Wednesday, August 22, 2012

Radio Bilal News August 22, 2012


በቡራዩ ከተማ የመጅሊስ ምርጫ ሊካሄድ እንደሆነ ነዋሪዎች አመለከቱ

በስልጤ ዞን የመጅሊስ ምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩ ተገለፀ

የታሰሩ ሙስሊሞች እንዲፈቱ ሂውማን ራይት ዎች እና ሲፒጄ ጠየቁ

በትላንትናው ዕለት በወሊሶ ከተማ የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ ስብሰባ ተካሄደ

የወለኔ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

በቡራዩ ከተማ የመጅሊስ ምርጫ ሊካሄድ እንደሆነ ነዋሪዎች አመለከቱ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 16/2004
በትላንትናው እለት በቡራዩ ከተማ የመጅሊስ አመራር ምርጫ ሊካሄድ ታቅዶ እንዳልተሳካ ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሞት የታሰበውን የመጅሊስ አመራር ምርጫ እንዳሰናከለው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡
ምርጫውን በተመለከተ ነዋሪዎች በመስጅድም ሆነ ከየመኖሪያ ቤቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መረጃ እንደሌለው ጠቁመዋል፡፡
የመንግስት አመራሮች የመጅሊስ ምርጫውን ህዝበ ሙስሊሙ በማይፈልገው በቀበሌ ለማድረግ መሰናዳታቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ በቀበሌ ድንኳን ቢተከልም ህዝበ ሙስሊሙ ለመምረጥ ፍላጎት እንደሌለው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጅሊስ አመራር ምርጫ የፊታችን ሐሙስ  የመንግስት አመራሮች በቀበሌ ለማካሄድ  ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በስልጤ ዞን የመጅሊስ ምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩ ተገለፀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 16/2004
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የመጅሊስ ምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩ ተገለጸ ፡፡ በወረዳው አስተዳደር እና ድርጅት ጽ/ቤት የሚመራው የምርጫ ቅስቀሳ ህ/ሰቡ እንደማይቀበለው አስታውቀዋል፡፡ የመጅሊስ ምርጫ ቅስቀሳ የሚካሄደው ቤት ለቤት በመዘዋወር ፊርማ በማሰባሰብ እንደሆነ ተገልፆዋል፡፡
የምርጫ ቅስቀሳው አብዛኛው ህዝብ ያወገዘው ቢሆንም አንዳንድ  አዛውንት ግን መፈረማቸውን የወረዳው ነዋሪዎች አሳውቀዋል፡፡ ይህው  በትላንትናው  ዕለት የተጀመረው የቅስቀሳ ፊርማ ክርስቲያን ወንድሞችንም ያካተተ እንደነበር ተገልፆዋል፡፡

የታሰሩ ሙስሊሞች እንዲፈቱ ሂውማን ራይት ዎች እና ሲፒጄ ጠየቁ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 16/2004
ሐምሌ 14 በአንዋር መስጂድ ተፈጥሮ በነበረው ግርግር የታሰሩ ሙስሊሞች እንዲፈቱ ሂውማን ራይት ዎች የተባለው ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች መግለጫ ሲያወጣ ሲፒጄ የተሰኘው ዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች ተቆቆርቋሪ ድርጅትም የሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት አዘጋጅ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ ባለፈው ረዕቡ ባወጣው መግለጫ የእስልምና እምነት አስተማሪ የሆኑ ግለሰቦች ክስ ሳይቀርብባቸው ለሶስት ሳምንታት እስር ቤት መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጲያ መንግስት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለሚያነሳው ጥያቄና ተቃውሞ በመመካከር እንጂ በአመፅ ማስቆም መሞከር እንደሌለበት የሂውማን ራይትስዎች የአፍሪካ ሲኒየር ሪሰርቸር ኬን ራውለንስ ገልጸዋል፡፡አክለውም የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሀገሪቱን ህግ ማክበር እንጂ መጣስ የለባቸውም  ብለዋል፡፡ ድርጅቶቹ ኢትዮጲያ የኃይሞኖት መቻቻል የሚታይባት ሀገር እንደሆነች በማመልከት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገሪቱ የሚታየውን ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በወሊሶ ከተማ የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ ስብሰባ ተካሄደ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 16/2004
በትላንትናው ዕለት በወሊሶ ከተማ የመጅሊስ ምርጫን አስመልክቶ ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው ላይ የመንግስት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ውሃብዮች በምርጫ መሳተፍ እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡ የወረዳው ካቢኔ ቤት ለቤት ከመዘገቧቸው ጥቂት ሰዎች በስተቀር በምርጫው ላይ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል ብለዋል፡፡ ምርጫውን አስመልክቶ በመስጂድ መካሄድ እንደማይችልና በቀበሌ መሆን እንዳለበት ከመድረኩ መወሰኑን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

የወለኔ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 16/2004
          የወለኔ ህዝቦች ፓርቲ የሆነው ጥያቄ ከ20 አመት በፊት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ይሁን እና ከነሐሴ 9 ጀምሮ 5የፓርቲው አባላት እንደታሰሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ፋይሰል ገልጸዋል ዘጠና ከመቶ የሆነው የወለኔ ማህበረሰብ ሙስሊም በመሆኑ ጥያቄአቸውን ከአክራሪነት ጋር እንዳያያዙት አክለው ገልፀዋል፡፡ ከታሰሩት የስራ አመራር አካላት ውስጥ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዲ ተማም እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ሰማን ጀማል ይገኙበታል፡፡ አምስቱ የፓርቲው አባላት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ተገልፆዋል፡፡

No comments:

Post a Comment