የመጅሊሱ ቁማርተኞች (ክፍል አንድ)
ሰሞኑን እዚህ ቦታ ልገልፀው በማልፈልገው ቤተሰባዊ ጉዳይ (ለደህንነቴ ስል ነው የማልገልፀው)፣ ለሳምንት ያህል ከአዲስ አበባ ራቅ ወዳለች ከተማ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ወደዚህች ከተማ የወሰደኝ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ሁሌም የዲኔ ጉዳይ ያሳስበኛልና ስለሙስሊሙ ወቅታዊ እንቅስቃሴ በዚህች ከተማ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ ጉጉት ነበረኝና በምችለው አቅም ለማወቅ ጥረት አደርግ ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ እኔና ሌሎች 3 የቅርብ ዘመዶች ያረፍንበት ቤት አንዱ ጎረቤት ሰውዬ በዛው አካባቢ የሚገኝ አንድ መስጂድ ኢማም ናቸው፡፡ ኢማሙ ያሳረፈን ግለሰብ አባት ናቸው፡፡ ካለኝ ልምድ የትም ቦታ ብሄድ የአካባቢውን ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከማጥናት ውጭ ስለራሴ መግለፅ ብዙም ፍላጎት የለኝምና በዛች ቤት ውስጥ ከወሰደኝ ጉዳይ ውጭ ስለምንም ነገር ትንፍሽም አላልኩም፡፡ ወደዛች ከተማ የሄድኩበት ጉዳይ ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ሲቀረኝ ግን ድንገት ካስጠጉኝ ሰዎች ጋር የመወያየት እድል ገጠመኝ፡፡ ወቅቱም የነቢያችን (ሰዐወ)መውሊድ ሊከበር ሳምንት ያህል ጊዜ ቀርቶታልና ወሬው ስለ በአሉ ሆነ፡፡
ኢማሙ ወደኔ እያዩ ፡- “ለምን መውሊድን ከኛ ዘንድ አክብረህ አትመለስም?” ጠየቁኝ፡፡ አስተያየታቸው የቆቅ ነው፡፡ በአይናቸው አይኔን ሰርስረው ለመግባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ከሁኔታቸው ስረዳ ማንነቴንም ለማወቅ የፈለጉ ይመስላሉ፡፡ እድሜያቸው ወደ 60ዎቹ ገደማ ይሆናሉ፡፡ ስለኔ ለማወቅ ጭንቅላታቸውን ክፉኛ እያስጨነቁት እንደሆነ ከሁኔታቸው ተረዳሁ፡፡ከተቃዋሚዎቹ ወገን ይሆን ወይስ ከየትኞቹ ይሆን ? የሚል ጉጉት ይታይባቸወል፡፡ ሳቅ ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አባት የሚላቀቁ አይነት አይደሉም፡፡ ደግመው ጠየቁኝ፡፡
“አብሬያችሁ ባከብር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን በቶሎ መመለስ ስላለብኝ ነው፡፡ስራ ትቼ ነው የመጣሁት” በርጋታ መለስኩኝ፡፡ አባት ተንፈስ አሉ በፎይታ፡፡ ከሳቸው ወገን እንደሆነኩ ደመደሙ፡፡ “እኔስ ከውሃቢያዎቹ መስለከኝ ነበር፣ መንግስትን ከሚያስቸግሩት አክራሪዎች፡፡” ሳቄ መጣ፡፡ ቢሆንም ምንም የተለየ ስሜት አላሳየሁም፡፡ ሰውየው መለፍለፋቸውን ቀጥለዋል “እዚህ ከተማ እኮ መንግስትንም እኛንም መቀመጫ አሳጥተውናል አንተን መሰል ወጣቶች”፡፡ “ምን ልሁን ብለው?” የኔ ጥያቄ ነበር፡፡ “እንዴ ጥጋብ ነዋ! መቼም እርግጠኛ ነኝ አንተ አክራሪነትን አትደግፍም አይደል?...” ኦ ኦ ኦ ሰውየው ከኔ ራስ ሊወርዱ የፈለጉ አልመሰለኝም፡፡ ዝምታዬ ደብሯቸዋል፡፡ በእንግድነት ያሳረፈን ልጃቸው ደግሞ አባቱ እኔን ከሌሎች በተለየ በወሬ ማስጨነቃቸው አልጣመውም፡፡ “አባባ ተወው እንጂ፡፡ እሱ አንተ ለምትለው ጉዳይ ጊዜ የለውም፡፡ ቢያደርገውም እኛን አይመለከተንም፡፡” ልጅ ከረር ያለ አስተያየት ሰጠ፡፡ እኔ ደግሞ ነገር ላለማወሳሰብ ብዬ “ተዋቸው ውይይታቸውን ወድጄዋለሁ፡፡ እንዳባትነታቸው የኛ የወጣቶች ጉዳይ ሊያሳስባቸውና ሊመክሩን የግድ ነው፡፡” በማለት የልብ ልብ ሰጠኋቸው፡፡ ቀጥዬም “አባባ እኔ ሙስሊም ነኝ፣ እንደሙስሊምነቴ ከቁርአንና ሃዲስ ውጭ ልሆን አልችልም፡፡ የሙስሊሙን ተቃውሞ ግን ግዜ ስለሌለኝ ተቀላቅዬ አላውቅም፡፡ እርሶ ምን ይመክሩኛል?” ኢማሙ ፈጠን ብለው “ደግ አድርገሃል እንዳትቀላቀል፡፡ እንዳንተ የተማሩ ወጣቶች በእንደዚህ የማይረባ ነገር ውስጥ መግባት የለባቸውም፡፡ ይህን ተቃውሞ መንግስት ላይ ያስነሱት የእንትን ብሄረሰብ አባላቶች ናቸው ፡፡(“የእንትን ብሄረሰብ” ያልኩት ኢማም ተብዬው የጠሩልኝን የአንድ ብሄር ስም መጥቀስ ስላልፈለኩኝ ነው)፡፡ እኛ ደግሞ የእንትን ብሄረሰብ ስለሆንን የእነሱን ብሄር መከተል የለብንም ፡፡ አክራሪነትን እያስፋፉ ያሉትም የእነሱ ብሄረሰብ አባላቶች ናቸው፡፡” አሉኝ፡፡ ውስጤ እርር ቢልም ሰውየውን ማሰጨረስ ፈለኩ፡፡ መቼም ውስጤ ማረር ከጀመረ አመት(365 ቀናቶች) አልፈውኝ የለ? ይሄንን መቻል አያቅተኝምና ለመቻል ሞከርኩ፡፡ ደግሞም ግራ ገባኝ፡፡ በአንድ ወቅት እዚህ ፌስ ቡክ ላይ አቢይ ጣሰው የተባለው ግለሰብ የአንድ ብሄርን ስም አንስቶ ከሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ጋር የማይገናኝ ቅራቅንቦ ጉዳይ አንስቶ ሲዘበዝብ የነበረው ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ! መንግስት በከተማም በገጠርም ደህና አድርጎ ነውና ያደራጃቸው፡፡ ሙስሊሞች ከዳር እስከ ዳር “አንድ” ሆነው ሲያስቸግሩት በብሄር ለመከፋፈል ሆዳም ቡችሎቹን አሰልጥኖ እየመጣ ይሆን? ለማንኛውም እኔም ወደ አባባ ልመልሳችሁ ፣ ወደ ካድሬው ኢማም፡፡ መቼም ካድሬ ኢማም ስላችሁ ተደናገራችሁ አይደል? ግዴለም ትንሽ ጠብቁኝ፡፡ ኢማማችን ካድሬ መሆናቸውን እራሳቸው ያበስሩናል፡፡ “የኢትዮፕያን ህዳሴ እናበስራለን ” አይደል የሚለው ETV? አቤት መመሳሰል፡፡ ኢማማችንም ጥቂት ቆይተው ካድሬነታቸውን ያበስሩናል፡፡ እኔም አደምጣለሁ፡፡ አሁን እኔ ወደ ጠየኳቸው ጥያቄ እናምራ፡፡ “አባባ የዚህ ከተማም ሆኑ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ያሉ ሙስሊሞች ምን አገባን ብለው ነው የሚቃወሙት ታዲያ? እርስዎ እንደነገሩኝ አክራሪዎቹና ተቃዋሚዎቹ “የእንትን” ብሄረሰቦች ብቻ ከሆኑ ማለቴ ነው፡፡” አልኳቸው፡፡ “አልገባቸውማ፡፡ ህዝቡኮ ዝም ብሎ ነው በስሜት የሚነዳው፡፡ መንግስት ችሎ ነው እንጂ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እኮ እያንዳንዱን ለቃቅሞ ነው የሚያስገባው” አሉኝ፡፡ ቁጣም ጭምር የታከለበት ድምፀት ነበረው መጨረሻ ላይ የወረወሩት ሃረግ፡፡ “ይገርማል” አልኩኝ ፡፡ ሳላስበው ከአፌ አምልጦኝ ነበር የተናገርኩት፡፡ ኢማማችን ደግሞ እሳቸውን ደግፌ የተናገርኩ መስሏቸው “በጣም እንጂ፡፡ በጣም ነው የሚገርሙት፡፡ ውሃቢያ ጠገበች እኮ፡፡” አሉኝ እጃቸውን ጭምር በማወናጨፍ፡፡ ቀጥለውም “ልጄ አንተ ጥሩ ልጅ ትመስላለህ ፣ አዲሳባ ስትመለስ የሃጂ ጡሃን ስልክ ቁጥር እሰጥሃለው፡፡ እሱ ጋር ብትገናኝ ሁሉን ዘርዝሮ ይነግርሃል፡፡ ዘመዴ ነው እለዋለሁ፡፡ ሃጂ ጡሃ ጋር ሆነን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ብዙ ስብሰባዎች አድርገናል፡፡ እንዳንተ ያለ የሚያዳምጥ ወጣት በጣም ነው የሚወደው” ብለውኝ እርፍ ፡፡ እንደ መልማይም ይሰራራቸዋል ለካ ኢማሞቻችን፡፡ ነገሩ ምንም አላማረኝምና እንደደከመኝ ተናግሬ ልነሳ ሳስብ የኢማማችን ስልክ ጮህ፡፡ ኢማሙ “አሎ” አሉ፡፡ ደዋዩ ሰው ሰላምታ ሰጥቷቸው ስሙን ሲነግራቸው ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ተነሱ ኢማማችን፡፡ በኛ አጠገብ ማውራት ስላልፈለጉ ይሁን ፣ወይም የኛ ድምፅ እንዳይገባባቸው ሰግተው እንደሁ አልገባኝም ኢማማችን ካለንበት ክፍል ወጥተው ወደ ጓዳ ገቡ፡፡ ቢሆንም የሚያወሩትን ማዳመጥ እችል ነበር፡፡ ጆሬዬን ደግሞ የበለጠ ወደሳቸው አሰማራሁት፡፡ “… አዎ ጌታዬ ምንም ችግር የለም፡፡ መውሊዱን በደንብ ነው የምንጠቀምበት፡፡ የዚህ ከተማ ህዝብ እኮ መውሊድ በጣም ነው ሚወደው፡፡ እስኪበቃው እናስጨፍረዋለን፡፡ ……አዎ አዎ አዘጋጅተናል፣ መንዙማ የሚሉ ሁሉ አዘጋጅተናል፡፡ ምድረ ፂሙን ያሳደገ አሸባሪ ሁሉ እንዳያውከን ግን የናንተ ጥበቃዎች ይመደቡልን፡፡…….ም…ን…ምንም ችግር የለውም አይጨነቁ ቀላል እኮ ነው! እነሱ ይጨፍራሉ ቀጥለን እኛ ደግሞ ስለአክራሪዎቹ አንዳንድ ነገር እንላለን፣ ከዚህ በኋላ የከተማው ሙስሊም እርስ በርሱ የጎሪጥ እንዲተያይ ነው ምናደርገው….(ፈገግ እያሉም ጭምር ነው የሚያወሩት)….” ቀሪውን የካድሬውን ኢማም ንግግር ከዚህ በላይ ለዚህ ፅሁፍ አንባቢያን ማቅረቡ ዋጋቢስ ነው፡፡ እኔው ትክን እንዳልኩኝ እዛው ያብቃልኝ እንጂ እናንተ ምን በወጣችሁ፡፡ ከሰውየው አፍ የሚወጡት ቃላት ሁሉ ሙስሊምነታቸውን አጠራጥሮኛል፡፡ ስልካቸውን ሲጨርሱ ፊታቸው በፈገግታ ደምቆ ተመለሱ፡፡ ምንም ሳያፍሩ በኩራት የደወለላቸውን ሰው ስም ነገሩን፡፡ (ደዋዩ የዞኑ አስተዳዳሪ እንደሆነም ጭምር አበሰሩን)፡፡ በገደምዳሜም ከባለስልጣናት ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት አለኝ ነው ነገሩ፡፡ ምናለ ከአላህ ጋር ለመቀራረብ ቢጥሩ? ሙስሊሙን ማስገደል፣ ማስደብደብ፣ ማሳሰር፣ በመስጂዱ ፀሎቱን እንዳያደርስ ማስከልከል፣ በሙስሊም መካከል ቁርሾና ልዩነት ለመፍጠር ቀን ከሌት ከጠላቶች ጋር አብሮ ማሴር እውነት ኢስላማዊ አደብ ነው? ከአንድ ሙስሊም ሰውስ ይጠበቃል? አላህ ይፋረዳቸው ከማለት ውጪ ምንም የምለው የለኝም፡፡ የሆኖ ሆኖ ሲነጋ የመጀመሪያው ስራዬ የሰውየውን ማንነት ማጣራት ነበረና ያንን አደረኩኝ፡፡ ሰውየው በመንግስት አማካኝነት የዛ መስጂድ ኢማም ከሆኑ 2 ወር እንኳ እንደማይሞላቸው፣ ለኢማምነት የሚያበቃ እውቀት እንደሌላቸው፣ ኢማም ከሆኑ በኋላ ከሚኖሩበት መንደር አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የእርሻ ቦታ እንደተሰጣቸው፣ ትእዛዝ የሚቀበሉት ሁሉ ከመንግስት አካሎች እንደሆነ ሰማሁ፡፡ እዚህ ጋር አንድ የሚያሳዝንም፣ የሚያስቅም ነገር አብሮ ተነግሮኛል፡፡ የካድሬው ኢማም ካዳሚና በዛው ወረዳ ባለው ህገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ በመንግስት እንዲገባ የተደረገው የኢማሙ የቅርብ ሰው (እንደካዳሚያቸውም ጭምር ነው የሚያገለግለው) በአንድ ወቅት ሰደቃ ይደረግና ሰደቃው ቦታ ይሄዳል፡፡ ሰደቃ የተደረገበት ቤት ሲደርስ ገና ቁርአን እየተቀራ በመሆኑ እሰከዛው ገብቶ ቁርዐን ከሚቀሩት ሰዎች ጋር ተደባልቆ ቁጭ ሲል ቁርዐን ለመቅራት የፈለገ መስሎዋቸው አንዱ የሰደቃ ቤቱ ካዲም ቁርዐን ይሰጠዋል፡፡ ይህ ሰው ታዲያ ቁርዐን መቅራት አይችልምና የምን ተፍረቱን ቁርዐኑን ከፍቶ ቁጭ ይላል፡፡ የሚያስገርመው ይህ አይደለም፡፡ቁርዐን መቅራት አልችልም ብሎ መመለስ እየተቻለ እንደሚቀራ ሰው ከፍቶ አፍጦበታል፡፡ ባጋጣሚ ሰደቃው ቦታ ሌላ ሰው ይገባና ከዚህ ሰውዬ ኋላ ይቀመጣል፡፡ ቁርዐኑን ከፍቶ ወደተቀመጠው ሰው ሲመለከት ግራ ገብቶት ሰውየውን ተመለከተው፡፡ ቁርዐን እንደሚችል ሰው ቁርዐኑን ከፍቶ አቀርቅሮ የተቀመጠውን ሰው “ጤነኛነት” የተጠራጠረው ሰው ሰውየውን ትከኛውን ይነካውና ቁርዐኑን ገልብጦ እንደያዘው ይነግረዋል፡፡ እንዴት አድርጎ መያዝ እንዳለበትም አስተካክሎ ሰጠው፡፡ ቁርዐንን መቅራት አለመቻል ብቻም ሳይሆን አስተካክሎ መያዝ የማይችል ሰው ነው እንግዲህ መንግስት “ለመጅሊሳችሁ” ይመጥናል ብሎ የሾመላቸው፡፡ ባካባቢው ሰው ለተጠሉት ካድሬው ኢማምም ካዳሚ በመሆን ተጨማሪ ስራ አለው፡፡ እንዴት አይነት አሳቢ መንግስት ነው ያለን! የመንግስት ውለታ በዛብን እኮ ጃል! ይህን አሳፋሪ ነገር ሰምቼ ከቤተቦቼና ከቅርብ ዘመዶች ጋር ወደ አዲሳባ ስመለስ ክፉኛ ሃዘን እየተሰማኝ ነበር፡፡ ወጣቱ ለሃይማኖቱ ተቆርቁሮ ህይወቱን እስከመስጠት እንቅስቃሴ ሲያደርግ በአንፃሩ ለመቃብር የቀረቡ አንዳንድ ባለ “ሁለት ፀጉሮች” ግን መስጂድ ውስጥ በዲኑ ላይ ቁማር ይጫወታሉ፡፡ አዲስ አበባ ገብቼ ይህን ነገር ለአንዱ የልብ ወዳጄ ስነግረው ሌላ ነግርም ጨመረልኝ፡፡ ይህ ወዳጄ እንደነገረኝ ባለፈው ሃሙስ ሸህ ጡሃ ከኢሻ በፊት መንዙማ ብሎ እንዳበቃ “ፂም ከማሳደጋችሁ በፊት መጀመሪያ ፀጉራችሁን አበጥሩ ”፣ “… ሙስሊም ሆነው ነቢዩን የማይወዱ አሉ…” ብሎ እንደነበር አወጋኝ፡፡ በተጨማሪም በድምፃችን ይሰማ በኩል የተለቀቀ መረጃ ሳነብ ይሄው ሸህ ጡሃ የተባለ ግለሰብ ለአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሰዎች “…ህዝቡን ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ በነፈሰበት የሚሄድ ነው፡፡ በሬ ብናርድለትና ብናበላው አላሁ አክበር ማለቱን ትቶ በግፊያ ወደኛ እንደሚመጣ ከዚህ በፊት ባለን ልምድ እናውቀዋለን…” በማለት ሙስሊሙ ዐላማ ቢስ እንደሆነና ለሆዱ ሲል ዲኑን እንደሚሸጥ አድርጎ የተናገረውን አገኘሁ፡፡ እርግጥ ነው ይህ ግለሰብ አብዛኛውን ግዜ የአላህን ቃልና የነቢያችንን (ሰዐወ) ንግግሮች ከማስተላለፍ ይልቅ ሙናፊቃዊ ንግግሮችን በማስተላለፍ ይታወቃል፡፡ የሃገራችንን ትላልቅና የተከበሩ ዐሊሞችን ስም እየጠራ ከሱ እንደማይበልጡ ያወራል፡፡ በአንፃሩ አደግሞ መስጂድ ውስጥ የኢስላም ጠላቶችን በማወደስ ይታወቃል፡፡ በአድ ወቅት በአንዋር መስጂድ ቅዳሜ ቀን ለህዝቡ ጥሪ አድርጎ መንግስትም ጣልቃ አልገባም፣ እህባሽም የለም ለማለት በጠራው ስብሰባ ላይ ህዝቡ ዶክተር ሽፈራው በሃረማያ ያደረጉትን ንግግር ሲያስታውሷቸው “የተከበረ የመንግስት ባለስልጣን ስም እዚህ ባናነሳ ይሻላል” በማለት ዐሊሞቻችንን እየተዛለፈ ለባለስልጣኖች ግን ጥብቅና የቆመ ሌላኛውና ዋነኛው የመጅሊሱ ስር ቁማርተኛ ነው፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርላማ ቀርበው የአርሲ ሙስሊሞች አልቃኢዳ እንደሆኑ የዘባረቁበትንና ለአሰሳ ሙስሊሞች ጭፍጨፋ ምክንያት ለሆነው ንግግራቸው እውቅና በመስጠት ፖለቲከኛውና የመጅሊሱ ስር ቁማርተኛው ሸህ ጡሃ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስድብ ቅጂ ከቢሮው ሆኖ በማይክ በመልቀቅ አቻ የሌለው የኢስላም ጠላትቱን ማስመስከሩን አንረሳውም፡፡ በአንድ ጁሙዐ ላይም ከጁሙዐ ሰላት በፊት ባደረገው ንግግሩ አይሁዶችን ጨምሮ ከኢስላም ውጭ የሆኑትን እምነቶች ስም በመጥራት ካወደሰ በኋላ በየትኛውም አለም የሚገኙ ሙስሊሞች ግን በሀይል እንደሚያምኑ ደስኩሯል፡፡ ስለ ዲናችሁ ነፃነት ለምን በሰላማዊ መንገድ መንግስትን ተቃወማችሁ ነው ነገሩ፡፡ መቼም ግን ሙስሊም ተጨቆነ፣ ተገደለ ብሎ ተናግሮ አያውቅም፡፡ ከነዶክተር ሽፈራው ጋር ባደረገው ስብሰባ ኮሚቴዎቻችንን ከመሳደቡም በላይ ሙስሊም አይደሉም ብሏል፡፡ ኮሚቴዎቻችን እንደሱ ሆዳሞችና ቁማርተኞች ስላልሆኑ በሱ አፍ መሰደብ ነበረባቸው? ለነገሩ እሱ (ሸህ ጠሃ)ለእስልምናና ለሙስሊሙ የሚጨነቅበት ግዜም ሆነ ምክንያት የለውም፡፡ እሱ የመጅሊሱ ስር ቁማርተኞች አንዱ አባል ነውና! ከላይ መግቢያዬ ላይ ያነሳኋቸው ካድሬው ኢማምና የሸህ ጡሃ አይነት የመጅሊስ ስር ቁማርተኞች አሁን አሁን መንግስት ከራሱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ኮሌጅ እየተመረቁ ወደ ስራ እየተሰማሩ ነው፡፡ ሰሞኑን የህይወት መስዋእትነት ተከፍሎባቸው የተገነቡ መስጂዶቻችንን እየወረሩ ያሉት እንዚህ ቁማርተኞች ናቸው፡፡” መውሊድ ብለን ህዝቡን እንከፋፍለዋለን” እያሉ በጓዳ ከመንግስት ጋር ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ሲዶልቱ አላህ እያጋለጣቸው ነው፡፡ ሲጀመር እነዚህ ሰዎች ስለ ረሱል (ሰዐወ) ፍቅር ለማውራት ምንም ሞራል የሌላቸው ናቸው፡፡ ፂም ማሳደግ፣ ሱሪም ሆነ ጀለቢያ ማሳጠር የነቢዩ ሱና እንደሆነ እያወቁ ይህን ያደረገ ሁላ አሸባሪ ነው ይላሉ፡፡ ወጣቱን ደግሞ ወደ ሱስ እንዲሄድ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ በመጅሊሱ በኩል እየመጡ ያሉት ቁማርተኞች መውሊድ ተከበረ፣ አልተከበረ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ የነሱ ፍላጎት ጥቃቅን ሊዩነቶችን እያነሱ ሙስሊሙን ሰላም መንሳት ነው፡፡ ከመጅሊሱ ቁማርተኞች አውራውና የህዝበ ሙስሊሙን ገንዘብ በመመዝበር አቻ የማይገኝለት ሸህ ኤልያስ ሬድማን ከዚህ ቀደም “ስለ አንድነት ምንም ወሬ አልፈልግም” በማለት ትላልቅ ዐሊሞች ስለ አንድነት ውይይት እንደጀመሩ ከመንግስትጋር በመሆን እንዳኮላሸው አንረሳም፡፡ ፍላጎታቸው አላህን ማገልገል አይደለም፡፡ የነሱ ፍላጎት በመጅሊስ ስር ሰርገው ገብተው የሙስሊሙን አንድነት መበታተን ነው፡፡ ለዚህ ውለታቸው ደግሞ ከኢስላም ጠላቶች ቋሚ አበል አላቸው፡፡ የሚያዋጣው ጥምጣም ጠምጥሞ ቁማር መጫወት ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በረሱል ዐለይሂ ሰላም ዘመን መዲና ውስጥ የሙናፊቆች አለቃ ከነበረው ከአብደላህ ቢን ኡበይ የበለጠ ቁማርተኞች ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ሙስሊሙ ያለማንም ውትወታ አንድነቱን መልሷል፡፡ በጥቃቅንና መሰረታዊ ባልሆኑ ሃይማኖታዊ ቀኖናዎች (Doctrines) መለያየትን ትቶታል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ መንግስትንና የመጅሊሱ ቁማርተኞችን ሰላም ነስቷቸዋል፡፡ ለዚህ ነ ው መንግስት በግልፅ ባጀት መድቦላቸው “በታትኗቸው” ብሎ ሰሞኑን በመውሊድ ሰበብ የቤት ስራቸውን ይዘው ከተፍ ያሉት፡፡ ከመንግስት ጋር ሲሆኑ በጓሮ ህዝቡን “ሆዳም ነው ለሆዱ ሲል ሲመጣ እንበታትነዋለን” እያሉ ፣ፊት ለፊት ሲሆኑ ደግሞ ለስለስ ብለው የነቢዩ ወዳጆች ነን ይላሉ፡፡ አንድም ቀን ግን የነቢዩን ፈለግ ሲተገብሩ አይታዩም፡፡ ሙስሊም ማስገደል ፣ ማሳሰር፣ ማስደብደብ፣ መስጂድ ማስቀማት የነቢዩ ፈለግ ነው ብሎ ያቀራቸው የትኛው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጠቢብ እንደሆነ አላህ ይወቀው፡፡ እነሱም ይህ አያሳስባቸውም፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ፣ እንዲሁም በአላህና ነቢዩ ዲን ላይ ቁማር መጫወታቸውን ግን ቀጥለዋል፡፡ ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች የመውሊድን በአል አስታከው ሰሞኑን እየመጡ ሆዳም ቁማርተኞችን ልናሳፍራቸው ይገባል፡፡ ይህን ፅሁፍ ያነበብን ሁላ ብንችል ፕሪንት አድርገን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆኑ ወንድሞች፣ እህቶች፣ እናቶችና አባቶች እናድርስ፡፡ ያልቸልን ደግሞ ቢያንስ ያነበብነውን ሃሳብ እናስተላልፍ፡፡ አላህ የመጅሊሱ ስር ቁማርተኞችን ሴራ ያክሽፍልን፡፡ የሙስሊሙንም ለቅሶ ይስማ፡፡ አሚን፡

No comments:
Post a Comment