Tuesday, January 1, 2013

Global Council for justice in Toronto Dec 30-2012



የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ትግል የጀመሩበትን 1ኛ አመት ቶሮንቶ በሚገኘው ሳላህዲን እስላማዊ ማእከል ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን አከበሩ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አለማቀፍ ምክርቤታ የቶሮንቶ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው በዚህ አንደኛ አመት መታሰቢያ በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል።
በአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ፤ ከጀርመን ተጉዘው የመጡትና፤ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ሙስሊም ሀጂ መሀመድ አህመድ ልጅ፤ አቶ መሀመድ ሀሰን ስለሙስሊሞች ትግል ውጣውረድ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን እንዳቀደ የሚያሳይ ሰነድ ከእጃቸው እንደገባ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፤ ላለፉት 12 ወራት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርገው አፈና በዚህ ምስጢራዊ ሰነድ ውስጥ እንደተካተተ ተናግረዋል።
አተ መሀመድ ሀሰን የሙስሊሞችን የአንድ አመት ትግል ሂደት የሚያሳዩና ለትግሉ የተደረገውን አለማቀፍ ድጋፍ የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎችን ለተሰብሳቢዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ ተሰብሳቢዎቹ አቶ መሀመድ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ የአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የህገመንግስቱ አንቀጽ 27 እንዲከበር ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፤ “ድምጻችን ይሰማ፤ ሰላም አጣን ባገራችን፤ መንግስት የለም ወይ” የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል።
በዝግጅቱ ላይ በቶሮንቶ የሚገኙ አገር ወዳድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንም ተገኝተዋል።

No comments:

Post a Comment