ከታች
የተዘረዘሩት የነገ ጁምአ የተቃዉሞ ሂደታችን ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቅ ስላለበት የጁምአ ሰላት ከተጠናቀቀ ቡሀላ ሁላችንም ባለንበት ቦታ በመቀመጥ ብቻ ነዉ ሰላማዊ የተቃዉሞ ድምፃችንን የምናሰማዉ:: ባለንበት ቦታ ተቀምጠን ተቃዉሟችንን መግለፃችን ማንኛዉም አካል ሰላማዊ ሂደታችንን ለማደፍረስ ቀዳዳ እንዳያገኝ ያደርገዎል:: ከጁምአ ሰላት ቡሀላ ሁሉም ሰዉ በቦታዉ መቀመጡን እርግጠኛ እንሁን!!! ማንኛዉም ሰዉ ከመቀመጫዉ ተነስቶ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከተመለከትነዉ ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብና እንዲቀመጥ ማድረግ ይኖርብናል:: ሌላዉ ማሳሰቢያ ተቃዉሟችንን በሰላማዊ መንገድ የምናካሂደዉ
ተቀምጠን በመሆኑ ከፊታችንም ሆነ ከኃላ የሚደረጉት እንቅስቃሴ ለሁሉም በግልፅ ስለሚታዩ የተለየ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን ስንመለከት በሞባይላችን መቅረፃችንን አንዘንጋ!! ይህንን መልዕክት ላልሰሙት አሰሙ!! ከጁምአ ሰላት ቡሀላ ከቦታችን ሳንነሳ በተቀመጥንበት ብቻ ተቃዉሟችንን እናካሂዳለን!!!!
ሰላማዊና ደማቁ ተቃውሞአችን በአሁኑ ጁምዓም ይቀጥላል
በሰላማዊነቱና በሙሉ መግባባት በመፈፀሙ ልዩ የሆነው የጁምዓው የተቃውሞ ትዕይንት በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ሲሆን ስርአቱንም በሚመለከት ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
1. የሂደታችንን ሰላማዊነትና ለማንኛውም ሰላማዊ አማራጭ (ሽምግልናን ጨምሮ) ከማንም ቀድመን የምንገኝ መሆናችንን ለማሳየት ሰላት እንዳበቃ ለ5 ደቂቃ ሁላችንም ነጭ ጨርቅ፤ ወረቀት ወይም ሶፍት እናውለበልባለን፡፡
2. የኮሚቴዎቻችንን እና የዱአቶችን መታሰር፤ ጥያቄዎቻችንን ለመጠምዘዝ እና ለማድበስበስ የሚደረገውን ጥረት በመቃወምና ኮሚቴዎቻችን እስኪፈቱ ሁሌም ከልባችን እንደሚኖሩ ለማሳየት
• 17 ግዜ አላሁ አክበር
• 17 ግዜ ድምፃችን ይሰማ
• 17 ግዜ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ
• 17 ግዜ ምርጫችን በመስጂዳችን በህብረት በማለት ተቃውሞአችንን እናሰማለን
3. ለ 3 ደቂቃ አንድነታችንን እና ፅናታችንን ለማሳየት እጅ ለእጅ እንያያዛለን
4. በመጨረሻም እጃችንን በማንሳት ሁላችንም ከልባችን በተናጠል ዱዓ ለ3 ደቂቃ እናደርግና እንለያያለን
5. ከተንኮለኞች ሴራ ለመጠበቅና ሂደታችንን ቀጣይ ለማድረግ እንደተለመደው እጅግ ሰላማዊ መሆን የሚጠበቅብን ሲሆን ከላይ የተቀመጡትን ብቻ በመፈፀም በእኩል ጀምረን በእኩል በመጨረስ ትዕይንቱ እንደበቃም ቶሎ ከስፍራው መሄድ ይኖርብናል፡፡

ድምፃችን ይሰማ
( 9 hours ago)
በአሁኑ ጁመዓ ዛሬም አላማችንን እንዳልሳትን በተግባር እናሳያቸዋለን
በመላው ዓለም የምንገኝ ሙስሊሞች ላስቀመጥናቸው ቀላልና ግልፅ የመብት ጥያቄዎች መከበር መታገል ከጀመርን ስምንት ወራት አልፈውናል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አምስት ወሳኝ የሆኑ እጅግ ተፈታታኝ ግን ደግሞ በድል የተወጣናቸው ምእራፎች አሳልፈናል፡፡
1. ገና ከጅምሩ ህዝባዊ ጥያቄዎቻችንን አንጥረን በማውጣት እንዴት እንሂድባቸው ብለን ስንመክር ‹‹በአወሊያ ተማሪዎች ጥያቄ ሰበብ የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት የተሰባሰቡ አክራሪዎች›› ተብለናል፡፡ ይህ ግን አላማችንንም ሆነ አካሄዳችንን ቅንጣት ታህል ሳይሸርፈው ሃገራችን አይታ የማታውቀውን ያልተደራጀ ግን ደግሞ መላው

ሙስሊምን ያንቀሳቀሰ ሰላማዊ የመብት ትግል ማድረግ ችለናል፡፡ ምዕራፍ አንድ በገጠሙን ፈተናዎች ሳንበገር በድል ተወጥተነዋል፡፡
2. በሰበብ የተሰባሰቡ አክሪዎች ከተባልን በኋላ ለጥያቄአችንና ለሂደታችን አግባብነትና ሰላማዊነት መንግስት እያንቆለጳጰሰ በኮሚቴዎቻችንም ሆነ በሚዲያው በኩል እየነገረን በተግባር ደረጃ ግን መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልነበረበት የየካቲት 26 ቀጠሮ ደረሰ፡፡ ይህ እለት ወሳኝ ምእራፍነቱ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመንግስትም የነበረ ሲሆን ውይይቱ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ ኮሚቴዎቻችን ለመግሪብ ሰላት በወጡበት ከመንግስት በማይጠበቅ ስርአት በድብቅ በተሰጠ መግለጫ ‹‹ጥያቄዎቹ መመለሳቸውና ይህም ከኮሚቴው ጋር መግባባት ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በአወሊያም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሚኖሩ መሰባሰቦች ህጋዊ አይደሉም›› ተባልን፡፡ ለሃቅና ለህዝብ ፍላጎት በማደርና ለአለማ በመፅናት በእድሜያችን አይተን በማናውቀው ቁርጠኝነት ውድ ኮሚቴዎቻችን ግን የውይይቱን ሙሉ ይዘት ከነሸፍጡ በመንገር ጥያቄዎቻችን በሚገባ እንዳልተመለሱ እና የመጨረሻ የሚባለውን ሰላማዊ ሂደት እንደሚገፉበት በግልፅ አወጁ፡፡ ይህ ሁለተኛው ምዕራፍ ከቀደመው የከበደ ቢሆንም በአላህ እገዛና በህዝባችን ፅናት በድል ተወጥተን አስደማሚ የሆነ ታሪክ በመስራት ቀጠልን፡፡
3. ጥያቄአችንን ለመመለስ ፍቃደኛ ያልሆኑ ግን ደግሞ ስልታዊ በሆነ መንገድ ማኮላሸት ያልተቻላቸው አካላት በሶስተኛው ምእራፍ የተከተሉት መንገድ አለምን ያስገረመ ዛቻና ማስፈራሪያ ነበር፡፡ ‹‹ሰላማዊና ህገመንግስታዊ›› ባሉበተ አፋቸው ‹‹ለሰላማዊ ሂደት ፍላጎት የሌላቸው ፀረ ሰላም ቡድኖች›› እያሉ ህዝብን ለመለያየትና ሂደታችንን ያለውጤት ለመቅጨት የፕሮፖጋንዳ ሃይላቸውን በሙሉ ተጠቀሙት፡፡ በዚህ ምእራፍ ግን ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን መላው የሃገራችን ህዝብ በመንግስት በማፈር ከሰላማዊው ህዝበ ሙስሊም ጎን ተሰለፈ፡፡ መንግስት በሰራው አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ሰበብም ሂደታችን በርካታ እድገቶችን አሳየ፡፡ እኛን የሚያስቆመን የጥያቄዎቻችን መመለስ እንጂ ባዶ ማታለልም ሆነ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳልሆነ በመግለጫው ማግስት እኛኑ ያስገረመ የተቃውሞ ትእይንት በአንዋርና በሌሎች ቦታዎች ተካሄደ፡፡ ምዕራፍ ሶስትን በድል አለፍነው፡፡
4. ለመንግስት ቀጣይ የሆነው ሂደታችንን የማኮላሸት እርምጃ ደግሞ ለማስታወስ በሚከብድ መልኩ መስጂዶቻችንን በደም በሚዋኙና በስቃይ በሚያቃትቱ ቁስለኞች እንዲሞሉ ያደረገው የሃምሌ ስድስቱ ጭፍጨፋና እና እሱን ተከትሎ የተባባሰው የህግ ጥሰት ነው፡፡ የህግ ጥሰቱን ለመሸፋፈን ሚዲያዎቹን በሙሉ ከእውነትና ከህዝብ ተቃራኒ በማሰለፍ ‹ህጋዊ› መስሎ ለመገኘት ሲሞክር በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ እርምጃ በኋላ ‹‹መብቴ ይከበርልኝ›› የሚል ዝር የሚል ሰው አይኖርም አይነት መተማመን አሳድሮ ነበር፡፡ በደል የሚያስፈራው አላማ የሌለውን እንጂ እኛ በአላማ የተነሳነውን ሰላማዊ ንፁሃን ሙስሊሞችማ የሚደርስብን በደል የሚመጣልንን የአላህ እርዳት እና የኛን ጥንካሬ ይጨምረዋል እንጂ እንደማይቀንሰው በቀጣይ ቀናት የታዩት አለም አቀፍ ተቃውሞዎች ምስክር ናቸው፡፡ አራተኛው ምእራፍም ብዙ ዋጋ ያስከፈለን ቢመስልም ከትግል ሂደት አንፃር ሲመዘን ግን በድል የተጠናቀቀ ነበር፡፡
5. የመጨረሻ ያሉትን እና ይህን እርምጃ በመውሰድ መጪው ግዜያት በነሱ ቋንቋ ‹‹እንደተለመደው ሰላማዊ›› እንደኛ አተረጓጎም ደግሞ ‹‹የህዝብ ድምፅ የሚታፈንበትና መብቱ የሚረገጥበት›› ሁኔታ እንደሚቀጥል ማስተማመኛ ያሉትን እርምጃ ወሰዱ፡፡ ይኸውም የምንወዳቸውን፤ የምንናፍቃቸውን፤ በአካል ብቻ ሳይሆን በድምፅ እንኳን ሊርቁን የማንፈልገውን፤ ከነስቃያቸው አብረን መሆን ካልተቻለን በነሱ ቦታ ራሳችንን ለመስጠት ቃል የገባንላቸው በምንም መስፈርት የማንደራደርባቸውን ውድ ኮሚቴዎቻችንና ዱአቶቻችንን ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ በመያዝ ለእስር ዳረጓቸው፡፡ ይኼኛው ምእራፍ ለነሱ ‹የሁሉ ነገር መጨረሻ› አድርገው ነበር የወሰዱት፡፡ ለኛ ደግሞ ‹‹የቀጣዩ ምዕራፍ ጅማሮ›› ነበር፡፡ በእርግጥም እውነቱ ይህ ነው፡፡ በትግል ሂደት የአስተባባሪዎች መታሰር ወሳኝ ነው፡፡ ሂደቱ ‹‹የታሰሩት ይፈቱልን›› ወደሚለው ከተቀየር ሽንፈትን የሚያሳይ ሲሆን ‹መብታችን ይከበር የታሰሩትም ይፈቱ› በሚል ከቀጠለ ግን ትግሉ መቼም ሊቀለበስ በማይችል ጠንካራ መሰረት ላይ መቆሙን ማረጋገጫ ነው፡፡ አምስተኛው ምእራፍ በድል ለማለፋችን አሁን ያለንበትን ፅናትና ቁርጠኝነት ሁሉም እያየው ነውና ሌላ መስካሪ አያሻም፡፡
በመሆኑም እያንዳንዱ የሚያጋጥሙን መሰናክሎችና የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሰወኛ በሆነ ግምገማ ትክክለኛ ለመሆናቸው የሚጠራጠር የለም፡፡ ባሳለፍናቸው የትግል ወራት ብንኮራ እንጂ የሚያሸማቅቀንና የሚያሳፍረን አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ ጉዞአችን በውል የሚታወቅ ጫፍ ስላለው መሃል ሰጥመን የምንቀር እንዳልሆንን ለኛም ሆነ ለሌላው ሂደታችን አስተምሯል፡፡ በቀጣይ የምንከተላቸው ስልቶችም በአላህ እገዛ የተጠኑና ከውጤት ሊያደርሱን እንደሚችሉ እርግጠኞች ነን፡፡ ኢንሻአላህ፡፡ በተለይ ያለንበት ወር የድል ወር ነውና የአላህን ቁድራ በቅርቡ ያሳየን ዘንድ ተናንሰን እንለምናለን፡፡ ፀንተንም እንታገላለን፡፡ ባሳለፍናቸው ሶስት የረመዳን ጁመአዎች የኢትዮጵያ ሙስሊም የደረሰበትን የብስለትና የአይበገሬነት ደረጃ በየጁመአው በሺዎችና በመቶቸዎች የሚቆጠሩ ወንድምና እህቶቻችን እየተደበደቡና እየታሰሩም ‹‹ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም›› በሚል መርህ ለትግል ታሪካችን ድንቅ ምእራፍ ጨምረንለታል፡፡ ይዘገይ ይሆናል እንጂ ዛሬ ያንቋሸሹን በዳዮች ነገ ሊያመሰግኑን እንደሚችሉ ፍንጮች እየታዩ ነው፡፡
በመጨረሻም ማስተላለፍ የምንፈልገው መልእክት አላማችን ጥያቄዎቻችንን ማስመለስ እና የታሰሩ ብርቅዬዎቻችንን ማስፈታት በመሆኑ ያንን ሊያሳኩ የሚችሉ አማራጮችን በሙሉ አሟጠን መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ሰሞኑን ሂደቱን ያልለየና ስድስተኛ ምእራፍ የሚመስል የሽምግልና ሂደት መጀመሩን ሁላችንም ሰምተናል፡፡ ሽምግልናውን እንደአቋም ብንደግፍም እንደአካሄድ ግን በርካታ ህፀፆችን በመለየት ተችተናል፡፡ ሽምግልናው ለድርድር መቅረብ ያለባቸውንና የሌባቸውን ነጥቦች ከህዝብ ትርታ አኳያ ሊያጤን እንደሚገባ አሳስበናል፡፡ የትችታችን አላማ የሽምግልና ባቡሩን ወደሃዲዱ ለማስመለስ በመሆኑ ቀጣይ ሂደቱን ግዜ ሰጥተን መከታተል እንደከዚህ ቀደሙ እንደ ስልት ልንከተለው ይገባል፡፡ ሽምግልናው የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ሽማግሌዎቹን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አቅጣጫ እንዲይዙ በማድረግ ተበዳይ ዳግም የማይበደልበት በፍጥነት ሊታይ የሚችል (በተለይ ታግለው የሚያታግሉን የኮሚቴዎቻችን መፈታት ጋር በተያያዘ) ውጤት ማምጣት የሚያስችል አካሄድ መሄድ ይችሉ እንደሆነ ለማየት ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን ሽምግልና እና የተቃውሞ ሂደታችን አንድ የጋራ ችግር ለመፍታት ጥቅም ላይ ለማዋል የተቀየሱ በጣም ሰላማዊ መንገዶች በመሆናቸው ሁለቱም ጎን ለጎን ሊጓዙ እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡ ሂደቶች እንደመሆናቸው መጠን አንዱ በአንዱ ውስጥ የግድ መስመጥ አይጠበቅባቸውም፡፡ የጋራ የሚያደርጋቸው ግባቸው በመሆኑ ለግብ ለመድረስ የፈጠነው አካሄድ የተሸለ ድጋፍ ማግኘቱ የማይቀር ነው፡፡ ያንን ለማረጋገጥ ግን ሁለቱም ፈጣን በሆነ መልኩ መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ግዜው አጭር ነው፡፡ ረመዳን ከመውጣቱ በፊት አዝማሚያውን የሚያሳይ ፍንጭ ማየት ግድ ይለናል፡፡ በመሆኑም ሽምግልና ነፍስያን እየታገሉ ለአላህ ተብሎ የሚሰራ ስራ በመሆኑ በተቃውሞው ትዕይንት መቆምና አለመቆምን ተንተርሶ ከስራው መውጣት ተገቢ አይሆንም፡፡ ከተቃውሞ ሂደታችንም የሚጠበቀው ውጤት እንጂ ድምቀት ብቻ ባለመሆኑ ለውጤት የሚያደርሱ ሌሎች አማራጮችን ትኩረት ሰጥተን ልንከታተላቸው ይገባል፡፡ አሁን ላለንበት ሁኔታ ግን የተቃውሞ ሂደታችንን ሊያሳርፍ የሚችል ተጨባጭ ፍንጭ ማየት እስከምንችል ድረስ የነበረንን ሂደት አጠናክረን እንገፋበታለን፡፡ ከዚህ ትግል ልዩ መገለጫዎች ውስጥ ‹‹እውነት›› እና ‹‹ሙሉ መግባባት›› ዋነኞቹ ናቸውና ይህንኑ አጠናክረን እንድንሄድ መልእክታችን ነው፡፡ ከወትሮው በተለይ በድምቀት እንደሚካሄድ የሚጠበቀውን የፊታችንን የጁምዓ ስልት እንደተለመደው በተለያዩ መንገዶች የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ እየገለፅን በግልፅ ልዩነት የሚታይበት የህዝብ ብዛት በመስጂድና በተለይ ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ እንዲታይ የበኩላችንን እንወጣ፡፡

No comments:
Post a Comment