መንግስት የመጨረሻ ጥይቱን ተኮሰ!!
ሕዝበ-ሙስሊሙ ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄውንካቀረበ ጊዜ ጀምሮ መንግስት በእጁ ያሉትን ጥይቶች ወርውሯል፡፡ ወደ መጨረሻአካባቢ ደግሞ ገዳይ ጥይትም ተኩሶ ሰው ገድሏል፡፡ መቼም ሰው መሆናቸው ካልተካደበስተቀር አሰሳ ላይ የተገደሉት ወንድሞቻችንን የሞቱት በመንግስት ጥይት ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ መንግስት በዛሬው የራዲዮ ፋና ፕሮግራምም የመጨረሻውን ጥይት ተኩሷል-ኡስታዛችንን እንደ አይን ብሌናችን የምናየውን ዶ/ር ኢድሪስን ወርውሮብናል፡፡ ዶ/ር ኢድሪስ ኡስታዛችን፣ ታላቅ ወንድማችን መሆኑ የማይካድ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት የተነሱጉዳዮችን አንዳ በአንድ ለማየት በዚሀ አንድ ጽሁፍ ከባድ ነው፡፡ ሆኖም፤ የአጭር አጭር በሆነ መልኩ እንወቃቀሳለን፡፡
የዛሬው የራዲዮ ፋና ፕሮግራም ዋነኛ አጀንዳ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ወቅታዊ ሙቀት ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው፡፡ ሆኖም፤ የሙስሊሙ ህብረተሰብን ህጋዊና ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በተራ ፕሮፓጋንዳ እና የመንግስትን ‹‹ሆደ-ሰፊነት›› በመስበክ ይሟሽሻል ማለት ስህተት ነው፡፡የመንግስትን ሆደ-ሰፊነትማ የአወሊያ መስጂድ ሚንበርና መስኮቶች ይመሰክራሉ፡፡ የመንግሰትን ሆደ-ሰፊነትየተደበደቡ፣ ያለ ወንጀላቸው ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው በየእስር ቤቱ እየማቀቁ ያሉ ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ ምንድነው የመንግሰት ሆደ-ሰፊነት መገለጫው? የኢቲቪ የሐሰት ፕረግራሞች? ወይስ የግዳጅ ሰልፎቹ? እስቲ ጋዜጠኛ ብሩክ በነካ እጅህ ሠፋ ያለ ዳሰሳ ሥራበት፡፡
ባላጠፋነው ጥፋት ባልወረወርነው ድንጋይ ‹‹ባስ ሰባሪዎች፣ የህዝብ ንብረት አውዳሚዎች›› መባላችን ነው? ያልተመታውን ፖሊስ ‹‹ተቀጠቀጠ›› ብሎ በሐሰት ማውራት? የቤንሻንጉልን ነዋሪ የአዲስ አበባ ብሎ የሐሰትና የዛቻ ናዳ ማውረድ ነው? ስለ መንግሰት ሆደ-ሠፊነትማ የንጹሃን ደም የፈሰሰባቸው የአራተኛ ፖሊስ ጣቢያና የሠንዳፋ ግቢ ወለሎች ምስክር ናቸው፡፡ መንግስት በሐይማታችን ጣልቃ ሳይሆን ላይከፊት ለፊት ከገባ በኋላ የተዘጉት ኢስላማዊ ማህበረራትና ኤን ጂ ኦዎችስ የመንግስትን ብስለትና ቻይነት ይነግራሉ ሊባል ነው? ብቻ መንግስት እውነትም ሆደሰፊ ነው¡¡¡ ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ አለ ይባላል እስቲ ሌላው ቀርቶ የስም ማጥፋት ዘመቻውንና የሐሰት ድራማውን አቁሙትና እንይ፡፡
ዛሬ ያየነው አስቂኙ ነገር ደግሞ የቀበሌ ምርጫ ‹‹ሳይንቲፊክ›› መሆኑን ማብራሪያ ማግኘታችን ነው፡፡ እናመሰግናለን ሳይንቲስቶቻችን፡፡ ከሁሉ በፊት ምርጫው ፍትሃዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ቃል መገባቱን ብንለምደውም ‹‹ከክፉ ንግግርና ማስፈራርያ ይሻላል›› ብለን እናልፈዋለን፡፡ ምርጫው በቀበሌ ቢሆን ባይሆን መወሠን ያለበት ህዝበ-ሙስሊሙ ነው፡፡ ዛሬ ስለ ምርጫው በራዲዮ ፋና የተነገረን የምንወደውን፣ የምናደምጠውንና ቢቆጣን የምደነግጥለትንሰው ባካተተ መልኩ ከመካሄዱ ውጪ እስከዛሬ ሲነገረን የኖረው ነው፡፡ እነሱየነገሩንን ደግመው ደጋግመው ይነግሩናል፡፡ የእኛን ሐሳብ ግን ለመስማት ፈጽሞ ዝግጁ አይደሉም፡፡ እነሱየምናውቀውን ነገር ነገሩን፤ እኛ ግን እንንገራችሁ ያልናቸው የማያውቁትን ነው፡፡
ኮሚቴዎቻችንን መስጂድን ማዕከል ያደረገው ምርጫ ምን ያህል ሳይንቲፊክ እንደሆነ ማስረዳት እድሉን ከነፈጉ በኋላበራሳቸው ራድዮ ‹‹ቀበሌን ማዕከል ያደረገው ምርጫ ሳይንቲፊክ ነው›› እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ይደናነቃሉ፡፡ ሰዎቹ ቀበሌን መሠረት ያደረገው ምርጫ ሳይንቲፊክ ነው ያስባላቸው ነገር አንድ ነገር ብቻ ነው ይኸውም አስቀድሞ ተዋቅሮ ካለቀው የመንግስት መዋቅር ጋር ተስማሚ ስለሆነ ነው፡፡ ሌላ ምን ምክንያት አቀረቡ? የተነሱት ምክንያቶች ሁሉ ምርጫውን መስጂድ ከማድረግ የማያግዱ ‹‹ሠነፍ ምክንያች›› ናቸው፡፡ አንድም ውሃ የሚያነሳ ምክንያት አላገኘንባቸውም፡፡ እኛ ግን ምርጫው መስጂድ የመካሄዱን ሳይንሳዊነት ማስረዳት የሚችሉ ነገሮች ነበሩን - ለመስማት አልፈለጉም እንጂ፡፡መስጂድ ማዕከል ያደረገ የመጅሊስ መዋቅርችግር አለበት፤ የክርስቲያን ወገኖቻችን አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናትን ማዕከል ያደረገው አወቃቀር ግን ችግር የለበትም፡፡ በምን መስፈርት?
ቆይ ለመሆኑ ከሁሉም የእምነት ተቋማት በተለየ ሁኔታ የኛ መጅሊስ ብቻ የመንግስትን አወቃቀር እንዲከተል የሚደረገው ለምንድን ነው? እስከዚህም እኛ የራሳችንን መጅሊስ አወቃቀር በተመለከተ በአግባቡ አጥንተን የማናስቀምጥ ነፈዝ አደረጉን እንዴ? ለነገሩ መጀመሪያም ይህ ሁሉ ነገር ውስጥ መንግስትንም እኛንም ያስገባን (የባለስልጣናቱ ጥላቻ እንዳለ ሆኖ) መንግስት ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ያለው ንቀት ነው፡፡
የፌደራል ጉዳዮቹ አቶ ሙልጌታና ሌሎችም ‹‹ምርጫው ላይ መንግስት እጁን አያስገባም፡፡ ሁሉም ሙስሊም መመረጥ ይችላል›› ብለውናል፡፡ ታዲያ ምነው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ‹‹የኛ ሠው ደጋፊያችን፣ የነባሩ እስልምና ተከታይ እንዲመረጥ አድርጉ›› እያሉ ለበታች መስሪያ ቤቶችና ሠራተኞች ትዕዛዝ ማውረዳቸውን ማስቆም አቃታችሁ? ‹‹ዑለማ›› ምክር ቤቱስ መመረጥ ያለበት የነባሩ እስልምና ተከታይ ብቻ ነው በቴሌቪዥን እንዲያውጅ ለምን ተደረገ?
እስቲ አስቡት ምርጫው መስጂድ ይካሄድ የሚለውን ህዝብ የወከሉ ሠዎች ያለ ወንጀላቸው እጅግ አደገኛ በሆነው የጸረ-ሽብር አዋጅ ካሰሩ በኋላ የራሳቸውን ሐሳብ ያለማንም ከልካይ ለማጠጣት ሲሞክሩ ምን ይባላል?
በመጨረሻም ለመንግስትም ለሚዲያዎቹም ማስተላለፍ የምንፈልገው ነገር አለ፡፡ ይኸውም፤ እኛ ጀብደኞች ወይም ከጀርባችንየተደበቀ አጀንዳ የለንም፡፡ ተራ መድረቅረቅም አንፈልግም፡፡ መወያየት የሚባለውን ነገር ጠይቀን አጥተናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን (ጤናቸው ተመልሶ ለማየት ያብቃን) ለማነጋገር ስንቴ ጠየቅን? ችግሮችን በውይይት ለመፍታትም ችግር የለብንም፡፡ ሽምግልናውም እንዲሳካ መልካም ምኞታችን ዱዓችንም ነው፡፡ ለጊዜው ግን አጀንዳችን ከዚህ የሚከተሉት መሆናቸውን ለማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡
1. ሙቀታችን ሊቀዘቅዝ የሚችለው ሶስቱም ጥያቄዎች ሲመለሱ ኮሚቴዎቻችንም ሲፈቱ ብቻና ብቻ ነው፡፡
2. ዛሬ እንደተደረገው ሁሉ ‹‹ምርጫው በመስጂድ ይሁን›› የሚለው ህዝበ-ሙስሊምም የሃሳቡን ሳይንሳዊነት እንዲያስረዳ እድል ስጡት፡፡ ስህተት ከነበርን በህጋዊዎቹ ኮሚቴዎች በኩል የሚነገረንና ይሆናል፡፡
3. እስካሁን ትኩረት ለመስጠት የተሞከረው የምርጫ ቦታውን ነው፡፡ የተቀሩት ጥያቄዎችስ የመንግሰት አህባሽን የመጫን ሩጫስ? መልስ የሚፈልጉ ናቸው እኮ፡፡
እዚህ ጋር ይብቃን:: አላህ ቸር ያሰማን!!!

No comments:
Post a Comment