Thursday, August 9, 2012

A Atatement From The World Federation of Muslim Scholars

አለም አቀፍ የሙስሊም ዑለማ አንድነት ማህበር በኢትዩጵያ መንግስት አማካኝነት እየተካሄደ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያወግዝ መግለጫ አወጣ
 አዲስ አበባ  ሬዲዮ ቢላል ሐምሌ 3/2004
  በመግለጫውም መንግስት ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ማቆም እንዳለበትና ችግሩን ከሙስሊሙ አመራር ጋር በመወያየት መፍታት እንዳለበት አሳስቧል ።
ይህ ካልሆነ ግን አገሪቷ ላይ የከፋ ክስተት ሊያስከትል እንደሚችልም አስጠንቅቋል። በተጨማሪም በአለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች ግፍና በደል እየደረሰባቸው ያሉትን ሙስሊሞች በሙል ሊታደጓቸውና ከጎናቸው ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስቧል።
ሙሉ መግለጫውን  እንደሚከተለው አቅርበነዋል :
“ ምስጋና ለአላህ ይገባው ፣ የአላህ እዝነትና ሰላም በመልክተኛው ሙሃመድ ፣ በባልደረቦቹ እና እነሱን በተወዳጁ ላይ ይሁን ። በመቀጠል ፡
ማህበሩ በ ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየተከሰተ ያለውን ድርጊት በንቃት እየተከታተለ ይገኛል።
ኢትዩጵያ የመጀመርያዋ ሙስሊሞች የተሰደዱባት፣ በታላቁ ነብዩ ሙሃመድ (ሰዐወ) አንደበት “እርሱ ዘንድ ማንም አይበደልም” የተባለለት የንጉስ ነጃሺ ሃገር ናት ። ነጃሺ የነብዩ ሙሃመድ (ሰዐወ) ባልደረቦችን  ይደርስባቸው ከነበረ ጭቆናና በደል የታደገ ታላቅ ንጉስ ነበር ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ሁኔታ ከሃይለስላሴ ጀምሮ ወደከፋ አቅጣጫ ነበር ያመራው ። ሃይለስላሴ የኢትዩጵያውያን ሙስሊሞችን ጨቁኗል። የበደልን ገፈት አቅምሷቸዋል! ።
አሁኑ የአገዛዝ ስርአት ውስጥ ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ሰብአዊ መብታቸውን ሙሉ በሙሉ ባይጎናጸፉም በአንጻራዊ መልኩ ግን የነጻነት ጎህ በትንሹም ቢሆን አፈንጥቆላቸዋል።
ሰሞኑን ትልቅና አስደንጋጭ ክስተት ተከስቷል እርሱም የመንግስት ሃይላት አሸባሪ እና አልቃኢዳ በሚል ተልካሻ ምክንያት ዱዓቶች እና ሃይማኖተኛ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ሰንዝሯል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩትም በየ እስር ቤቶች ታጉረው ስቃይና ግርፋት እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ ፣ መሳጂዶቻቸው ተደፍረዋል፣  ጋዜጦቻቸውና መጽሄቶቻቸውም ታግደው ይገኛሉ። ከተጠቀሱት በላይ አስከፊው ድርጊት ደግሞ መንግስት  በሃይልና መጅሊስን በመጠቀም ጠማማው አብደላ አል_ሃረሪ ያመጣውን የአህባሽ እምነት ለማስፋፋት መዳከሩና በሙስሊሞች መሃከል ግጭትና እልቂት በመፍጠር የመንግስትን ፖለቲካዊ አላማን ለማሳካት የሚደረገው ጥረት ነው ።
ይህ ክስተት የኢትዩጵያውያንን ሙስሊሞች ቁጣ የቀሰቀሰና ታላቅ የሆነን ተቃውሞ ያስነሳ ክስተት ነው።
ይህ መከራና ችግር በኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ሰፍሮ ባለበት ሂደት አለም አቀፍ የሙስሊም ዑለማዎች አንድነት ማህበር በጉዳዩ ላይ ያለውን ዓቋም በአጽንኦት እንደሚከተለው ያሳውቃል፡
1_ ማህበሩ የኢትዩጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እያደረሰ ያለውን በደል እንዲያነሳ፣ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውንና ተወካዩቻቸውን በራሳቸው የመምረጥ መብታቸውን እንዲያከብር በተጨማሪም ከክርስትያኖች ጋር እኩል መብታቸውንና ግዴታቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ ማድረግ እንዳለበት ያሳስባል ። 
ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች  ሃገራዊ ግዴታቸውን እየተወጡና ብዙሃን ሆነው ሳለ ለምንድነው መብታቸው የሚረገጠው !? በክልሎቻቸው ላይስ ለምንድነው ድህነት፣መሃይምነትና ኋላቀርነት እንዲንሰራፋ የሚደረገው!?።
  ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች በታሪክ ሂደት ላይ የመቻቻልና የአብሮነትን ባህል ያሳዩ ናቸው። ያለምንም ጥርጥር የኢትዩጵያን መንግስትና ህዝቦቿን  ጠንካራ ሊያደርግ የሚችለው መብትንና ግዴታን በእኩልነት መወጣት ሲቻል ብቻ ነው።
2_ አምባገነንት፣እስራት፣ግርፋት፣ያለምንም መረጃ ሙስሊሙን መወንጀል እንዲሁም በመሃከላቸው ግጭትንና ረብሻን ማቀጣጠል ፡ በፖለቲካዊ ሂደት ላይ በሀገሪቷ ላይ ውድመትንና ህዝባዊ እልቂትን ከማስከተል ውጭ ውጤታማ እንዳልሆነ በሶማልያና መሰል አገሮች ላይ ዓለም በሙል በገሃድ ያየው ነው። ስለዚህ  የኢትዩጵያ መንግስት ችግሩን ከሙስሊሙ ምሁራን ተወካዩችና ከጎሳ ባላባቶች ጋር በመደራደር መብትንና ተቻችሎ መኖርን ዘላቂ በሆነ መልኩ ሊያረጋግጡ በሚችል መልኩ ችግሩን መፍታት አለበት።
3_ ማህበሩ ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ መረዳጃ ማህር፣ የሙስሊም ምሁራንና ልሂቃን ባጠቃላይ በአለም ላይ ላለው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከኢትዩጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ማቴርያላዊም ሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪውን ያስተላልፋል።
4_ ማህበሩ ለአለምአቀፍ መረዳጃ ማህበራትና አለምአቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች  ለኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ልዩ ትኩረት እንዲሰጡና የተለያዩ ዘርፎችን ያማከለ እድገት እንዲፈጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል።
5_ ማህበሩ በሊቀመንበሩ መሪነትና በታላላቅ ልዑካኖቹ አማካኝነት ኢትዩጵያውያን ሙስሊሞች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅና ከኢትዩጵያ መንግስት እንዲሁም ከሙስሊሙ ምሁራን ጋር ውይይት ለማድረግ ኢትዩጵያን ለመጎብኘት ዝግጁ መሆኑን ያሳውቃል ።
በመጨረሻም  የማህበሩ ፍላጎት በ ኢትዩጵያ ሰላም፣መቻቻል፣እኩልነት፣ፍትህ እና ሁለገብ የሆነ እድገት ሰፍኖ ማየት መሆኑን እናሳቃለን።
“በላቸውም፦ስሩ አላህ ስራችሁን በእርግጥ ያያልና መልእክተኛውና ምእመናንም (እንደዚሁ ያያሉ) “ (አል_ተውባ: 105)

ደውሃ ረመዳን 18/1433 እንደ ሂጅራ አቆጣጠር
ወይም እአአ 06/08/2012
ፕር/ዩሱፍ አልቀርዳዊ  የማህበሩ ሊቀመንበር
ፕር/አሊ አል_ቁራ ዳጊ የማህበሩ ፕሬዝዳንት
The World Federation of Muslim Scholars issued a statement calling on the Ethiopian government to protect the rights of Muslims and dialogue with their leaders, and warned the consequences of causing discord among them, also called the Islamic world to protect their fellow oppressed everywhere, and this is the text of the statement:

Praise be to God, prayer and peace upon the Messenger of Allah Muhammad and his family and
allies .. And after;;
The World federation of Muslim Scholars is following the situation of Muslims Habesha (Ethiopia) land first migration, the land of the good King Nejashi, under whom nobody was oppressed, therefore he stood with the com panions of the Messenger of Allah peace be upon him the oppressed and show magnanimity, values and high morals, and the outcome of the conditions of Muslims today, starting from the emperor Haileselase which wreaked havoc in the land, and he restricted the life of Muslims and left them with suffering.

Today, under the current government, which began a kind of openness to Muslims - and that did not get to all their rights - there have been recent major problems where the government launched an attack against the preachers and committed youth on charges of terrorism and Al Qaeda, and plunged hundreds of them in prisons, with torture, and it stormed some mosques and closed most of their newspapers and magazines, and more than that the government's attempt to bring about dissension Ahbash followers to stray Abdullah Harari, and the government trying to impose ahbash on the Ethiopians and the majority of the Supreme Council of Muslims and this is what Muslims see as blatant interference in religious affairs, and the seed of dissension among them to achieve the political goals of the government, and therefore resulted in massive wave of protests from Muslims, and in front of these problems and calamities that befell our brothers the Muslims in Ethiopia (Abyssinia) the International Federation for Muslim Scholars confirms the following:

1 – Federation calls on the Ethiopian government to lift oppression and injustice of Muslims in
Ethiopia, and the granting of religious freedom, the right to choose their representatives, and the achievement of their equality with Christians in rights and duties, they are also people of the earth, and they make up a large proportion of the population, why digest their rights while they carry their citizenship duties properly? Why it is intended for their areas of backwardness, ignorance and poverty? Muslims in Ethiopia has been a good and tolerance throughout history.
It is without doubt the realization of this true partnership and equality in rights and duties is the one who strengthens the Government and people of Ethiopia.

2 – Federation warns that the Ethiopian government to proceed with the policy of violence,
oppression, imprisonment and false accusations to all Muslims and cause discord among them may have failed in the whole world, and it means to destroy the people and government together as we have seen in Somalia and elsewhere. Therefore we demand the government to dialogue with representatives of Muslim scholars and tribal leaders and worshipers to reach a permanent peaceful coexistence formula protects the rights and borders.

3 – Federation calls on Organization of Islamic Cooperation and the leaders of the Muslim world and its scholars and its people to stand with the oppressed of th ir brothers in Ethiopia, and their support financially and morally, and pressure on the government to achieve universal justice and full equality, and remedies for them and injustice.

4 – Federation calls for charitable organizations and humanitarian care in Ethiopia (the land of the first migration) to achieve comprehensive development for them.

5 – Federation show its readiness to visit Ethiopia through high-level delegation headed by its
secretary general for the situation of Muslims to closely, and dialogue with the government and
scholars in order to achieve security, stability and peaceful coexistence based on justice and equality in this country that bears fragrant history and magnanimity and dignity, hence the Federation does not wish this country except good and peaceful coexistence based on tolerance and the rights of full citizenship for all, and the overall development and prosperity.

{Say work and Allah observe your work and His Messenger and the believers [Al Toba: 105].
Doha: 18 Ramadan 1433 AH
Posted: 06/08/2012 m
A. Dr. Ali Al Dagi a                        Dr. Yusuf al-Qaradawi

No comments:

Post a Comment