Sunday, August 5, 2012


የሐረርሙስሊሞች ጉዳይ
እንደሚታወቀው ሙስሊሙ የመረጥኳቸው የመጅሊስ አመራሮች ይመረጡልኝ የሚል የመብት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ይህን ተያይዞ ግፍ እየተፈፀመበት ያለን ሙስሊም ቤት ይቁጠረው፡፡
በሀረር እስካሁን ድረስ ሙስሊሙ ረብሻ እንዲፈጥር እየተፈለገ ቢሆንም አላህ ፍቃድ ረብሻ አልተፈጠረም:: ምንጮቻችን እንደዘገቡት አሁን ግን ሙስሊሞች ጠላቶች ሀይለኛ ሴራ ተጠንስሶ ይህንንም ለመተግበር ቀን ቆርጠዋል፡፡ መንግስት ሚፈልገውን ሙስሊም እንዲሁ በባዶ መሬት አያስርም መጀመሪያ ምክንያት ይፈጥርለታል:: በፖለቲካው አለም እንደሚባለው "ማጥቃት በምትፈልገው አካባቢ ረብሻን ፍጠር፡፡ ምትፈልገውን አካል ለይተህ ካወጣህ በኋላ ዳኛ መስለህ በመግባት ለፈጠርከው ችግር መፍትሄን አበጅለት፡፡" በሀረርም ይህንን የፖለቲካ ቲያትር ለመተግበር ተዘጋጀቷል፡፡
 
ምን እንደተጠነሰሰ በመቀጠል ልግለፅላችሁ፡፡
ጀጎል ያሉ ሙስሊሞችን እና አራተኛ እና ከዛውጭ ያሉ ሙስሊሞችን እንዴት እናፋጃቸዋለን ሲሉ ስብሰባ አደረጉ
የሚከተለውንም መንገድ ቀን በመቁረጥ አፀደቁ

1.
ጀጎል ባሉ ሙስሊሞች እና አራተኛ እና አካባቢው ባሉ ሙስሊሞች መሃል የሀሳብ ልዩነት አለ::የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሞችን ለመለያየት በሚጠቀሙበት ስያሜ መሰረት ጀጎሉ ሱፊያ ሲሆን አራተኛ ሰለፊያ/ውሀቢያ ናቸው(ይህንን መከፉፈያ መጠሪያ እኛ ሙስሊሞች የማንቀበለዉ መሆኑ ይታወቃል)

2.
አሁን በመንግስት ውሀብያ አክራሪነት ተፈርጇል

3. የጀጎል ሱፊያ እና ሰለፊያውን ማጣላት እና ምንፈልጋቸውን ሰዎች ማሰር አለብን ፡፡

ይህንንም አላማ ለማስፈፀም የሚከተሉት መንገዶች ተጠንስሰዋል

1.
በጩቤ የታጠቀ 300 በላይ ሀይል አደራጅተዋል
2.
በጃሚአ መስጊድ ሙስሊሙን በመምሰል ይገባሉ
3. እዛ ውስጥ የሚገኘው ሙስሊም ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ
4.
ወዲያውኑም እነዛ እንዲፈፅሙ ትእዛዝ የተሰጣቸው
ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
5.
የሰለፊያ መሪዎች ናቸው ያስታጠቁን ሲሉ ይመሰክራሉ
6.
የሰለፊያ መሪዎች ተብዬዎች እንዲታሰሩ ይደረጋል፡፡

ይህ መንገድ ሁለት የፖቲካ ትርፍ ያስገኝላቸዋልየሚፈልጉትን አካል ነጥሎ በማሰር ውሃቢያ/ሰለፊያ ተብሎ የተፈረጀውን እንቅስቃሴ ማዳከም እንዲሁም አንዱን የወገነ በመምሰል አንዱን ማጥቃት በጀጎል ሱፊያ እና ሰለፊያ በተባለው ሙስሊሞች መካከል የከረረ ጥላቻ እስከ ምን ጊዜውም መፍጠር፡፡
ይህ መረጃ እንዳይወጣ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ ውድ ሙስሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህን መረጃ ላልሰማ በማሰማት የሙስሊሞች ደም በዚህ በተከበረው ወር እንዳይፈስ ኢስላማዊ ግዴታችንን እንወጣ
 " አንድ ሰው የአንድ ወንድሙን ደም ካፈሰሰ የሰውን ልጅ በሙሉ ደም እንዳፈሰሰ ይቆጠርበታል ፡፡ አንድ ሰው የአንድ ሰው ህይወትን ካተረፈ የሰውን ልጅ በሙሉ እንዳዳነ ይቆጠርበታል፡፡"( አልማኢዳህ 32)

No comments:

Post a Comment