Monday, February 11, 2013


ሰበር ዜና

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የአርቡ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ሁከት ለመፍጠር ያደረገው ሙከራ ከሸፈ

ሁከት ፈጣሪዎቹ በራሪ ወረቀቶች እንዲበትኑ ተልእኮ ተሠጥቷቸው ነበር

የድርጊቱ ዋነኛ ተዋናይ ዶክተር ሺፈራው እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ናቸው

ባለፈው ሳምንት መንግስት ሕገ መንግስቱንና የራሱን ፍ/ቤቱን ትዕዛዝ በመጣስ ያሰራጨው ‹‹ጂሀዳዊ ሃራካት›› ‹‹ፊልም››ን በመከተል ሙስሊሙ ህብረተሰብ ባለፈው ጁሙዓ በአንዋር መስጊድ ባካሄደው ከባድ ተቃውሞ ላይ መንግስት ሁከት ለማስነሳት ሙከራ አድርጎ እንደነበርና፤ ሙከራውም ሳይሳካ መክሸፉ ተሰማ፡፡ በእለቱ የመንግስት ባለስልጣናት ዶ/ር ሺፈራው፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሕመድ እንዲሁም የፌዴራል መጅሊስ ሀላፊዎች በጋራ ለመጅሊስ ተመራጭና በአዲሱ የአሕባሽ ማህበር ስር ለተሰባሰቡ ሰዎች አበል በማዘጋጀት አንድ ተልእኮ ሰጥተው ነበር፡፡ ይኸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ‹‹በጂሃዳዊ ሀረካት›› ፊልም ስለተቆጣ ዛሬ ትንሽ ነካ ብናደርገው ለብጥብጥ ወደኋላ አይልም የሚል ግምት በማዘል የተሰባሰቡት ሰዎች በራሪ ወረቀት በአርቡ የተቃውሞ ትዕይንት መሀል እንዲበትኑ ነበር፡፡ ይበተናል የተባለው ወረቀት ‹‹መስጂዶቻችን የጥቂት አክራሪዎች መፈንጫ አይሆኑም›› የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት የነበረ ሲሆን ይህን ይበትናሉ የተባሉትና ስለተሰጣቸው አደገኛ ተልእኮ በውል የማያውቁ የሚበዙበት ቡድን ስራውን ለማሳካት ወደ አንዋር ቢንቀሳቀስም አንዋር ቢንቀሳቀስም በአንዋር የገጠመው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሙስሊምን ሲመለከት ሀሳቡን እንዲቀይር አስገድዶታል፡፡

ከኢዱ ተቃውሞ ቀጥሎ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረበትና ሰዎች በአደባባይ እንባቸውን እየዘሩ ጭምር ለመሪዎቻቸው ያላቸውን ታማኝነት እንዲሁም መንግስት በመሪዎቻችን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ ቶርች በምሬት የገለጹበት ትይንት ላይ የተገኙት የመንግስት ተልእኮ አስፈጻሚዎች የሚያዩትን ነገር ባለማመንና የሙስሊሙን ቁጣ በቅርበት ማየት በመቻላቸው የተሰጣቸውን ተልእኮ ሳይፈጽሙ ቀርተዋል፡፡ ብዙዎቹ የተልእኮው አስፈጻሚዎች መንግስት እኛን እርስ በእርስ ሊያስገድለንና የራሱን የፖለቲካ ትርፍ ሊያጋብስ በማሰብ የጎነጎነው ሴራ ነው በሚል ስሜት የተሰጣቸውን ወረቀት ሳይበትኑ ተመልሰዋል፡፡ የወረቀቱ መበተን አላማ ወረቀቱን በሚበተንበት ወቅት የሚከሰተውን ግርግር ተጠቅሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ መቀየር እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ይህ የከሸፈው የጁመዓ ሴራቸው ባለፈው አንድ አመት በመላው ሃገሪቱ ለተፈጠሩ ሁከቶችና ግድያዎች መነሾውና ጠንሳሹ መንግስት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

የዚሁ ተልእኮ አስፈጻሚዎ በነጋታውና ከዚያም ቀን በኋላ ከመጅሊስና አቶ ኩማ ደመቅሳን ጨምሮ ከሌሎች የመንግስት ሀላፊዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቁጣ በተሞላበት መለኩ መንግስት ሰጥቷቸው የነበረው ተልእኮ አደገኛ እንደነበርና መንግስት በመሰል ተግባሮች ለምን መሰማራት እንደፈለገም ጠይቀዋል፡፡ በሙስሊሙ መሀከል ግጭት እና አለመግባባት እንዲፈጠር መንግስት ለምን ይፈልጋል? የሚለው ዋነኛው ጥያቄ ነበር፡፡ በተጨማሪም ማክሰኞ ከ‹‹ፊልሙ›› በኃላ ሌሊት ላይ በስህተት ተለቀቀ በተባለው ፊልም ለምን እንደተለቀቀ ተሳታፊዎቹ የጠየቁ ሲሆን አቡበከርን በዚህ አይነት ሁኔታ የሚያንገላታ ቪዲዮ ለሕዝብ መሰራጨቱ ፋይዳው ምንድን ነው? የሚል ሞጋች ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ብዙዎቹ የመጅሊስና የፍ/ቢሮ ሃላፊዎችም በወቅቱ መልስ መስጥት ሳይችሉ ቀርተው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በገንዘብና በስልጣን ተደልለውም ሆነ መንግስት በጎ የሰራ መስሏቸው በሌላው ህዝብ ላይ በተንኮል የሚሰለፉ ካለ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው፡፡ ዛሬም ደግመን የምንናገረው የሚሊዮኖችን ጥያቄ በሃይል እርምጃና በተንኮል ለማክሸፍ መሞከር መንግሰታዊ ባህሪ አለመሆኑን ነው፡፡ ከመንግስት የሚጠበቀው ተግባር ህዝብን አስተባብሮ ለልማት ማሰለፍ እንጂ ህዝብን በህዝብ ላይ አነሳስቶ እልቂትን መጋበዝ አይደለም፡፡

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment