by Meranu Habibti
ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ዘጋቢ ጌታቸው ተድላ” እውነቱ ይህ ነው”
በቅድሚያ ለዚህ ፅሁፍ አንባቢዎች በሙሉ ልባዊ የሆነ ሰላምዬ ባላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡ብዘገይም ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች እንኳን ለኢደልፊጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ፡፡ከኢድ ሰላት መልስ እንደሌሎች ሁሉ እኔም የኢድ ሰላትና ሰላማዊ ተቃውሞው በሰላም እንደተጠናቀቀ ፖስት አድርጌ በኢዱ እለት የነበረውን ድባብና የህዝቡን ስሜት በተመለከተ አጭር ፅሁፍ ለማቅረብ (በተለይ ከሃገር ዉጭ ያሉ ኢትዮፕያውያን ስለጠየቁኝ) እንደምሞክር ቃል ገብቼ የነበረ ቢሆንም በግል ችግር ምክንያት ሁኔታዎች አልተመቻቹልኝም ነበርና ቃል በገባሁት መሰረት ለማቅረብ ባለመቻሌ ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ፡፡
ለዛሬ ግን ዋነኛ የፅሁፌ አላማ አንዳንድ የሃገርና የውጭ ሚድያዎች ለኢድ በዐልና ተቃውሞ የወጣውን ህዝብ ብዛት ቁጥር አሳንሰው ሲዘግቡ በመስማቴና በማየቴ እርምት እንዲደረግበት ለመጠቆም ነው፡፡በዚህ ፅሁፍ ላይ ስህተት ፅፌ ከሆነ በማስረጃ እንድታርሙኝ እየጠየቅሁ ወደ ሃሳቤ ልግባ፡፡መቼም የዘንድሮው ኢዳችን ከመቼውም ግዜ በላይ ደማቅና ታሪካዊ እንደሆነ ሁላችንም የምንመሰክረው ነው፡፡በርግጠኝነት ሙስሊሙም ሆነ ሙስሊም ያልሆኑ ፍትህ ናፋቂ ኢትዮፕያውያን ኢዱን በጉጉት፣በፍርሃትና በጭንቀት ስሜት ሆነው ነበር ሲጠብቁት የነበረው፡፡ እዚህ ጋር እንዳውም ሳልጠቅስ የማላልፈው ነገር አንድ ሙስሊም ያልሆነ ኢቶፕያዊ በኢድ ዋዜማ ላይ በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ ፖስት ያደረገውን መልእክት መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡”እግዚያብሄር ሆይ የነገውን የሙስሊሞች በአል ሰላም አድርግላቸው፣የሚወራው ሁሉ ያስፈራልና በስታዲየሙ ፀሎታቸው ላይ አብራሃቸው ሁን”የሚለውን የመልካም ምኞቱን በልእክት መልቀቁ ለሙስሊም ወገኖቹ ያለውን ተቆርቋሪነት የሚያሳይ ሲሆን ጭንቀቱንም አብሮ ገልፆታል፡፡በርካቶችም ተጨንቀው የነበሩ ወገኖች በዋዜማው እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኋላ ስግደቱ ስታዲየም መሆኑን ሲረዱ “እሱ አንድዬ በሰላም ይመልሳችሁ”የምትለዋ ምርቃት ምን ያህል ለሙስሊሙ ወገኖቻቸው እንደተጨነቁ አመላካች ነበር፡፡ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አመት ሊሞላው ቢበዛ የ2 ወር እድሜ የቀረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ምንም አይነት ምላሽ ባለማግኘቱና የመንግስት ጣልቃ ገብነት ከመቸውም ግዜ በላይ በመታየቱና ሙስሊሙም ተቃውሞውን አጠናክሮ በመቀጠሉ ያለውን ፍጥጫ ከግምት በማስገባታቸው ነበር ጭንቀቱ የተፈጠረው፡፡ነገሩን እንዳይረግብ ካደረጉት ዋነኛ ምከንያቶች ደግሞ የሙስሊሙ ኮሚቴዎችና የሃይማኖት አባቶች መታሰራቸው፣ጭራሽ በመንግስት ድጋፍ ሰጪነት ዜጎች በካድሬዎች እየተገደዱ(ሙስሊም ያልሆኑትንም እንደሆነ ልብ ይበሉ) የሙስሊሙን ተቃውሞ ተቃወሙት፣ተቃውሞ አድራጊዎቹን አይወክሉንም በሉ፣አላማቸው ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ነው ወዘተ የሆኑ የተሳሳቱ ፕሮፖጋንዳዎችን መልቀቅና የግዳጅ ፌክ ሰልፎችን በማስወጣት ጥያቄው የጥቂቶች እንደሆነ ለማስመሰል የሚችለውን ሁሉ እያደረገ መታየቱ ነው፡፡መንግስት ለሃገር ልማት ላቡን ጠፍ አድርጎ ከማሰብና ከመስራት ይልቅ በሃገሪቱ ልማት ዙሪያ እጅና እግሩን አጣጥፎ ተቀምጦ አቅሙን ሁሉ የሙስሊሙ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ መዳከሩን የመረጠው ይመስላል፡፡ከዚህ በመነሳት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመንግስትንና ተለጣፊ ህገ ወጥ የመጅሊስ አመራሮችን(የዑለማ ምክርቤት ተብዬዎችንም ይመለከታል) የሙስሊሙ ማህበረሰብን ሰላማዊ ተቃውሞ የጥቂቶች ተቃውሞ ብቻ በማስመሰል አለምን ለማደናገር ሲጥሩ ስለነበር እነሱን ከማጋለጥ አንፃር የኢዱ ቀን ለሙስሊሙ ወሳኝና የምትጠበቅ ቀን ነበረች፡፡እንደተጠበቀውም አልቀረ በመላው ኢትዮፕያ ከእቅድ በላይ በሆነ ሁኔታ ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጓል፡፡እኔ በበኩሌ የዚህ ትውልድ አባል ስላደረገኝ እጅግ ኮርቻለሁ፣ተደስቻለሁ፡፡በዚህም ምክንያት አላህን ከልቤ አመስግኘዋለሁ፡፡እናንተስ?ተቃውሞውን በተመለከተ ደግሞ እጅግ ጨዋነትና ስልጡንነት የታየበት፣ተፈላጊው ግብ የተመታበት ሆኖ ነው የተገኘው፡፡ከ1997 በኋላ ተቃውሞ አስተናግዳ የማታውቀው መዲናችን አዲስ አበባ ለኢድ እለት ግን ከአዲስ አበባ አልፎ ባብዛኛው የሃገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ ሊባል የሚችል ተቃውሞ ለማስተናገድ ተገደዋል፡፡በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ የተቃውሞው ደረጃ እጅግ ከፍተኛ የነበረና ለረጅም ሰዐት የቆየ ነው፡፡ከ2.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ምእመናን በተገኙበት የተቃውሞ ሂደት ያለምንም ልዩነት ህዝቡ አንድ አይነት ተቃውሞ ሲያሰማ ነበር፡፡ኢስላም ሰላም መሆኑን የሚያመለክት ነጭ ወረቀት በማውለብለብ ተክቢራ ለረጅም ደቂቃ የተባለ ሲሆን ከዛ በመቀጠል ድምፃችን ይሰማ ፣ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ምርጫችን በመስጅዳችን፣ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫ የለም፣አሸባሪ አይደለንም፣ይሄ ነው እውነቱ፣መንግስት ከሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ ገብነት እጁን ያንሳ ፣ሀስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል ፣ወዘተ መፈክሮች ህዝቡ ወደቤቱ እስኪበተን ድረስ ቀጥሎ ውሎ ነበር፡፡ከዚህ በተጨማሪም የሚወዳቸውንና የሚያከብራቸውን የጀግኖቹን ኮሚቴዎቻችንን ፎቶዎችን በባነር በማሰራት በኣደባባይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡አልሃምዱሊላህ ህዝቡ በሰላም ዐላማውን አሳክቶ ተመልሷል፡፡በዚህም
1)”ጥቂቶች ናቸው” እያሉ አለማቀፉን ማህበረሰብ በመንገስት ጋዜጦችና በETV ሲያደናግሩ ለነበሩ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ የህገ ወጦቹን የመጅሊስና ዑለማ ምክር ቤትን ፐሮፖጋንዳ ሰብስቦ ገደል ከቶታል፡፡
2)እውነቱን ለዐለም አሳይቷል፡፡
3)ከዚህ በኋላ በመንግሰትም ሆነ በዑለማ ምክር ቤት ደረጃ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ በተመለከተ ለሚሰሩት የተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ እምነት እንዲያጡ ሆነዋል፡፡
4)ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለስግደት ሲወጣ ተቀጣሪ ካድሬዎችና ጥቂት በዒዱ ቀን በድራግ የደነዘዙ ሙናፊቆችን አስርጎ በማስገባት (በእለቱ በጫትና መጠጥ ወስደው በመምጣት አላስፈላጊ ቃላት ሲናገሩ የነበሩ ጠብ ያለሽ በዳቦዎች እንደነበሩ ታይተዋል)ትርምስ ለመፍጠርና የተቃውሞውን አላማ ለማሳት ቢሞክሩም በአላህ እርዳታና በህዝቡ ንቃት ተቃውሞው ለአለም ተምሳሌት በሚሆን መልኩ በሰላም ተጠናቋል፡፡ኢስላም ሰላም መሆኑን ለዐለማቀፉ ማህበረሰብ አሳይቷል፡፡
እንግዲህ በዚህ መልኩ የነበረውን የኢድ አከባበርና የተቃውሞ ሂደት በተመለከተ የተለያዩ የሀገር ውሰጥና የውጭ ሚዲያዎች የዘገቡት ሲሆን የጀርመኑ የአማርኛ ሬድዮም(የDoce Welle) አንዱ ነበር፡፡የጀርመን ሬድዮ አማርኛ ክፍል ከአዲስ አበባ የዘገበው ጌታቸው ተድላ ትንሽ ከሙያ ስነ ምግባር ያፈነገጠ የዘገባ ስህተት ሰርቷል ብዬ በማሰቤ ነው ይህን ለመፃፍ ያነሳሳኝ፡፡ጌታቸው ተድላ ህዝቡ ተቃውሞ ማሰማቱን አምኖ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገኘውን ህዝብ ቁጥር ግን ልክ እንደ አዲስ ዘመን ጋዜጣና ኢቲቪ የህዝቡን ቁጥር ለማሳነስ ሞክሯል በዘገባው ላይ፡፡በሱ አገላለፅ እንዲህ ነበር ያለው“…….ዘንድሮ በአሉን ለማክበር በስታዲየም የተገኘው ህዝብ ከባለፈው አመት በአንፃራዊነት ሲታይ ቀንሶ ታይቷል……”ጉድ ነው ይህን የዘገቡት የጋዜጠኝነት ሙያ ስነምግባር ምናቸውም ላልሆነው የመንግሰት ጋዜጠኞች ዘግበውት ቢሆ ኖሮ ምላሽ ለመስጠት ባልሞከርኩኝ ነበር፡፡ነገሩ የመጣው ግን ፕሮፌሽናል ባለሙያ በመቅጠር ከሚታወቁት በአውሮፓ ከሚገኝ የሚዲያ ተቋም ከአንዱ በመሆኑ እንጂ፡፡በዘገባው ላይ ”……….ህዝቡ ከባለፈው አመት በአንፃራዊነት ሲታይ ቀንሶ ታይቷል……” የምትል ፖለቲካዊ ሃረግ ለጨመርክባት ጋዜጠኛው ጌታቸው ተድላ እውነቱን በተመለከተ አለቆችህ Vedeoውን ከyoutube ላይ አይተው ምን ያህል ሃሰተኛ ዘገባ እንደሰራህ ተመልክተው እንደሚገስጡህ እምነቴ ነው፡፡አንተም ብትሆን ይቅርታ ብትጠይቅ መልካም ነው፡፡ለምን መሰለህ አንተም የጥቂቶች ተቃውሞ ነው ለማለት የፈለክ ያስመስልብሃልና ነው፡፡እንደዛ ለማለት ደሞ ተመልሰህ ETV እና አዲስ ዘመን ላይ መቀጠር አለበለዚያ ደግሞ የመንግስት ሹመኛ መሆን ይጠበቅብሃል፡፡አለም ትኩሱን እውነት በአይኑ አይቶ እያጣጣመ ባለበት ሰዐት አንተ ግን ተሳስታችኋል እያልክ ነው፡፡እንዴት ነው ጌታቸው ከእውነት አፈንግጠህ፣ከጋዜጠኝነት ስነምግባር ወጥተህ ስትዘግብ እውነት አምነህበት ወይስ ሰዎች እንደሚያጉረመርሙት ከቀጠረህ ተቋም እውቅና ውጭ ያልሆነ ነገር ውስጥ ገብተህ ነው?ምላሹን ላንተው አተወዋለሁ፡፡በዚህ ዘመን እውነት መደበቅ እንደማይቻል ግን ከETV እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ በተሻለ እውቀቱ ይኖርሃል የሚል እምነቱ ነበረኝ፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰላማዊ ተቃውሞው ላይ ተገኝቶ በነበረው ህዝብ ቁጥርን በተመለከተ ሰኞ እለት የወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አሁንም ጥቂቶች ተቃወሙ ያለ ሲሆን ከኛም ውስጥ አንዳንዶቻችን አሁንም በቁጥር ግምት ላይ ጥሩ እንዳልሆንን አንዳንድ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ለዚህ ማሳያ እንዲሆነኝ ደግሞ ሰኞ ምሽት 3 ሰዐት ላይ በVOA የአማርኛ ፕሮግራም ላይ የሙሰሊሙን የተቃውሞ ዉሎ በጥሩ ሁኔታ ለሬድዮ ጣቢያው ሲያስረዱ የነበሩት ወንድም(አቀራረባቸውን ከልቤ ወድጀዋለሁ አላህ ምንዳቸውን ይክፈላቸው) ቁጥሩ ላይ ግን በተደጋጋሚ “….በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ….”ሲሉ ተደምጠዋል፡፡(ስሰማው ተሳስቼ ከሆነ እታረማለሁ ግን በሚሊዮን እንዳሉ እርግጠኛ ነኝ)በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት በሚል ቢተኩት ይሻል ነበርም ባይ ነኝ፡፡እኛኮ መንግስት “ጥቂቶች” እያለ ለማሳነስ የሚጠቀመውን ፐሮፖጋንዳ ለምን እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡መንግስት የቁጥር ግብግብ ውስጥ ሲገባ እኛ ደግሞ ጥቅሙን ዘንግተን መለሳለስ የለብንም ሃቁ ላይ፡፡እርግጥ ነው እንኳን ሚሊዮኖች ጥያቄ ጠይቀው አይደለም “መቶዎችም ” ቢጠይቁ ምላሽ መኖር አለበት፡፡የህዝብ ጥያቄ በሚከበርበት አገር ብንሆን ኖሮ ጥያቄያችን ምላሽ አግኝቶ እኛም ይሄኔ ስንት ለሃገር በሚጠቅም ስራ ውስጥ ተጠምደን ነበር፡፡አለመታደል ሆነና የኛ ሃገር ለዚህ አልታደለችም፡፡ስለዚህ በኔ እምነት ያለማጋነን በእሁዱ የኢድ ተቃውሞ ከ 2.5ሚሊዮን እስከ 3ሚሊዮን የሚደርስ ቁጥር ያለው ህዝብ ተገኝቶ ነበር ለማለት እችላለሁ፡፡ይህን ስል ደግሞ ስሜታዊ ገማች ሁኜ እንዳይመስላቸሁ፡፡ለዚህ ማመሳከሪያ ያደረኩት በ1997 ቅንጅት በጠራው ተቃውሞ ላይ የተገኘው ህዝብ 2 ሚሊየን የሚጠጋ እንደነበር በዚህ አመት ሚያዝያ መጨረሻ ላይ ወጥቶ በነበረ አንድ የነፃው ፕሬስ ጋዜጣ ላይ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡እንግዲህ 2 ሚሊዮን ድረስ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ህዝብ እንበለው በቅንጅት ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ከነበር ያኔ ይሄን ያህል ቁጥር ተገምቶ የነበርው ተቃዋሚ ሰልፈኛ የት ድረስ ደርሶ ነበር የሚለውን ማየት ነው፡፡2 ሚሊዮንና ከዛ በላይ ተብሎ ግምት የተሰጠለት የቅንጅቱ ሰልፍ ህዝቡ የነበረባቸውን የመጨረሻ መዳረሻዎች ቦታ ካየን እሁድ ተከብሮ በዋለው ኢድአልፈጥር በዐል ላይ ተገኝቶ ተቃውሞውን በአደባባይ የገለፀው ህዝብ ደግሞ የነበረበትን መዳረሻዎች እንይ፡፡ከወደ ጦር ሃይሎች ልደታን አልፎ ተሰግዷል፣ከቦሌ እስከ መስቀል ፍላወር፣ከ22 ማዞሪያ እስከ ባምቢስ አልፎ ኡራኤል ቤተክረስቲያን መዳረሻ፣ከፒያሳ ለመጡ እስከ በኒ መስጂድ ድረስ ተሰግዷል፣በቄራ ገነት ሆቴልን አልፎ ሳርቤት፣በግዮን አልፎ ወደ ሸራተን አዲስ፣ወደ ካዛንቺስ ወዘተ ባሉ ቦታዎች ተሰግዶባቸው ተቃውሞም ተካሂዶባቸዋል፡፡የቅንጅቱን ሰልፍ እጥፈ ሊሆን የሚችል ህዝብ ተገኝቶ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተገኘ ተብሎም መታለፍ የለበትም፡፡ከ2.5 እስከ 3 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ነው የተገኘው፡፡በኔ እድሜ ታሪክ ደግሞ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ህዝብ በስቴዲየም ተገኝቶ ሲሰግድ አላየሁም፡፡ታዲያ የጀርመኑ ዘጋቢ ጌታቸው ተድላ ከየት አምጥቶ ነው በአንፃራዊነት ከሌላው ግዜ የህዝቡ ቁጥር ቀንሶ ታይቷል ማለቱ? እስከ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተቃውሞ አሰማ ለማለት ቀፈፈው ይሆን? መቸስ እሱ ከቀፈፈው ምን ይደረጋል ብለን እንለፈው፡፡!
በመጨረሻ ግን አንድ ነገር ብዬ ላብቃ፡፡እንደ መንግስት ሴራና ዝግጅት ከሆነ ተቃውሞው በሰላም ለመጠናቀቁ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል አንደኛው የህዝቡ ቁጥር ከልክ በላይ መሆን ነው ባይ ነኝ፡፡ህዝቡ በበዛ ቁጥር መንግሰት በየቦታው ሸሽጎ ያስቀመጣቸው አድማ በታኝ ፖሊሶቹ በህዝቡ እየተከበበ በመምጣቱ ህዝቡን ለማጥቃት ቢሞክሩ እንኳን የማጥቂያ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ፌዴራል ፖሊስ አባላቶቹ ለቅኝት የመረጧቸው ቦታዎችና ህንፃዎች እንኳን ሳይቀሩ ተከበዋል፡፡በዋነኝነት የአላህ እርዳታ ሆኖ የህዝቡም መብዛት ለጥቃት እንዳንጋለጥ አድርጎናል፡፡በተረፈ አስደማሚውንና ሰላማዊውን የሙስሊሙ ፍትሃዊ ጥያቄ ህዝቡ በማያሻማና በማያጠራጥር መልኩ ለመንግስትም ሆነ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ግልፅ አድርጓልና ከዚህ በኋላ መንግስት ድብብቆሹን አቁሞ የህዝቡን ጥያቄ ይሰማል፣ ከህዝቡ ፍላጎት ጋርም የሚሄድ የአቋም ለውጥ ያሳያል ብዬ አስባለሁ፡፡ከዚህ በኋላ የዚህን ሰላማዊና ጨዋ ህዝብ ጥያቄ አለማክበር ወንጀል ነው፡፡ የጠየቅናቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙና ኮሚቴዎቻችንን ጨምሮ የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱ ዱዐ እናድርግ፡፡ከረመዳን ማለቅ ጋር ተያይዞ ዱዐችን መቆም የለበትም፡፡ኮሚቴዎቻችንን አላህ ይጠብቅልን፡፡እኛንም አላህ ይርዳን፡፡በዚህ አጋጣሚ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት መለየት ለቤተሰቦቻቸውና ለህዝቡ መፅናናትን እመኛለሁ፡፡

No comments:
Post a Comment