የፊታችን
ጁምአ የኢድ ዎዜማ በመሆኑ ማንኛዉም አይነት ተቃዉሞ በሁሉም ቦታዎች መኖር እንደሌለበት ስለታመነበት ማንኛዉም
አይነት ተቃዉሞ መደረግ እንደሌለበት እናስታዉቃለን:: ምክንያቱም የፊታችን ጁምአ መንግስት የኢድ ሰላትን ለማጨናገፍ
ያመቸዉ ዘንድ የተለያዩ ሴራዎችን ማሴሩን በተጨባጭ ተደርሶበታል:: ከጁምአ ሰላት ቡሃላ ህዝበ ሙስሊሙ በተለያዩ
ከተሞች በሚገኙ መስጂዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞዉን ሲያሰማ የነበረ ሲሆን መንግስትም ይህንን ተቃዉሞ ተገን
በማድረግ ረብሻ በመፍጠር የኢድ ሰላታችንን ተሰብስበን እንዳንሰግድ ለማድረግ ስላሰቡ ይህንን ሴራቸዉን ለማክሸፍ
ሲባል የፊታችን ጁምአ በመላዉ ሀገሪቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዝምታ ያሳልፈዉ ዘንድ እናሳስባለን:: ማንኛዉም አይነት
የዝምታም ሆነ ሌላ ተቃዉሟችንን የሚገልፁ ነገሮችን ማድረግ እንደማይገባን እናሳስባለን:: በታላቁ አንዎር መስጅድም
ተቃዉሞ የሚደረግ ከሆነ የመስጂዱን ኢማም በግርግር ለመደብደብና ጥቂት አክራሪዎች ጥቃቱን ፈፀሙት በማለት በሙስሊሙ
ላይ በማላከከ የኢድ ሰላትን በጀምአ በአንድ ቦታ እንዳይሰገድ ለማድረግ እንዳማራጭ ዘዴ ስለያዙ በታላቁ አንዎር
መስጂድም ምንም አይነት ተቃዉሞ መደረግ እንደሌለበት እናሳስባለን:: ህዝበ ሙስሊሙም በየመኖሪያ አካባቢዎች በሚገኙ
መስጂዶች የጁምአን ሰላት ይሰግድ ዘንድ እናሳስባለን:: በአንዎር መስጂድ በብዛት ሆነን መስገዳችን ተቃዉሞ ባናሰማም
በህዝቡ ቁጥር ተገን በማድረግ አላማቸዉን ለማሳካት የተለያዩ ሴራዎችን ሊያሴሩ ስለሚችሉ አብዛኞቻችን ከረመዳን
በፊት ስንሰግድባቸዉ በነበሩ መስጂዶች የጁምአን ሰላት መስገድ እንደሚኖርብን እናሳስባለን!! ይህንን መልዕክት
በተለያዩ መንገዶች አስተላልፍ!!! "ብልጦች አይደለንም ብልጣብልጦችም አያታልሉንም"
No comments:
Post a Comment