ይኸው
በታዳጊና ወጣት የአወሊያ ተማሪ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የተጀመረው ሃይማኖታዊና ህገመንግስታዊ መብቶቻችንን
የማስከበር ትግላችን አንድ ዐመት ሊደፍን ከሰባ የማይበልጡ ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል፡፡ የትግላችን ዐይነተኛ ባህሪ
ሰላማዊነት ነው፡፡ ሰላማዊነት ሲባል ህግ አክባሪነትን፣ የሌሎችን ዜጉች ፀጥታና ደህንነትን መጠበቅን እንዲሁም
በጥቅሉ ህግና ስርዐት አለመደፍረሱን ማረጋገጥ ጭምር ነው፡፡ እስኪ ከዚህ አንጻር ያለፉትን ከ290 በላይ ቀናት
በምን መልኩ እንዳሳለፍናቸው እንቃኛቸው፡፡ ገና ከጅምሩ በጀግኖቹና ከዕድሜያቸው በሚልቅ ርዕይ በአወሊያ
እንድንሰባሰብ ግብዣ ባቀረቡልን የአወሊያ ተማሪዎች ጥሪ ከተሰባሰብንና የሃይማኖታችን
መደፈር፣
የእምነታችን በእኩያን መነካት አስቆጥቶን መሪ ኮሚቴዎቻችንን ከመረጥንበት ጊዜ አንስቶ ሁነኛ መርኃችን ሰላም፣
ህግና ስርዐት ማስጠበቅ ነበር፡፡ ኮሚቴዎቻችንም በህዝብ ከተወከሉበት ቀን አንስቶ ሲያንፀባርቁት የነበረውም መርህ
ይህንኑ ነው፡፡ ኮሚቴዎቻችን በህዝብ ሲመረጡ የተሰጣቸው ውክልና በኢትዩጲያ ሙስሊም ህብረተሰብ ስምና ፊርማ
እንዲረጋገጥና ህዝቡም ውክልናውን ህግና ስርዐቱ በሚጠይቀው መልኩ እንዲያጸድቅላቸው ያደረጉት ጥረት ገና ከጅምሩ
ለህግ መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት አመላካች ነበር፡፡ ኮሚቴዎቻችን ከመንግስት አካላት ጋር ውይይትና ድርድር
በጀመሩበት ወቅትም ይህ ህግ አክባሪነታቸው በሰፊው ተንፀባርቋል፡፡ ሳምንታዊ በሆኑት በአወሊያ የተቃውሞ መድረኮችም
ሆነ ኮሚቴው ለሚመለከተው አካል በሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ተገቢውን አክብሮት ለመንግስት በማሳየትና መንግስት ለተነሱት
ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ ባለሙሉ ተስፈኛ በመሆንም ጭምር የተከናወኑ ነበሩ፡፡ ኮሚቴዎቻችን
ሰላም የሚመሩት የተቃውሞና ህግን የማስከበር ሂደት ዐይነተኛ ባህሪ መሆኑን በተገኙባቸው መድረኮች ሳይገልጹ አልፈው
አያቁም ነበር፡፡ ይህ ሰላምን የመሻት ጽኑ ፍላጎት እንዲሁ የላይ የላይ (lip service ) ብቻ ሳይሆን የምር
መሆኑን አሁን እነሱ ካሉበት ሁኔታ እንኳን መገንዘብ እንችላለን፡፡ ኮሚቴዎቻችን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ሙስሊሙ
ህብረተሰብ መብቱን በማስከበር ሂደት የሚገጥሙትን ሰላም አደፍራሽ ክስተቶች (የህብረተሰቡን በፖሊስ መደብደብና
መገደልን ጨምሮ) በሰላምና በትዕግስት ብቻ እንድናሳልፍ ሲማፀኑን ነበር፡፡ ሐምሌ 6 ዐርብ ምሽት በንጹሃን
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ በአወሊያና አካባቢው ፖሊስ አሰቃቂ ግፍ ከፈጸመ በኋላ ኮሚቴዎቻችን በአንዋር መስጂድ
ሐምሌ 7 እና 8 ተገኝተው ያደረጓቸው ንግግሮች ምስክሮች ናቸው፡፡ ከህዝቡ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት
የአንዋር መስጂድ የሐምሌ 8 የሰደቃና አንድነት መድረክ እኛ የቱንም ያህል በደል፣ ግፍና እስራት ከአሁን በኋላ
ቢደርስብን ትግሉን በሰላም ለመቀጠል ቃል እንገባለን የሚል ቃለ መሃላ እንዳስፈፀሙን ፈፅሞ አንረሳውም፡፡
የዚህ ሰላማዊነታችን ሙሉበሙሉ የተቃና መሆን ሂደታችንን የተሳካ አድርጎታል፡፡ ነውጥና ግርግር የምንፈልግ ብንሆን ፤ ሰላምን ማደፍረስ አላማችን ቢሆን ኖሮ ሒደታችን እንዲህ የተዋበ ብዙዎችንም ያስደነቀ ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ የተቃውሟችን የጊዜ ርዝማኔ እንዲሁ አሁን ኢትዮጲያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር አንድ ዐመት ለመድፈን አይንደረደርም ነበር፡፡ ከጊዜው ርዝማኔም በላይ ግን ተቃውሟችንን የገለፅንባቸው ጥበቦችና ያለመታከት ያካሄድናቸው ዘርፈ ብዙ የተቃውሞ መንገዶች አሁንም ቢሆን አንገታችንን ቀናና ከፍ አድግረን እንድንሄድ ምክያኒያት ሆነውናል፡፡ ሰላማዊ የሆነው ተቃውሟችን በሌላው ዐለም non-violent በሚል ከነማርቲን ሉተርና መሃተመ ጋንዲ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቢሆንም የኛ ተቃውሞ ከዐላማውና መርሑ ጀምሮ በብዙ መልኩ በሌላው ዐለም ከሚታወቁት ተቃውሞዎች ይለያል፡፡ ተቃውሟችን ከጨቅላ ህጻናት አንስቶ አረጋዊያንን፤ ከልጃገረዶች አንስቶ ባልቴቶችን ሁሉ በፍቃደኝነት ያካተተ ነበር፡፡ ይህንንም ሂዩማን ራይትስ ዋችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኙ ዝነኛ የሰብዐዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንኳ በሪፖርቶቻቸው መስክረውታል፡፡ አሁንም ጮክ ብለን እንናገራለን- ሰላማዊ ነን! ተቃውሟችን ሰላም በሚለው መርኅ የተቃኘ በመሆኑ ጠላት ቀዶ ሊገባበት የነበረው ሃይማኖታዊ ወንድማማችነታችንም ዳግም ወደማይናድ ግንብ ለውጦታል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ላይም የማይናወጥ እምነት እንድንገነባም ምክኒያት ሆኖናል፡፡
ከምንም በላይ ግን እስካሁን ሰላማዊና የተናበበ የነበረው ተቃውሟችን ከመንግስት በኩል መልስ ባያስገኝልንም የልፋታችንን ፍሬ የምናይበት ጊዜ ግን ሩቅ እንደማይሆን እርግጠኞች ነን፡፡ የኛ ሃላፊነት አቋማችንን፣ በእምነታችን ላይ የሚፈፀምብንን እኩይ ድርጊት በምናምንበት የተቃውሞ መንገድ መግለጽ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ላለፉት 9 ወራት በተገቢ መንገድ አከናወነው፡፡ በዚህ ስራችን ዓለም ተደነቀ፡፡ ብዙዎች በኛ ኩራት ተሰማቸው፡፡ ዓለም የኛ ጉዳይ አሳስቦት እንዲነጋገርበትም ምክኒያት ሆነ፡፡ ከትናንሽ የገጠር ቀበሌዎች አንስቶ እስከ ትላልቆቹ የአገሪቱ ከተማዎች ድምጻችን ከፍ ብሎ ተሰማ፡፡ የአንድነት ዜማችን ሁሉንም ጠራ፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን በአክራሪነት ጠረጠሩን፡፡ በሰላም አደፍራሽነት ወነጀሉን፡፡ በጥቂነትም መነዘሩን፡፡ ለዚህም ቢሆን ግን መልስ እንዳለን ከቀናት በፊት አሳየናቸው፡፡ የታላቁ ወር ፍጻሜ በሆነው የዒድ ሰላት ከጫፍ እስከ ጫፍ በመላው አገሪቱ የሚገኙ ዜጎች በተመሳሳይ ሁኔታና ሰዓት ድምጻችንን እንዲሰሙ አደረግናቸው፡፡ ሰላማዊነታችንን ነጭ ሪባን በማውለብለብ፣ ብዙነታችንን ሚሊዮኖች በመሆን አቋማችን የፀና መሆኑን ጎዳናዎች ላይ በጉልበታችንን በመንበርከክና እንባ ከዐይናችን በማፍሰስ ዳግም አረጋገጥናላቸው፡፡ እባካችሁ ድምጻችንን ስሙ ስንል ተማጸናቸው፡፡ ተደጋግሞ እንደተገለጸው በሶስቱ መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን ያነሳነው ጭብጥ የህገ መንግስትን መከበር ነው፡፡ ይህን ህገ መንግስትን የማስከበር ሃላፊነት ደግሞ የሁሉም ዜጋ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ግን ከማንም በላይ የመንግስትና የፍትህ አካላት ሚና በዚህ ረገድ የጎላ እንደሚሆን ጥያቄ የለውም፡፡ የኛም ሃላፊነት ለሚመለከተው አካል ህግ ተጥሷል፣ ዜጎች ሃይማኖታዊ መብታቸው በጥቂት ሹማምንቶች እየተጣሰ ነው፣ መንግስት ተገቢውን መፍትሄ ይስጠን ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ ይህንንም በተገቢ በልኩ አድርገናል፡፡ አሁንም ተገቢውን ምላሽ ከሚመለከተው አካል እናገኛለን የሚል እምነት አለን፡፡ ይህን ምላሽ ሊሰጠን የሚችለውን አካል (መንግስትን) በበላይነት የሚያስተዳድሩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አሁን በሞት ተለይተውናል፡፡ የመንግስት የሃላፊነት ቦታም ዳግም በሽግሽግ ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በሌላ በኩልም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ሞት በአገሪቱ ከፍተኛ የሀዘንና የስራ መደራረብ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ የሁለቱ ሟች ግለሰቦችን ስርዐተ ቀብር ለማስፈጸምም መንግስት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ይህም ሆኖ ግን ያነሳነውንን ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ዳግም አሁን አስተዳደሩን ለሚረከበው መንግስት እናቀርባለን፡፡
እኛ ኮሚቴዎቻችን ሲያደርጉት እንደነበረው የሚመለከተው የመንግስት አካል የኮሚቴዎቻችንን ከእስር ነጻ መሆንን ጨምሮ ሶስቱን መሰረታዊ ጥያቄዎች እስኪመልሱልን ድረስ ላልተወሰነ ቀናት ተቃውሟችን ጋብ በማድረግ በትዕግስት ለመጠባበቅ ዝግጁነታችንን እናሳያለን፡፡ እነዚህ ተቃውሟችንን ጋብ የምናደርግባቸው ያልተወሰኑ ቀናት አቶ መለስን የሚተካቸው አዲሱ አስተዳደር ጥያቄያችንን ዳግም እንዲመለከትልንና ጥያቄዎቻችንን አጢኖ ምላሽ እስኪሰጠን ብቻ ይሆናል፡፡ በየሳምንቱ ዐርብ የምናደርገው የነበረውን ተቃውሞም በዚሁ መሰረት የቀብር ሥነ-ስርዐቶቹ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈፀሙ ከማድረግ አንጻርና አዲሱ መንግስትም ጥያቄያችንን ለማየት ፋታ እንዲያገኝ ሲባል በጊዜያዊነት መቆም እንዳለበት ለመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እናስታውቃለን፡፡ በቀጣይነት ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን አስፈላጊ የሆኑ መልእክቶችን እንደምናወጣ እየገለጽን እስከዛው ይህንን መልዕክት እንደተለመደው ላልሰሙ ሰዎች በማሰማት ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment