አስቸኳይ ማሳሰቢያ
(ነሐሴ 17 2004)
አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በከባድ የሐዘን ድባብ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በመላ አገሪቱም የሀዘን ቀን ታውጆ ባንዲራዎች ዝቅ ብለው እየተውለበለቡ ዜጎችም የሀዘን ስሜታቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጡ ይገኛሉ፡፡ የዓለም አገራትም ከአገራችን አልፎ አሕጉራዊ የጎላ ሚና በነበራቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሞት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጡ ኢትዮጵያችንም ይህንን ሁኔታ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ምንም እንኳን ባነሷቸው ጥያቄዎች ዙሪያ በተቃውሞ ላይ የሚገኙ ቢሆንም በጠቅላይ ሚንስትሩ ሞት የተሰማቸውን ስሜት እንደማንኛውም ዜጋ ስሜታቸውን ገልጠዋል፡፡ ጥያቄዎቻችን ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት ሙስሊሙ ሕዝብ በዒድ አደባባይ ባሳየው ጠንካራ የአንድነት ስሜትና ድምፅ እስከዛሬ ድረስ ይዘነው የቆየነው ሠላማዊ የተቃውሞ ሂደት ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አስተማማኝ ጉልበት አግኝቷል፡፡ ይህም ጥያቄያችን ተገቢውን ትኩረት አግኝቶና የታሰሩት ወኪሎቻችንም ከዕስር ተለቅቀው እስከምናይ ድረስ ሰላማዊ የተቃውሞ ሒደታችን መላ የአገራችንን ክልሎች ባካለለ መልኩ ይቀጥላል-ኢንሻ አላህ፡፡
ይሁንና አስተውሎት የተሞላበትና በሰከነ ስሜት ታጅቦ በህዝበ ሙስሊሙ እየተተገበረ የቆየው ሂደታችን ዛሬ አገራችንና መላ ኢትዮጵያዊያን ያሉበትን ስሜት ለማስተዋል አይሳነውም፡፡ አሁን ያለው ተጨባጭ የአገራችን ሁኔታ ነገሮችን በጥንቃቄ እና በትኩረት እንድንመለከት የሚያስገድደን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በመላ ኢትዮጵያ ሲደረጉ የቆዩ የተቃውሞ ሂደቶች በዚህ ሳምንት ሊኖሩ አይችሉም፡፡በዚህም መንግስት ልቦናውን ሰብሰብ በማድረግ ሀዘንን ከመወጣት ጎን በጎን ሙስሊሙ ሕዝብ እየወሰደ ያለውን ብስለት እና አስተውሎት የተሞላበትን እርምጃ በሰከነ ስሜት እንዲያጤን እድሉን እንደሚጠቀምበት ተስፋችን የላቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
ሕገ ወጡ የመጅሊስ አመራር በዚህ አጋጣሚ የራሱን አጀንዳ ዳር ለማድረስ ከመንቀሳቀስ ይቆጠባል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ይህ ፍፁም የዋህነት መሆኑን ተገንዝበን መንግስት በዚህ የሀዘን ወቅት ፋታ እንዲያገኝ የበኩላችንን ጥረት እያደረግን ባለበት በአሁኑ ሰዓት መልካም አጋጣሚ ያገኙ መስሏቸው ተንኮል የተሞላበትን ሩጫቸውን በሚስጥር ተግባራዊ ለማድረግ መሯሯጣቸው አይቀርም፡፡ በመሆኑም መላ የአገራችን ሙስሊም ሕዝብ ከዚህ ቀደም በተባበረ አንድነት መጅሊስና ሕገ ወጥ አመራሩ እያደረሱበት የነበረውን መሰሪ ድርጊት በንቃት በመከታተል ውድቅ እንዳደረገባቸው ሁሉ ዛሬም ይበልጥ በመንቃት ድርጊታቸው ሁሉ ከህዝብ ዓይን ስለማይሰወር የደረስንበትን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ተንኮላቸውን በሙሉ ማክሸፍ ይኖርብናል፡፡
ምርጫን በተመለከት ሙስሊሙ ሕዝብ ኮሚቴዎቻችን በታሰሩበት እና ምርጫውም ገለልተኛ ሆኖ በተሰየመ የአስፈፃሚ አካል በመስጂዳችን እስካልተካሄደ ድረስ አንሳተፍም፤ እንዲሁም ይህን ያላማከለ ምርጫ ሳይሆን ቅርጫ ቢካሄድ ምንም ዓይነት ዕወቅና ሊሰጠው እንደማይችል ግልፅ አድርጓል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ነሐሴ 15 በየቀበሌው የምርጫ ኦሬንቴሽን ይሰጣል ተብሎ በ “ኡለማዎች ምክር ቤት” ፀሐፊ ሼኽ ኢዘዲን” በኩል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታወጀ ቢሆንም ይኸው ሳይካሄድ ማለፉ እና በሕዝቡም ጠንካራ የተቃውሞ ድምፅ መቀጠልም “ምርጫ” የተባለው ነገረ በተባለለት ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህ ማለት ግን ሁኔታዎችን በመዘናጋት መተው አለብን ማለት እንዳልሆነ ግንዛቤ ተይዞ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ሁኔታዎችን በዓይነ ቁራኛ መከታተል ይኖርብናል፡፡
በዚህ አሁን ባለንበት የሀዘን ጊዜ ድርጊቶች ይቅርና ከአንደበት የሚወጡ ንግግሮች እንኳ በቀጥታ ያልተፈለገ ትርጉም ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ከፍተኛ እድል ከመኖሩ ጋር በተያያዘ ይዘነው የዘለቅነው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ እና ሕገ መንግስታዊ መሰረቱ የፀና እንዲሁም ምንም ዓይነት ከሐይማኖት አጀንዳነቱ የዘለለ ፍላጎት እንደሌለው ማረጋገጥ ስለሚኖርብን ከያዝነው አጀንዳ ሊያስወጡ ከሚችሉ ንግግሮችና ድርጊቶች እንድንጠነቀቅ እያስታወስን ሙስሊሙ ሕዝብ እንደተለመደው እርስ በራሱ እየተናበበ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡
አላህ ይርዳን፡፡

No comments:
Post a Comment