የኢትዮጵያ ሙሲልም ምዕመናን በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት መንግስት ሰዎችን ማሰሩን መቀጠሉን፦ እስር ላይ የሚገኙትንም ፍርድ ቤት በነፃ ሲያሰናብት ፖሊስ አለቀቀም ማለቱን ለዶቼ ቬለ ገለፁ።
የመብት ተማጋቾቹ ዘገባ ይፋ ከሆነ በኋላ የከሚሴ ኗሪ መሆናቸዉን የገለፁ አንድ አድማጭ ለዶቼ ቬለ
በላኩት መልዕክት እንዳመለከቱት በአካባቢያቸዉ ቤቶች እየተፈተሹ አሁንም ሰዎችም ይታሰራሉ። ወደአካባቢዉ ደዉለን
ለማረጋገጥ ስንሞክር የእሳቸዉ የስልክ መስመር ባይሳካልንም ደቡብ ወሎ የሚገኙ አንድ ሌላ ኗሪ በሃይማኖታች ጣልቃ
ይገባል ያሉት መንግስት ኃይሎች በአካባቢያቸዉ ይፈፅማሉ ያሉትን እንዲህ ገልፀዉልናል። እሳቸዉ እንደሚሉት ከሌሎች
ስፍራ የተያዙ ሰዎች ወደእነሱ አካባቢ ተወስደዉ ይታሰራሉ፤ ከዚያም የት እንደሆነ ወዳልጠቀሱት ወደሌላ ስፍራ
ይወሰዳሉ። ሌላዉ ኤሎባቡር የሚኖሩ የሃይማኖቱ ተከታይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸዉ እስራት እየተካሄደ
ባይሆንም ከዚህ በፊት የታሠሩትን ፍርድ ቤት በነፃ ቢያሰናብትም ፖሊስ አልለቀቃቸዉም ይላሉ፤
የአምነስቲ ዘገባ ፖሊስ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሟቸዉን በሚያገልፁ ወገኖች ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ መጠቀሙንም ገልጿል። የዩናይትድ ስቴትስ የሃይማኖት ነፃነት ተመልካች መድረክ በበኩሉ መንግስት በሙስሊም አማኞች ላይ ቁጥጥሩን አጥብቋል ሲል ከሷል።የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን USCIRF በዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሟቸዉን ያሰሙ ሙስሊሞችን አስሯል፤ 29ኙን ደግሞ ባለፈዉ ሰሞን በአሸባሪነት ወንጅል ከሷል ሲልም አመልክቷል።
ሥለ ጉዳዩ የመንግስት ቃል አቀባይን በስልክ ለማነጋገር ያደረግ ነዉ ሙከራ ለጊዜዉ አልተሳካም።ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት መንግስት የአክራሪ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ያሰጋኛል ባይ ነዉ። ባለፉት በርከት ያሉ ወራት መንግስት ሐባሽ የተሰኘዉ የእስልምና ሃራጥቃ እምነትን ተቀበሉ በሚል አስገድዶናል፤ የእስልማና ምክርቤትን ተጠሪዎች በመምረጥ ሂደት ደጋፊዎቹን ለማስመረጥ ጣልቃ ገብቷል በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ እያካሄዱ እንደሆነ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠቅሷል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ
No comments:
Post a Comment