Friday, August 24, 2012

ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚ ሳይመረጥ በምርጫዉ አንሳተፍም




  • በሀረር ከተማ በኢማን መስጂድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ከጁምአ ሰላት ቡሀላ ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚ ሳይመረጥ በምርጫዉ አንሳተፍም በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ተቃዉሟቸዉን ማሰማታቸዉን ምንጮቻችን አስታወቁ:: በተመሳሳይ ሁኔታም በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞን በዳዌ ወረዳ ከጁምአ ሰላት ቡሀላ ህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎቻችን ይመለሱ በማለት ከፍተኛ ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን ምንጮቻችን አስታወቁ:: አላሁ አክበር!!!
     

    ድምፃችን ይሰማ

    በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ ከጁምአ ሰላት ቡሀላ የዞኑ መጅሊስ ተብየዎች ለህዝበ ሙስሊሙ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ የሞከሩ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ሙስሊሞች በአጠቃላይ ለምርጫዉ ተመዝግበዎል እናንተም አሁን በፍጥነት ተመዝገቡ አለበለዚያ ግን አልመዘገብም ያለ ይታሰራል ይሰቃያልም በማለትለ ለማስፈራራት መሞከራቸዉን ምንጮቻችን አስታወቁ:: ህዝበ ሙስሊሙም ማስፈራሪያዉና ዛቻዉ ሳይበግራቸዉ በከፍተኛ ቁጣ ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫ የሚባል ነገር አናዉቅም!!! ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!! በማለት በከፍተኛ ተክቢራ ተቃዉሟቸዉን ማሰማታቸዉን የአካባቢዉ ምንጮች አስታዉቀዎል:: አላሁ አክበር!!!


  • በወለጋ መጫራ ከተማ ነሐሴ 16 መንግስት ባካሄደዉ የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ አስፈፃሚዎች ምርጫ መንግስት በራሱ የመረጣቸዉ ግለሰቦች በመሆናቸዉ እና የተመረጡት ሰዎችም በጥንቆላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በመሆናቸዉ የአካባቢዉን ሙስሊሞች ወክለዉ ምርጫ አስፈፃሚ መሆን የለባቸዉም በማለት ህዝቡ በራሱ ምርጫ የፈለግነዉን ምርጫ አስፈፃሚ አድርገን መምረጥ አለብን በማለት መንግስት የመረጣቸዉን ግለሰቦች ህዝቡ አልቀበልም በማለቱ እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት 10 ሰዎች መታሰራቸዉን ምንጮቻችን ዘግበዎል:: በተመሳሳይም በበደሌ ከተማ ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫዉን አንሳተፍም ያሉ 15 ሙስሊሞች መታሰራቸዉ ተሰምቷል:: እንዲሁም በአጋሮ ከተማ የመጅሊስ ምርጫን እንዲያስፈፅሙ መንግስት የመረጣቸዉን ግለሰቦች የከተማዎ ሙስሊሞች አንቀበልም በማለታቸዉና ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫዉን አንካፈልም በማለታቸዉ የመንግስት አካላት በየቤቱ እየዞሩ በከፍተኛ ሁኔታ ማህበረሰቡን እያስፈራሩ እንደሚገኙም የአካባቢዉ ምንጮች አስታዉቀዎል::


  • በጎንደር ከተማ የመጅሊስ አመራሮችን ምርጫ ለማካሄድ መንገስት ባዘጋጀዉ 15 የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈፃሚና የምርጫ ታዛቢዎች መመረጣቸዉ ተሰማ:: በሚያስገርም ሁኔታም የምርጫ አስፈፃሚ ተብለዉ ከተመረጡት መካከል በግንባር ቀደምትነት የጎንደር ከተማ የአህባሾቹ ኡለማ ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ሙስጦፉ አሚኑ እና የሳቸዉ ዎና ፀሀፊ የሆነ መሀመድ ሳልህ ይገኙበታል:: ሙስጠፉ አሚኖ የሚባለዉ ግለሰብ በጎንደር የአህባሽ አስተሳሰብ ፊት አዉራሪ ሲሆን በየመስጂዱ በመዞር የኢትዮጲያ ታዎቂ ዳኢ የሆኑትን ኡስታዝ ያሲን ኑሩን, በድሩ ሁሴንን, ሀሰን ታጁን እንዲሁም አለም አቀፍን ዳኢ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ካፊሮች ናቸዉ በማለት በአደባባይ የሚያስተምር ግለሰብ መሆኑን የጎንደር ምንጮቻችን ገልፀዎል::በአሁኑም ወቅት በየቀበሌዉ የነ ሼህ ሙስጠፉን ቡድን (አህባሽን) ያልመረጠ አሸባሪ, ወሀቢይ, ካፊር ፀረ ሰላም ነዉ ወ.ዘ.ተ....... እየተባለ በከፍተኛ ደረጃ ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀዎል:: የጎንደር ወጣት ሙስሊሞች ግን ኮሚቴዎቻችን ከእስር ሳይፈቱ ምርጫ የማይታሰብ ነዉ በማለት በአቖማቸዉ ፀንተዉ እንደሚገኙ ነዉ የጎንደር ምንጮቻችን ያስታወቁት!!!!


 ድምፃችን ይሰማ
በስልጤ ዞን አሁንም ማዋከቡና ማሰሩ ቀጥሏል፡፡ በትላንትናው እለት አቶ ሰላሃዲን የሚባል ወራቤ መናኻርያ የሚሰራ ልጅ ከዚህ በፊት የውሸቱን ድጋፍ ሰልፍ እንዳይወጣ ቀስቅሰሃል ተብሎ ታስሮ ነበር፡፡ አሁንም በጠቅላይ ሚንስተሩ ሞት ተደስተሃል ብለው አሰሩት ፡፡ ወላሂ በጣም ይገርማል መብቱ መሰለኝ እኮ ደስ ቢለው የራሱን አስተሳሰብ በነጻነት ማራመድ ይችላል ተብሎ ህገ መንግስቱ ላይ እኮ ተፏል፡፡ ስልጤ ዞን ማለት ሆድ አምላኩ ሙጅሪም አመራር የተሰበሰበበት ነወ፡፡ ከዚህ ጋር በተያየዘ ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ ከሳንኩራ ወረዳ 14 ልጆች አህበሽን በመቃወማቸው መታሰራቸው ይታወሳል፡፡ ከ14 ልጆች ውስጥ 8 መፈታታቸውና 6 ቱ እስከ አሁን እንዳልተፈቱ ተነግሮዋል፡፡ በመቀጠልም ምርጫውን አስመልክቶ ትላንትና የወራቤ ከተማ ከንቲባ የሆኑት የአቶ ሙርሰል አማን አባት፣ የእህቱ ባል የወራቤ ከተማ ስፖርት ጽ/ቤት የሆኑት አቶ ከድር ሼ /ሙዘይን አባት የሆኑት ሼ/ሙዘይን ሼ/ሰኢድ ከፍተኛ የአህባሽ አቀንቃኝና አመራር እንዲሁም አቶ ከማል አህመድ የሜላት ካፌ ባለቤት የሆኑት ለመጅሊስ ምርጫ መመረጣቸውን ነግሬያችሁ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አስመራጭ ኮሚቴውን በተመለከተ ትላንትና በወራቤ የተመረጡ ሰዎች ስብሰባ የተጠሩና በፖሊስ ታጅቦ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ልክ ድርጅት ላይ ምርጫ ሲደረግ ሰዎች ተዘጋጅተው እከሌን ምረጥ ተብሎ ይዘጋጅና ሰው እጅ ሲያወጣ ለማን ለማን እንደሚሰጥ ማንን እንደሚመርጡ ተነግሮዋቸው ልክ ድርጅት ላይ እንደሚሰሩት የመጅሊስ አስመራጭ ኮሚቴ ማስመረጣቸው ተገልጾል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአብዛኛው የጎጥ አመራሮች/የፖለቲካ አቀንቃኞች/ ተካተዋል፡፡ በጣም የሚገርመው ሃጂ ሻፊ የአቡበከር መስጂድ ኢማም የሆኑት በሰደቃ ፕሮግራሙ ላይ ምርጫ መስጂድ ካልሆነ አንመርጥም ሲሉ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን የአቋም መዋዠቅ ታይቶባቸው ምርጫው በቀበሌ መሆኑን ደግፈው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ እኛ የወራቤ ነዋሪዎችም እንደዚህ አይነት እኩይ ተግባራትን የሚሰሩትን ሁሉ አጋልጦ ማውጣት አለበት፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የኢድ ሰላት በከፍተኛ ተቃውሞ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን በወራቤ ከተማ ግን እነ ሃጂ አብዱልሃዲ ቡርሃን የሪያድ ሆቴል ባለቤት ህዝቡን በማሰመንና በመለመን ምንመ ተቃውሞ እንዳይደረግ ከፍተና አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሃጂ አ/ሃዲ ከፍተኛ አክብሮትና ተሰሚነት ስላላቸው ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት ውስጥ ለውስጥ ቀጣይ ስትራቴጂዎችን እየሰራን እንደሆነ እና ሁላችንም የስልጤ ዞን ሆዳም አመራሮች የሚሰሩትን ስራ ተከታትለን እንድናጋልጥና በዚህ በቤተ ዘመድ ጉባኤ ምርጫ እንዳንሳተፍ መልእክቴን አስተላልፋለው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ተጨማሪ መረጃዎች ያሏችሁ ሰዎች መረጃ ለሙስሊሙ በመስጠት ለጥቅም ዲናቸውን የሸጡ አመራሮችን እናጋልጥ እላለሁ

No comments:

Post a Comment