አባይና የኢትዩጲያ ሙስሊም
(በኢትዮ-አልሀበሺ)
መቼም የአባ ጉዳይ የኢትዩጲያና የተፋሰሱ ሀገራት የልብ ትርታ መሆን ከጀመረ ዘመናት አልፈዋል፡፡ የአባይ ግድብ ጉዳይ ደግሞ ትርታውን በይዘትም በፍጥነትም አሙቆታል፡፡ የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉ የዘርፉ ምሁራን ሠላማዊ የመሠለው የአባይ ግድብ ግንባታ ሂደት እንደሚታሠበው አልያም እንዲታሠብ እንደተፈለገው ፍፁም ሠላማዊ እንዳልሆነ መግለፅ ጀምረዋል፡፡ ከባቢውም ከአደጋ አልፀዳም፤ እንደውም የቁርሾ እና በጎሪጥ የመተያየት ጉም ማንዣበብ ስለመጀመሩ አንዳንድ ምልክቶች እየተስተዋሉ እንደሆነ አሁን አሁን መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዩጲያን ፖለቲካና ወቅታዊ የሙስሊሞችን ጉዳይ ካሠብነው በላይ ሠፋ ባለ መልኩ የቃኘው የቀድሞ የኢህአዴግ አባል አብደላህ አደም ተኪ ዝርዝር ፅሁፍም በተወሠነ መልኩ ከመጋረጃው ጀርባ ያሉ ድብቅ ተልዕኮዎችን ዳሷል፡፡ የመለስ ኢትዩጲያ (እዚህ ላይ እኛ በሀገርነቷ የምንኮራባት፤ እትብታችንን የቀበርንባት እና ልንዋደቅላት ተፈጥሮአዊ ቃልኪዳን የገባንላት ውዷ ኢትዩጲያችን ሳትሆን፡ የእግር እሳት ሆና ዕምነታችሁን ቀይሩ እስከማለት የዘመተችብንን ኢትዩጲያ ለመግባባት ያክል “የመለስ ኢትዩጲያ” ለማለት መርጫለሁ፡፡) አህባሽን ለማጥመቅ ስትሠናዳ እና በህዝብ የተተፋውን የኤልያስ REDMAN መጅሊስ ለህዝብ ያሠቡ በማስመሠል እጅግ በተጠና መልኩ ማንነታቸው የማይታወቅ፤ ሲያዩአቸው ግን እስላማዊ ቁመና ያላቸው የሚመስሉ አህባሽ አመራሮችን ከያሉበት ለቅመው በሲስተም ሲያሰርጉ፡ ቀጣይ ጥንስሶችንም በአህመዲን አብዱላሂ ያልበሠለ ካቢኔ እንጭጭ አዕምሮ ሊታሰብ ከሚችለው በላይ በተጠና አኳኋን አላህ እስካጋለጠው ድረስ ውስጥ ውስጡን ማስፈፀም የጀመሩበት አካሄድ እንደሚታሠበው ከአንድ እና ሁለት ሠው ውሳኔ የዘለለ ውስብስብ የፖለቲካ ሴራ ነበር፡፡
ፅሁፌን ስጀምር እንደርዕሱ ስለአባይ ያነሳሁትም ያለነገር አይደለም፡፡ ዝርዝሩን ለጊዜው ወደጎን ትተን በግርድፉ ስናየው የአባይ ግድብ ጉዳይ ዕውን መሆን የሚያስደስተን ወገኖች እንዳለን ሁሉ የሚያስኮርፋቸውም እንዳሉ ግልፅ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ጥቅሜን ያሳጣኛል ብለው ከሚያምኑ ወገኖች መሃል ደግሞ፡ ግብፅ ግንባር ቀደሟ ናት፡፡ የግብፅን ፖለቲካ ጫና ውስጥ ማሳደር ከምንም በላይ የህልውና ጉዳይ ከሚሆንባቸው ወገኖች ዋነኛዋ ደግሞ እስራኤል ናት፡፡ የግብፅን ሳንባ በእጅ አዙር በጭብጧ ስር አስገብታ ፍልስጥኤምን እና ህዝቧን በተመለከተ ግብፅ ያላትን ጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥ ተጠቅማ እስራኤልን ለመጫን በሞከረች ቁጥር እስራኤል ደግሞ በኢትዩጲያ በኩል የግብፅን “ሳንባ” (አባይ) ጨመቅ እያረገች የ“አትድረሺብኝ አልድረስብሽ” ጨዋታ ለመጫወት ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዩጲያና እስራኤል አጋርነት ከምንም በላይ ለእስራኤል ይጠቅማል፡፡ በአባይ ግድብ ምክኒያት ታዲያ በኢትዩጲያና በግብፅ መካከል ሊኖር የሚችል ማንኛውም ተቃርኖ ለእስራኤል ግብፅን በኢትዩጲያ በኩል ለመቆጣጠር መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡ የአሁኑ የግብፅ አስተዳደር በኢስላማዊ ወንድማማችነት የሚያምን (ከነስሙ “ኢኽዋን አልሙስሊሚን”) መሆኑ እና በኢትዩጲያ ውስጥ የሙስሊሞች አንድነትን እና የዕምነት ጥራትን(ተውሂድ) ከምንም በላይ ማስቀደምን የሚሠብኩ በዕምነት እና በርዕዩተ አለም ከኢኽዋኖች ጋር እጅግ የሚቀራረቡ ሙስሊሞች መብዛታቸው ለነዚህ ወገኖች ይበልጥ ራስምታት ሆኖባቸዋል፡፡ ስለዚህም ለምን ተፈጠራችሁ? ከማለት፤ እስላማዊ መንግስት ልትመሠርቱ ነው ብንል ለሠሚ ቢያንስ አመክንዩአዊ (ሎጂካል) ይመስላል በሚል አየርን ለመጨበጥ ከመሞከር ያልተለየ ህልም ውስጥ ገብተው ብዙ ዳክረዋል፡፡ ኢትዩጲያ ግብፅን ለመቆንጠጥ መጠቀሚያ እንድትሆን እና የእስራኤል ውጥን እንዲሰምር ግብፅና ኢትዩጲያ እንደህዝብም እንደመንግስትም ሊወዳጁ አይገባም፡፡ ለዚህም ነው የግብፅም ሆነ የፍልስጥኤም ሙስሊም ጉዳይ ጉዳዬ አይደለም፡ የእኔ እስልምና “ሀበሻዊ/ሀገር በቀል” እስልምና ነው የሚል ከአለም የተነጠለ በራሡ ደሴት እየተኩራራ የሚኖር ሙስሊም በኢትዩጲያ እንዲኖር እስራኤልና የመለስ ኢትዩጲያ ሲጠነስሱ የኖሩት፡፡ ነገር ግን ሁኔታዎች በታሠበላቸው እና በተሠመረላቸው መስመር ሳይጓዙ ቀረና አህባሽም ከሸፈ፤ ሙሲሊሙም ባነነ፡፡ በድብቅ የተጠነሠሠውና “የህልውና ጉዳይ” ተደርጎ የተወሠደው የአህባሽ ፕሮጀክትም ሲመነምን እንዲሳካ ካላቸው ቁርጠኝነት የተነሳ በጊዜው በታያቸው መፍትሄ መንግስት በጉዳዩ የሌለበት በመምሰል ኮሚቴዎቻችንን እንደተወካይ “አክብሮ” በማነጋገር፡ ለመደለል እና ለማስፈራራትም በመሞከር የሙስሊሙን “መባነን” በጊዜ ለማክሰም (አባባሉን እንደወረደ ለመዋስም፡ “በእንጭጩ ለመቅጨት”) ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡ ሆኖም ኮሚቴዎቹም አልተበገሩ፤ ሙስሊሙም አልተከፋፈለ፤ አልሀምዱሊላህ፡፡ አህባሽ ብቻውን ዉኃ በላው፡፡ ዳግም ላይታደስ ከገጠር እስከ ከተማ በሁሉም ሙስሊም “ብላክ ሊስት” ውስጥ ሰፈረ፤ ይህም ከእንቅስቃሴው ድሎች እና በኮሚቴዎቻችን መስዋዕትነት ከፈሩት እጅግ ውጤታማ ፍሬዎች ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ይህን ጉድ ከመስማት ጆሮዬ ይደፈን ያለው የመለስ ኢህአዴግም ጉዳዩ ውስጥ ጠልቆ የገባውን ረጅም እጁን ምንም ቢሞክር የሚሸፍን ልብስ አልተገኘም፡፡ ጉዳዩም እንደጠዋት ፀሃይ ለሁሉም ግልፅ ሆነ፡፡ ስለዚህም የቀድሞዎቹ “ተወካዩች” የአቋምም የአካሄድም ለውጥ በፍፁም ሳያሳዩ፡ ድንገት ወደ “አሸባሪነት” ተቀየሩ፡፡
መፍትሄ?
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት በስተመጨረሻ እስራኤልን ተጠቃሚ በሚያደርገው ቀመር የመለስ ኢትዩጲያ የመስመር ዳኛ ሆና ለገዛ ዜሆቿ የእግር እሳት ሆናለች፡፡ ነገር ግን ያልተረዱት ነገር እስልምና የሃገር ክህደትን አይሠብክም፡፡ ምንም እንኳን እኛና የግብፅ ሙስሊሞች ከአንድ እናት ከተወለዱ ልጆች የበለጠ ወንድማማች የሚያደርገንን ዕምነት ብንጋራም ኢስላም ለፍትህ እንድንቆም ከማንም በፊት አስተምሮናል፡፡ የአባይ ግድብ እውን ቢሆን እና የኢትዩጲያ ኢኮኖሚ ቢሻሻል የእያንዳንዱ ኢትዩጲያዊ ሙስሊም ገቢ እና ኑሮ ተሻሻለ ማለት ነው፡፡ ይህም በአንፃሩ ግብፅንም ሆነ ሌሎቹን የተፋሰሱን ሀገራት እንደተባለው እስካልጎዳ ድረስ ፍትህ በኢትዩጲያ ሜዳ ናት፡፡ ስለዚህም እስካሁን ለግድቡ የተገዛ የቦንድ መጠን ቢሠላ እንዲያውም ከሌላው አማኝ ይልቅ የሙስሊሙ አስተዋፅኦ እጅጉን ይልቃል፡፡ ለዚህም ሸህ መሐመድ አልአሙዲን ጨምሮ ሁሉም ኢትዩጲያዊ ሙስሊም ባለሃብቶች ለሀገራቸው ታሪካዊ አስተዋፅኦ አድርገዋል፤ እያደረጉም ነው፡፡ ምክኒያቱም ጉዳዩ የሃይማኖት ሳይሆን የሃገር ጉዳይ ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን አሁን አሁን የኢትዩጲያ ሙስሊም ልብ በመለስ ኢትዩጲያ እጅግ ቆስሏል፡፡ ብሄራዊ ስሜቱም ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡ የእኔ ስጋት አሁን የአባይ ጉዳይ ግብፅን ስለማሳሰቡ እና የከፉ ነገሮች ሊከተሉ እንደማይችሉ ማንም በእርግጠኝነት መናገር የማይችልበት ሁኔታ እየተከሠተ ከመሆኑ አንፃር አይበለውና የተፈራው ቢደርስና ግብፅ ጡንቻዋን ብታሳርፍ የገዛ ሀገሩን ህዝብ አስኮርፎ የኢትዩጲያ መንግስት መመከት ይችል ይሆን? ፍጥጫው ካኮረፈው ከፊል የሀገሪቱ ህዝብ ጋር በዕምነት አንድ ከሆነ ህዝብ ጋር መሆኑንስ መንግስት አስተውሎት ይሆን? ብልህ እና እንደሚሰበከው “ባለራዕይ” መሪ ያላት ሃገር ከሆነችስ ሁኔታውን ቆም ብሎ መመርመር አያሻምን? የኢትዩጲያን ሙስሊም ጥያቄ በማያወላዳ መልኩ መልሶ ብሄራዊ ስሜቱን መመለስ እና የሚመጣውን በጋራ መጋፈጥ ይሻላል ወይስ ግማሽ እግሩ ጎረቤት የረገጠን ህዝብ ይዞ ከጎረቤቱ ጋር መገዳደር? በሶስተኛ ወገን ግፊት የገዛ ህዝብን ማሸማቀቅ ትርፍና ኪሳራው በሚገባ ተሰልቷልን? መንግስት ከመቼውም በላይ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሃገራችንም ሲል ታሪካዊ ስህተት ላለመስራት አቋሙን አሁንም አልረፈደምና ቆም ብሎ ቢፈትሽ ይበጃል፤ እልህ ዳቦ አይሆንምና፡፡ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ፡፡

No comments:
Post a Comment