Sunday, November 18, 2012

የዛሬውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የህዝብ ማዕበል


የዛሬውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የህዝብ ማዕበልን ፈስቢር እንደሚከተለው በአጭሩ አቅርባዋለች፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኝ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ገና ከመንጋቱ በፊት ነበር ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የደረሰው፡፡ በጣም በርካታ ሙስሊሞች ሱብሂ ሳላት አዛን ከማለቱ በፊት የደረሱ ሲሆን የሱብሂ ሰላትንም እዚያው በጀመዓ እና በተናጥል በየቦታው ምንጣፋቸውን አንጥፈው የሱብሂ ሰላትን አከናውነዋል፡፡

በተለይ ሱብሂ ሰላት ከተሰገደ በኋላ በጣም እጅግ ብዛት ያለው ሰው ወደ ማረሚያ ቤቱ የጎረፈ ሲሆን ይህ የሰው ማዕበል እስከመጨረሻው አልተቋረጠም፡፡

የማረሚያ ቤቱ በር ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ክፍት ተደረገ፤ ነገር ግን ያለምንም ጥፋታቸው በግፍ የታሰሩ ኮሚቴዎችንን እና የሃይማኖት አባቶችን ለመጎብኘት የመጣው ህዝብ ቁጥር አጅግ በርካታ በመሆኑ ህዝቡን ሊያስተናግድ እና ሊያሰልፍ የሚችል ቦታ በመጥፋቱ፤ ህዝቡ ወደ ተለያዩ መንደሮች እና ቅያሶች በረጅሙ፤ በሁለት እና በሶስት ረድፍ ለመሰለፍ ተገዷል፡፡

የማረሚያ ቤቱ አካባቢዎች፤ ቅያሶች፤ ሰፈሮች እንዲሁም ዋናውን ጎዳና ጨምሮ በሙስሊሞች ተጨናንቋል፡፡ በአካባቢው ያሉት መንገዶች እና ጎዳናዎች ህዝቡን ማስተናገድ ባለመቻላቸው፡፡ ሙስሊሙ ከማረሚያ ቤቱ በጣም ርቆ ተሰልፏል፡፡

በዛሬው ልዩ እና ድንቅ የሆነው፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከወከላቸው መሪዎቹ ጎን መሰለፉንና አጋርነቱን የሚገልፅበት ትዕይንት ብዙዎቹን ያስደመመ ነበር፡፡ በትዕይነቱ ላይ ህዝቡ ይበልጥ ወንድማማችነትንና አንድነትን ያንፀባረቀበት ሲሆን፤ ብዙ ሙስሊሞች ከቤታቸው አንዳችም ውሃም ሆነ ምግብ ሳይቀምሱ በስፋራው የደረሱ በመሆናቸው፤ አንዱ ለሌላው ውሃን እና በአካባቢው የሚገኘውን ብስኩት እና ሌላ ነገር ሲለግስ ተስተውሏል፡፡

በጣም ሳይመሰገን የማይታለፈው በአካባቢው የሚኙ ክርስቲያን ወንደሞቻችን ያበረከቱት አስተዋፅኦ ነበር፡፡ እነዚህ ወንደሞች ለረጅም ሰዓታታ ያለምንም መሰልቸት እና መድከም፡ በፀሀይ እየተንቃቃ ለሚገኙ ወንድሞቻቸው፡ የምግብ እና የውሃ አቅርቦት እያበረከቱ ነበር፡፡ አሁንም በድጋሚ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን ሳናመሰግን አናልፍም፡፡

ሌላው በዛሬው የዚያራ ፕሮግራም ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ የአዲስ አበባ ፖሊሶች በጣም በብዛት ተገኝተዋል፡፡ ስርዓቱንም በአግባቡ ሲመሩት የቆዩ ቢሆንም፤ ካሁን በፊት በአካባቢው ተገኝተው የማያውቁት የፌድራል ፖሊሶች ዛሬ በብዛት በአካባቢው መገኘት ብዙ ሙስሊሞችንና የአካባቢው ነዋሪዎችን ያነጋገረ ክስተት ነበር፡፡

እነዚህ የፌደራል ፖሊሶች መሳሪያቸውን፤ ከሙሉ ትጥቅ ጋር አንግበው፤ መኪናቸው ላይ ታጭቀው፤ እንዲህ በህዝብ በተጨናነቁ መንገዶች እና ቅያሶች ሙስሊሙን ህዝብ እየገፉ እና እያስፈራሩ፡ ትንኮሳ በሚመስል ሁኔታ፡ ወደ ላይና ወደ ታች በተደጋጋሚ መመላለሳቸው ህዝቡን ግርምት ውሰጥ እንዲገባ አድረጎታል፡፡
ሆኖም ሰላም ወዳዱ ሙስሉሙ ማህበረሰባችን ለእንዲህ ዓይነቱ ትንኮሳ ክፍተት እንዳይሰጥ ቀድሞውኑ በምርጥ አሚሮቻችን (ድምፃችን ይሰማ) የተላለፈለት በመሆኑ ትንኮሳውን በታላቅ ትዕግስት አልፎታል፡፡

በእንዲህ መልኩ እያለ የዚያራው ሰዓት ወደ መገባደጃው ወቅት ተቃረበ፡ ከቀኑ 6፡20 አካባቢ የማረሚያቤቱ ዘበኞች እና ፖሊሶች ከዚህ በላይ ህዝብ ማስተናገድ እንደማይችሉ እና የዚያራው ሰዓት በመጠናቀቁ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በሌሎች ቀኖች ተገኝቶ ዚያራውን እንዲያከናውን መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በቡድን በቡድን ሆኖ ወደ ማረሚያ ቤቱ ግቢ የሚገባው ሰው ኮሚቴዎቻችንን ከአንድ ደቂቃ ለማይበልጥ ጊዜ ብቻ አናግሮና ዘይሮ የሚወጣ ቢሆንም፤ ከህዝቡ ብዛት የተነሳ ዛሬ እነሱን ለመጠየቅ ከተሰለፈው ህዝብ መካከል አስር ፐርሰንት ያህሉ እንኳ ዕድሉን አላገኘም፡፡

በመጨረሻም ዘጠና ከመቶ የሚሆነው ተሰላፊ የዚያራውን ዕድል ባያገኝም፤ ያለምንም ረብሻ እና ሁከት ሙስሊሙ ህበረተሰብ ኢስላማዊ አደብን እንደጠበቀ፤ ወደየቤቱ ተመልሷል፡፡

ዛሬ በዚህ ታላቅ፤ ግዙፍ እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስተናገደው የጥየቃ ፕሮግራም ላይ ለተሳተፉ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አላህ የኸይር ጀዛአቸውን ይክፈላቸው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!!!
አላሁ አክበር!!!

Saturday, November 17, 2012

ከቃሊቲ የመልስ ጉዞ ወደ ቤት


‎6፡17

አሁን መሪዎቻችንን የመጠየቂያ ሠዓት በመጠናቀቁ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በር ተዘግቷል፡፡ በመርሐ ግብራችን መሰረት ዚያራችን ያበቃ በመሆኑም በሰላም ከአሁን ጀምሮ ሁላችንም (መሪዎቻችንን የዘየርንም ሆነ ያልዘየርን) ወደየቤታችን እንመለስ፡፡ የዚያራ መርሐ ግብሩን ሪፖርታዥ አጠናቅረን ከአፍታ ቆይታ በኋላ እናቀርባለን፤ አብራችሁን ቆዩ፡፡
Top of Form
ከቀኑ 6፡03

እሰከ አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከማለዳው 1:30 ቃሊቲ የደረሱ ሰዎች ከሕዝቡ ብዛት አንጻር ቃሊቲ ገብተው መሪዎቻችንን መጎብኘት አልቻሉም፡፡ የሕዝቡ ቁጥር ከተገመተውም በላይ ነው፡፡ አላሁ አክበር፡፡
ከቃሊቲ የመልስ ጉዞ ወደ ቤት

Top of Form
‎5፡54

በቃሊቲ ታሪክ እንደ አዲስ እየተጻፈ ነው፡፡ የታሪኩ ፈጻሚም ጸሐፊም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ላይ ያልታየ የኅሊና እስረኞችን የመጎብኘት ሕዝባዊ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬም አንናገራለን ሕዝብ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር የአላህ እርዳታ እየተከተለን ነው፡፡
Top of Form
ወደ ቤታችን ስንመለስ የሚገጥሙን ትንኮሳዎች ስለሚኖሩ ሁሉንም ለሰላም ስንል በመታገስ ወደ ትልቁ ዓላማችን እንገስግስ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!!
Top of Form
የቃሊቲ አካባቢ የረፋድ ጸሐይ ብርቱ ቢሆንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ጸሐዩ ሳይበግረው ወረፋው ላይ ቋሟል፡፡ የሕዝቡ ትእግስትና ጽናት የምርም ያስደንቃል፡፡
Top of Form
‎5፡25

በቃሊቲና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሌሎች ሕዝባዊ ትዕንቶቻችን እንደታየው ወረፋ ላይ ለሚገኙ ሙስሊም ዚያራ አድራጊዎች መብል እና ውሃ በመስጠት አጋርነታቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡
Top of Form
ከረፋዱ 4፡46

ወደ ቃሊቲ ከማለዳው ጀምሮ የሚደረገው ጉዞ እንደቀጠለ ነው፡፡ በቃሊቲና አካባቢዋ ያለው ሕዝብ ብዛት እንዳይታወቅና ሰልፉ ወደ ዋናው ጎዳና እንዳይወጣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሕዝቡን በመንደሮቹ ውስጥ ቢያሰልፉትም የሕዝቡ ብዛት የቃሊቲ ዋና መንገድ ላይ ከመድረስ አልተገታም፡፡ አሁን ሕዝቡ ዋናው አውራ ጎዳና ላይ ወለል ብሎ ይታያል፡፡ አሁንም ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ ቃሊቲ በመትመም ላይ ነው፡፡
Top of Form
ረጃጅም ሰልፎች በቃሊቲ




Top of Form

‎5፡42

የዚያራ ሰዓቱ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የቀሩት ቢሆንም ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መግባት የቻለው ሕዝብ ከሄደውና ወረፋ ከያዘው ሕዝብ አንጻር እጅግ በጣም ጥቂት ነው፡፡ የዚያራ ሰዓቱ ሲጠናቀቅ መሪዎቻችንን የማየት እድሉን ባናገኝ እንኳ አላህ ኒያችንን እንዲቀበለን ዱዓ በማድረግና በድል አድራጊነት ስሜት ወደየመጣንበት እንመለሳለን፤ ኢንሻአላህ፡፡
Top of Form
ሕዝቡ ወደ ቃሊቲ ውስጥ የመግባት እድል እንደሌለው እያወቀም በትዕግስት ቆሟል፡፡
Top of Form

ከረፋዱ 5:02

አዲስ አበባ ለሚኖሩና ዛሬ ቃሊቲ ለዚያራ ለሄዱ ሙስሊሞች የመልካም ምኞት መግለጫዎች እየመጡ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች መልእክታቸውን ያደረሱ ሙስሊሞች ‹‹መሪዎቻችንን የመዘየር እድል ባናገኝም በሐሳብ ግን ከእናንተ ጋር ነን›› የሚል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእሲያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ተመሳሳይ መልእክት ያዘለ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ልከዋል፡፡ የሁሉም መልእክቶች ጭብጥ በዚህ ታሪካዊ ትእይንተ ዚያራ የተገኙ ሙሊሞችን ታሪካዊ እድለኝነት ይመሰክራሉ፡፡
Top of Form

ቃሊቲ ወህኒ ቤት ለዚያራ ለመግባት የሚጠባበቁ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በፍጽም እርጋታ ወረፋቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ሰልፈኛ እርስ በእርስ በመተዛዘንና ያለውን ምግብና መጠጥ እየተካፈለ ፍቅሩንም ጭምር በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡
Top of Form
ወደ ቃሊቲ ውስጥ መገባት ተጀምሯል፡፡ በተለመደው እርጋታችን ወደ መሪዎቻችን እንግባ፡፡

Top of Form
· 
ወደ ጊቢ ከመገባቱ በፊትም ሆነ በኋላ ምንም ዓይነት መገፋፋት እና መሯሯጥ እንዳይኖር ጥንቃቄ እናድርግ፡፡
Top of Form

አሁን ከማለዳው 2፡45

እስከ አሁን ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር የለም፡፡ መንገዱ ሁሉ ሰላም ነው፡፡ ጉዞ ያልጀመርን በተጠቀሱት የትራንስፖርት መስመሮች በመጠቀም ጉዞ እንጀምር፡፡
Top of Form
በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ማረሚያ ቤቱ አስከ አሁን አልተከፈተም፡፡ ሕዝቡ በተለመደው ታጋሽነት የማረሚያ ቤቱን መከፈት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው፡፡
Top of Form
ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለምንመጣ ሁሉ የትራንስፖርት አጠቃቀም

1.
ከመርካቶና አካባቢዋ የምንመጣ ከአውቶቢስ ተራ ቃሊቲ ድረስ አዲስ ከተማ ት/
ቤት ፊት ለፊት ታክሲና ሎንችን እናገኛለን:: ይህንን ካጣን እስከ ሳሪስ ታክሲ በመያዝ ከሳሪስ ቃሊቲ መሳፈር እንችላለን:: እንደ አማራጭ መርካቶ ውስጥ ሲኒማራስ ጀርባ ቃሊቲ ድረስ ታክሲ ያለ ሲሆን ካሳጠሩት ሳሪስ ድረስ መሳፈር፤ ሌላው አማራጭ የከተማ አውቶቢስ ከመርካቶ ቃሊቲ 4 ቁጥርን መጠቀም እንችላለን፡፡ እሷን ካጣንና አማራጭ 29 ን አስከ ሳሪስ መጠቀም እንችላለን
2. ከአየር ጤና ዓለም ባንክ ካራቆሬና አካባቢዋ የምንመጣ ከአየርጤና አደባባይ ወደቆሼ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ሳሪስ አቦ ድረስ ሎንቺን በብዛት አለ፡፡ ማሰልጠኛ በመውረድ በእግር ቅርብ ሲሆን አማራጭ ታክሲም እናገኛለን ቆሞ ከመጠበቅ
እየሄዱ መጠበቅ ይመከራል አየርጤና አደባባይ ተሻግሮ በቄራ በኩል እስከ ሳሪስ የሎንችን መስመር እናገኛለን፡፡ከሳሪስ ቃሊቲ ታክሲ፣ ሃይገር እና ሎንችን መጠቀም እንችላለን፡፡ እንደ አማራጭ ከአየር ጤና በቆሼ በኩል 86 ቁጥር ባስ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ድረስ
መጠቀም እንችላለን

3.
ከፒያሳና አካባቢው የምንመጣ ሰዎች እስከ ሳሪስ ታክሲ፣ ሀይገር ወይም 14
ቁጥር ባስን መጠቀም እንችላለን፤ ከዚያ ከሳሪስ ቃሊቲ፡፡
4
ከአራት ኪሎና አካባቢው የምንመጣ ወደ ለገሃር በመምጣት የተሻለ
የትራንስፖርት አማራጭ አለ እስከ፡፡ ሳሪስ ካራዘሙት ቃሊቲ ድረስ ታክሲ እስታድየም
ጋር ለገሃር ውስጥ ሃይገር ቃሊቲ ድረስ በሽ ነው፡፡ እንደ አማራጭ 27 እና 25 ቁጥር
ባሶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ ከተገኘ 56 ቁጥር ባስ እስከ ሳሪስ ወይም 25 ቁጥር ልዩ 110 ቁጥርም እስከ ቃሊቲ መጠቀም እንችላለን::

5.
ከመገናኛና አካባቢዋ የምንመጣ ከውስጥ መገናኛ ሃይገር ሳሪስ አቦ ድረስ
በብዛት ያለ ሲሆን፤ ስንወርድ ዘንባባ ብለን በመውረድ ሳሪስ በዘንባባ ሆስፒታል
በማቋረጥ ከሳሪስ እንሳፈራለን፡፡ ሳሪስ አቦ ከሳሪስ እየሞላ ስለሚመጣ የታክሲ
እጥረት አለ፡፡

6.
ከውስጥ መገናኛ 76 ቁጥር ባስ ቃሊቲ ድረስ ትሄዳለች፡፡ ከመገናኛ ቦሌ፣ ከቦሌ ሳሪስ ታክሲ ቦሌ ድልድይ ስር እናገኛለን፡፡

የተሰጡትን የመርሐ ግብሩ ማሳሰቢያዎች በአግባቡ ለመፈጸም ሁላችንም እንጣር፡፡ የዚያራ መርሐግብሩ የቀጥታ ዘገባ (live blog) አሁን ተጀሯል፡፡Top of Form
ከሱብሂ ሶላት ጀምሮ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚተምመው ሕዝብ ብዛት ለማመን የሚቸግር ሆኗል፡፡ ከማለዳው 12፡30 የቃሊቲ ዋናው አውራ ጎዳና ደርሷል፡፡