አዲስ
ዘመን ጋዜጣ በዕለተ ረቡዕ ነሐሴ 2 2004 ዕትሙ “የእስልምና ምክር ቤት አባላትን በአዲስ የመተካት መብት
የሕዝበ ሙስሊሙ ብቻ ነው ” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ “ኡለማዎች” ምክር ቤት አስገነዘበ ሲል ስለ “ምርጫው”ሁኔታ
ዜና ሰርቷል፡፡
እርግጥ ነው በአሁኑ ሰዓት መልኩን እንዲቀይርና ያልተፈለገ ነገር እንዲያስከትል ወከባ እየተፈፀመበት የሚገኘው ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ሂደታችን ይዟቸው ከዘለቃቸው ጥያቄዎች መካከል “የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ” ይደረግ የሚለው አንዱ እና አንኳሩ ነው፡፡
የመጅሊሱ አመራር አካላት በአዲስና በሕዝብ ይሁንታ በተመረጡ አመራሮች ይተኩ የሚለውን ጥያቄያችንን ያቀረብነው ለመንግስትና ለመንግስት ብቻ ነበር፡፡ የአንድ እጅ ጣት ያህል እንኳን የማይሞሉት የ “ኡለማ” ምክር ቤቱ አባላት ምንም ዓይነት የህዝብ ይሁንታ የሌላቸው ናቸው፡፡ አባላቱ ሙሉ በሙሉ አሕባሾች ሲሆኑ “የኡለማ ምክር ቤት” የሚለውን ስም በመጠቀም እንደልቡ የሚፈነጭበት ሰው ቢኖር “ሸህ ኢዘዲን” ብቻ ነው፡፡
የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ሙሉ በሙሉ መወገድ ያለባቸው መሆኑ በሕዝብ በመታመኑ ምክንያት ተቃውሞ ሲነሳ ከህዝብ ጋር በመሆን ለጥያቄው መፍትሔ ይበጅለት ዘንድ ህዝቡ ጥያቄውን ያቀረበው ለ“ኡለማዎች” ምክር ቤት አልነበረም፡፡ ተገቢም አይሆንም፡፡ ራሱ እንዲወገድ ሕዝብ የፈረደበት አካል ምላሽ እንዲሰጥ ለሱ ጥያቄ አይቀርብለትም፡፡ “የኡለማዎች” ምክር ቤት ተቃውሞ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በመንግስት ሚዲያ በመቅረብ የሕዝብን ጥያቄ ሲያጣጥል እና ንቀት በተሞላበት ሁኔታ በሕዝብ ላይ በማንጓጠጥ ፍፁም ወገንተኛነት የተጠናወታቸው መግለጫዎችን ሲሰጥ የቆየ መሆኑ ከሕዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡ በዚህ አግባብ የ “ኡለማዎች” ምክር ቤት የሙስሊሙን ጥያቄ የመመለስ ቀርቶ የመመልከት (የማየት) መብት፣ ብቃትም ሆነ ሞራል አይኖረውም፡፡
የ “ኡለማዎች” ምክር ቤት ሚና እየጎላ የመጣው መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ያለመግባቱን በአንድ ወይም በሌላ አጋጣሚ ለማስመስከር በመሻት የሙስሊሙን ጥያቄ ምላሽ መስጠት ያለበት ራሱ ተቋሙ እና ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ነው በማለት ሴራ መጎንጎን ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ነው፡፡ይህን የአሻንጉሊት ሚና እንዲጫወት የተሰየመው ክፍል እና ስብስቡ እንደ የመጅሊሱ አመራር አካላት ሁሉ የህዝብ እውቅና የለውም፡፡ አስገራሚው ነገር የ“ኡለማ” ምክር ቤቱ በሊቀመንበር ( ከአዝሀር ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሰር ማዕረግ እንዳለው ይነገራል) የሚመራ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም ሊቀመንበሩ የአቋም ልዩነት በማሳየታቸው ብቻ ከሹመታቸው የመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ ከሚናቸው ገሸሽ ተደርገው ሲያበቁ በ “ቆራጥ አመራር” የታወቀው “ሸኽ ኢዘዲን” ቦታውን በመረከብ በየመገናኛ ብዙኃኑ በመቅረብ የታዘዘውን ያወራል፡፡
የአሕባሽ መለዮ እንደሆነ በውል የሚታወቀውን አረንጓዴ ጥምጣሙን አነግቶ በትላንትናው (ረቡዕ ነሐሴ 2 2004 )የአዲስ ዘመን እትም ላይ ስለ እኛ የምርጫ ሁኔታ መግለጫ ቢጤ ሰጥቷል፡፡ በንግግሩም ምርጫውን በተመለከተ ነሐሴ 15 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ያሳውቅና ጋዜጣው ንግግሩን በመጠቀስ “ነሐሴ 15 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም የቀበሌው ታላቁ መስጂድ ኢማም፣በቀበሌው ነዋሪነታቸው የተረጋገጠና ለምርጫው የተመዘገቡ ሕዝበ ሙስሊሞችን በቀበሌው መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኙለት በመስጂድና በሌሎች መንገዶች ጥሪ እንደሚያስተላልፉ ጠቅሰዋል” ይላል፡፡
ይህ “ምርጫ” ከ “ሀ” እስከ “ፐ” በ “ፌክ” የተሞላ ሲሆን ለወራት የዘለቀውን የተቃውሞ ሂደት በማኮላሸት ባዘጋጁት “መመሪያ” መሠረት ለቀጣይ 10 ዓመታት ስልጣኑን ተቆጣጥረው ሲያበቁ ህልማቸውን ተግባራዊ በማድረግ ሙስሊሙን በግፍ ለመግዛት ሁኔታዎችን ያመቻቹበት መድክ ነው፡፡ የምርጫው ተቀባይነት መገለጫ የሆኑት መሥፈርቶች በሙሉ ችላ በተባሉበትና የመንግስትን የሀይል ጡንጫ በመተማመን ያሻቸውን እየሰሩ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ህዝብ ምርጫውን አምኖ መቀበል ይቅርና ተሳታፊነቱ በራሱ ብዙ ርቀት የሚቀረው ጉዳይ ነው፡፡
የህዝብ ድምፅ ተሠሚነት ማግኘቱ ተረጋግጦ ምርጫውም ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው የ“ኡለማ” ምክር ቤት አመራርን ጨምሮ ሕዝብ ዕውቅና የነፈጋቸው የመጅሊሱ አመራሮች በሙሉ በይፋ ከቦታቸው እንዲነሱ ሲደረግ ነው፡፡ ገለልተኛና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሰዎች መመረጥ፣ በቀጣይም ቀጥተኛ የሕዝብ ይሁንታ የታከለበት የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያ መዘጋጀትና ምርጫው እንዴት መካሄድ እንዳለበት ለሕዝብ ይፋ መሆን ህዝብ በሂደቱ ባለቤት መሆኑ የሚረጋገጥባቸውና ሂደቱም ቅቡልነት የሚያገኝበት ሌላኛው መገለጫ ነው፡፡ ሕዝብ በምን መልኩ በምርጫው ተሳታፊ የሚሆንበት ሥርዓት መመሪያው ሊያካትታቸው ከሚገባቸው አንኳር ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡
የ “ኡለማ” ምክር ቤቱ አሁን አደርገዋለሁ በሚለው ምርጫ ምርጫው የሚካሄደው በእጅ ማውጣት ስርዓት ነው፡፡ ከአገሪቱ ህዝብ ግማሹን አሀዝ የሚወክለው ሙስሊሙ ህብረተሰብ የእምነት ተቋሙን አመራሮች ለመምረጥ የሚመጥነው አሰራር መስጂዱን ያማከለና ዘመናዊነት የተላበሰ እንጂ ለማጭበርበር የተጋለጠና የክፍል ሞኒተር የመምረጥ ያክል የሆነው እጅ የማውጣት ስርዓት አይደለም፡፡
ምርጫችን በመስጂዳችን የማድረግ መብታችን መከበሩ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኝልናል፡፡
1. አሁን ያለው መጅሊስ ከዚህ ቀደም ለይስሙላ የተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ ውጤት መገለጫ በመሆኑ የዚህ ስህተት ዳግም ሰለባ እንዳንሆን ያግዘናል፣
2. ምርጫውን ኮፊያ በደፉ፣ ጥምጣም በጠመጠሙ እና ጀለቢያ በለበሱ ካድሬዎች እጅ ከመውደቅ ታድገነው ፍፁም ሐይማኖታዊ ገፅታውን የተላበሰ ይሆናል፣
3. የምንመርጣቸው ሰዎች ጥቂቶች ሳይሆኑ ብዙዎቻችን የምናውቃቸው ይሆናሉ፣
4. ምርጫው ሙሉ በሙሉ በሙስሊሞች ቁጥጥር ሥር ሆኖ ይመራል ከመጭበርበር አደጋ ይድናል፣
5. የእምነታችን ስርዓቶችን (ለምሳሌ መሪዎቻችንን) ያለምንም ጣልቃ ገብነትና በአንፃሩ በተሻለ ነፃነት ተግባራዊ ማድረግ የምንጀምርበት የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ አጋጣሚ ይሆናል፡፡ኢንሻ አላህ፡፡
የመጅሊሱ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት መንግስት ካመነበት ጊዜ አንስቶ የይስሙላ ምርጫ ተደርጎ አመራሩን በሚፈልገው መልኩ መቆጣጠር እንዲቻል እንቅስቃሴ የተጀመረው ቀደም ተብሎ ሲሆን የምርጫ ስርዓቱን በመቆጣጠር ዳግም ወንበሩን እንዴት መቆጣጠር እንሚቻል ዘዴ በመቀየስ እንቅስቃሴ የተጀመረውም ቀደም ተብሎ ነው፡፡ ይህም የመንግስት ውሳኔ አለመሆኑን ለመሸፋፈን በማሰብ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔ ቀደም ሲል ያሳለፈው ውሳኔ ነው እየተባለ ተወርቷል፡፡ በዚህ መልኩ የተጀመረው ሴራ ቀጥሎ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የሚፈልጉት ሰዎች ብቻ መጅሊሱን እንዲረከቡ ለማስቻል በስውርም በይፋም እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡ ይህ እጅግ ግልፅ መሆኑ እየታወቀ ይህንንም በማስተባበል “ሸህ ኢዘዲን” “ ‹የኡለማ ምክር ቤት የፈለገውን ምርጫ አስፈፃሚ ሊያስመርጥ ነው፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት አለ› እያሉ ሕዝበ ሙስሊሙን የሚያወናብዱት መሠረተ ቢስ እንደሆነ… ” በማለት በአዲስ ዘመን ላይ ይነግሩናል፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተመለከት ድሮም የነበረና አሁንም እንደቀጠለ የሚገኝ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ብዙ ስለተባለለት ለጊዜው ወደ ጎን እንበለውና “ሼሁ” የሚሉት ግን መሰረተ ቢስ ሳይሆን መሠረቱ የጠና መሆኑን እናስምርበት፡፡ ለዚህም ነው ሕዝበ ሙስሊሙ መብቴ ይከበርልኝ በማለት በሚያሰማው የተቃውሞ ጩኸት የተነሳ በመታሰር፣በመጋዝ እና በስቃይ ላይ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆነው ሕዝቡን በላሳተፈ መልኩ እንዳሻቸው ሮጠው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ “…የተሳካ ምርጫ እንዲሆን ምክር ቤቱ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው ” የሚሉን፡፡
በዚህ የምርጫ የመጨረሻ ውጤት ከፍተኛ መተማመን ስላላቸውም ስልጣኑን ተቆጣጥረው ሲያበቁ ሙስሊሙን እየረገጡ መግዛት ያስችላቸው ዘንድ እንዲሁም ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳያነሳ ለማድረግ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ከአምስት ዓመት ወደ አስር ዓመት በማሳደግ “መመሪያውን” አሻሽለውታል፡፡ አለፍ ሲሉም ምርጫው በቀበሌ ብቻ መሆን እንሚገባው በየጊዜው ቁጥሩ በሚያሻቅብ አስቂኝና ረብ የለሽ ምክንያት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው በቀበሌ ይካሄድ በማለት ፈትዋ ቢጤ የሰጡት “የኡለማ” ምክር ቤቱ ሰውዬና ጓደኞቹ ያቀረቡት ምክንያት ውሀ አይቋጥርም፡፡ ይልቁንም ምርጫችን በመስጂዳችን እያለ የሚጮኸውን ኃይል በአቋሙ ላይ እንዲጸና አድርገውታል፡፡ በቅርቡ በራዲዮ ፋና ምርጫው እንዴት በመስጂድ ሊካሄድ እንደሚችል “ግራ የገባቸው”ና በቀበሌ እንዲሆን ሲሉ የሚያስተዛዝብ አስተያየት የሰጡትንም ግለሰብ ጨምሮ መላ ሙስሊሙን ህዝብ የሚያሳምንና የሚያረካ የምርጫችን በመስጂዳችን አፈፃፀም ሥርዓት ማዘጋጀት ሙዝ ከመላጥ የቀለለ ነው፡፡ ዋናው ነገር የኛን ለኛው ተወት ማድረግ ነው፡፡
የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ/የመንግስት ባለስልጣናት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ይደረግ ሲሉ የወሰኑት ምርጫ የት ይካሄድ? ሲባሉ ሙስሊሙ በፈለገው ቦታ ይሉናል፡፡ ነገር ግን ረዣዥም እና ስውር እጆቻቸው ምርጫው በቀበሌ እንዲሆን እየሠሩ መሆናቸው በውል የምናየውና የምንሰማው እውነታ ነው፡፡ ምርጫውን በፈለግነው ቦታ የማድረግ ውሳኔ የኛ የመብት ጠያቂዎቹ ከሆነማ እነሆ ጥያቄውን ያቀረበው የ “ኡለማ” ምክር ቤቱና “ሼህ ኢዘዲን” ሳይሆኑ እኛ በመሆናችን ከምርጫ ይካሄድ ውሳኔ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምርጫችን በመስጂዳችን የሚለው ድምፃችን ሊሰማ እና ገቢር ሊሆን ይገባዋል፡፡ ጉዳያችን ፍፁም የማይመለከተው የ“ኡለማ” ምክር ቤት በቀበሌ መሆን አለበት የሚለው ውትወታ ውድቅ መደረግ አለበት፡፡
“ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ታሳድራለች” እንዲሉ የመንግስትን የማይናወጥ ሁለንተናዊ ድጋፍ በመተማመን ያሻቸውን በመናገር ያሻቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ጠቃሚ ነጥቦች፡-
1. ላለፉት ስምንት ወራት ሕዝብን አደባባይ ያወጡት ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የቀረቡት ለመንግስት እንጂ ለ “ኡለማ” ምክር ቤት ወይም ለመጅሊስ ባለመሆኑ በየትኛውም የምክር ቤቱ አመራር እርከን ላይ የተቀመጡ አካላት የሚያመጡት መፍትሔ ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡
2. ምርጫ መካሄድ እንዳለበት መታመኑ የመፍትሔው አንዱ አካል እንደሆነ ግንዛቤ ተወስዶ የምርጫው አፈፃፀምን በተመለከተ የመጅሊሱ አመራሮች በይፋ ከቦታቸው ተነስተው ሲያበቁ በሚደረሰው ስምምነት መሠረት ሕዝብ በሚመርጣቸው ገለልተኛ አካላት አማካይነት ምርጫው መካሄድ አለበት፣
3. ምርጫው በቀበሌ ሳይሆን በመስጂዳችን ብቻ መካሄድ ይኖርበታል፡፡
4. ሕጋዊ አግባብነት ያለውን ሒደት ተከትለን የመረጥናቸው ወኪሎቻችን “ላም ባልዋበት ኩበት ለቀማ” እንዲሉ በ “አሸባሪነት” ተወንጅለው በእስር ላይ በሚገኙበት ሁኔታ የሕዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄዎች በመታከክ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
ልብ እንበል
ላለፉት ስምንት ወራት አደባባይ ያወጡን የመብት ጥያቄዎቻችን የሰፊውን ሕዝብ መብትና ክብር ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ አንዳቸውም ተገቢውን ምላሽ አላገኙም፡-
1. የመጅሊሱን ጉዳይ በተመለከተ ምርጫ ይደረጋል ቢባልም የተያዘው ሩጫ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ የህዝብን ጩኸት በማፈን መጅሊሱን ዳግም ለመቆጣጠር ነው፣
2. የአሕባሽ አስተምህሮትን በግዳጅ መጫን አላቆመም፡፡ ይልቁንም በሚያደርጉት ምርጫ የመጅሊሱን በትረ ስልጣን ተቆጣጥረው ሲያበቁ አጠናክረው ለመቀጠል እቅዱ አላቸው፡፡
3. አወሊያ አሁንም ቢሆን በአሕባሾች መዳፍ ውስጥ ያለ ሲሆን በቀጣይም ተቋሙን ጠንካራ የአሕባሽ አስተምህሮት መስጪያ ማዕከል ለማድረግ በሩጫ ላይ ይገኛሉ፣
4. ሕጋዊ ሥርዓትን ተከትለን የመረጥናቸው ወኪሎቻችን እና ታዋቂ የኢስላም ልጆች “አሸባሪዎች” ተብለው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
የሰመረለት አካሄድን እንጂ የሰመረለት ውጤት ሳናስመዘግብ ዛሬም በከፋ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ መሆናችን የጀመርነውን ሠላማዊ መብታችንን የማስከበር ሂደታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ግድ ይለናል፡፡

አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ይርዳን፡፡ አሚን
No comments:
Post a Comment