስጥ ገባ ግማሹ ያለቅሳል የተወሰነው ተክቢራ እያለ ነው ሌላው ያጨበጭባል በቃ ለጥቂት ደቂቃ ቢሆንም ድብልቅልቁ ወጣ ዋናው መንገድ ሙሉለሙሉ በሙስሊሙ ተዘጋ፣ አውቶቢሱም ነጎደ ከዛ ሰው መረጋጋት ጀመረ ፖሊሶቹ የህዝቡ ስሜት ሲመለከቱ ግራ ተጋብተው ታይተዋል በሂደት ግን ሰው ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር ሌላ ወሬ መወራት ጀመረ አሁን ያለፈው ባስ ኮሜቴዎቻችን የያዘው አይደለም የሚል ህዝቡም ተናደደ ሆኖም በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ፌድራል ፖሊሶች ከላይ እየሮጡ መጡ የተወሰኑ ወንድሞችና እህቶችንም በዱላ መማታት ተያይዙት ይህ ሁኔታ ደግሞ የበለጠ ውጥረት ፈጠረ፣ ሆኖም የሰላም አምባሳደር የሆነው ሙስሊሙ ጥረት ነገሮች መረጋጋት ጀመሩ ሆኖም ግን ሁልግዜ ሁከት የሚፈልጉ ሰላም አደፍራሽ የሆኑት ደህነት ተብዪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም መርዛቸውን መርጨት ጀመሩ በሙስሊሙ መሃል ገብተው ግርግር ፈጠሩ ከዛም አልፈው ደደብ የሆኑት ደህንነት ተብዪዎች በማዘናጋት የተወሰኑ ሙስሊሞቹን ጠልፎ ለመውሰድ ሙከራ አደረጉ በዚህ ግዜ ሙስሊሙ ነቅቶባቸው ሊጠለፉ የነበሩትን ሙስሊሞች ማስጣል ተቻለ ሆኖም ግን ደህንነቱ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ ምክያት ትንሽ ግርግር ተፈጠረ ድህነነቱም ሙስሊሙ ስሜት ውስጥ በመግባቱ ትንሽ ኩርኩም ቀመሰ ተደናግጦም በሩጫ ወደ ጓደኞቹ ተቀላቀለ ከዛም ጉዳት እንደደረሰበት በማስመሰል በደህንነት እና በፖሊሶች ታጅቦ ወደ ሙስሊሙ በመምጣት ለማስፈራራትና ለማስረበሽ ሙከራ ቢያደርጉም ሙስሊሙ በተረጋጋ መንፈስ ሁኔታውን አሳልፎታል ከዛ በመቀጠል የተወሰነ ቆይታ የተደረገ ሲሆን ኩሚቴዎች ሳይሄዱ አይቀርም የሚል መላ ምት በማመዘኑ 6፡25 አከባቢ ሙስሊሙ የተወሰነው ወደ ጦርሃይሎች አቅጣጫ ሴሄድ አብዛኛው ግን በጀመዓ ወደ ኮካ መስጅድ ሄዷል እሰከ 6፡35 ድረስ ግን ከጦርሃይሎች አቅጣጫ የሚመጣው የመኪና መንገድ ዝግ ነበር፣ ወደ 6፡40 አከባቢ ሁኔታውን በጥንቃቄ ስቃኝ ነበረ ሲሆን የተወሰኑ ወንድሞች ፍርድ ቤቱ አከባቢ በፖሊስ መኪና ተጭነው እንደነበር ለመመልከት ችያለሁኝ ሆኑም የመጨራሻውን ክስተት ለመመልከት አልታደልኩም፡፡ በመጨረሻም በዛሬው በነበረው ህዝበ ሙስሊም በጣም ኮርቻለሁኝ ወላሂ ለአላህ ብለን ለኩሚቴዎቻችን ያለንን ታማኝነት ነው ያሳየነው ወያኔ ግራ እንደገባው ተመልክቻለሁኝ፣ ለዚህም ነው ለሌላ ግዜ ተበሳጭተንና ተስፋ ቆርጠን እንድንቀር በማሰብ ይመስላል ሲያዋክቡን የነበረው በመሆኑም በቀጣይ በሚኖረው የፍርድ ሂደት ላይ የአሚሮቻችን ትእዛዝ በመጠበቅ መገኘት ይኖርብናል ሌላው አንዳንድ ወንድሞች ትንሽ ስሜት ውስጥ የመግባት ነገር ነበር እና ሰብር ይኑረን የወያኔ አላማ ሁከት መፍጠር ነው ብልጥ እንሁን ሌላው በአካል ባለውቃትም እንባዋን እየዘራች ለፖሊሶቹ ልክልካቸውን የነገርሽ እህቴ ጀዛኪላህ እኔ ያዩሁት ይህ ነበር እናንተ ይምትጨምሩትን እስቲ አካፍሉን 

ወንድማችሁ አማን

No comments:

Post a Comment