Tuesday, August 14, 2012

የ Google+ page የከፈተ ሲሆን የ“ድምጻችን ይሰማ


ፌስቡክ ሙስሊሙ ህብረተሰብ እየደረሰብትን ያለውን የመብት ረገጣ ለህብረተሰቡ ከማሳወቅ አንጻር ያለውን ጉልህ ሚና ለማጨናገፍ አንዳንድ ባለስልጣናት እንዲዘጋ እየጠየቁ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ እኩይ ዐላማቸው ተሳካላቸውም አልተሳካላችው አማራጭ መረጃ መለዋወጫ ዘዴ ዎችን አዘጋጅቶ መቀመጥ ብልህነት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር “ድምጻችን ይሰማ” አስተማማኝ የሆነ ቀጣይነት እንዲኖረውና በፌስቡክና ትዊተር ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጥ የ Google+ page የከፈተ ሲሆን የ“ድምጻችን ይሰማ” ተከታታዮች የነበራችሁ ሁሉ የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ከወዲሁ የፔጁ አባል እንድትሆኑ እናሳስባለን፡፡ Google+ ከዚህ ቀደም ላልተጠቀማችሁ እንዴት አባል መሆን እንደምትችሉ ከዚህ በታች ባጭሩ ተቀምጧል፡፡ 1. የጉግል አካውንት ከሌሎት ይክፈቱ 2. https://gplus.is/DimtsachinYisema ወይም https://plus.google.com/100427562987310232548/posts የሚለውን ሊንክ ይክፈቱ 3. ከዚህ ቀደም Google+ ተጠቅመው የማያውቁ ከሆነ ከዚህ ጽሁፍ ጋር በተያያዘው አነደኛ ምስል ላይ እንደሚያዩት Join Google+ የሚለውን አይከን ይጫኑ፡፡ ከዚያም በሁለተኛው ምስል ላይ እንደሚታየው Upgrade የሚለውን ይጫኑ፡፡ አሁን የGoogle+ ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበዋል ማለት ነው፡፡ 4. በመቀጠል ከላይ የተቀመጠውን https://gplus.is/DimtsachinYisema ወይም https://plus.google.com/100427562987310232548/posts ሊንክ ሲጫኑ የ“ድምጻችን ይሰማ” ገጽ በሶስተኛው ምስል ላይ እንደሚታየው ይመጣል፡፡ የ“ድምጻችን ይሰማ” ተከታታይ ለመሆን በምስሉ ላይ እንደሚታየው Follow የሚለውን ይጫኑ፡፡ ከዚያም በአራተኛው ምስል ላይ እንደሚታየው Following የሚለው ላይ ምልክት ያድርጉ፡፡ ይህን ሲጨርሱ በአምስተኛው ምስል እንደሚታየው Following የሚል ጽሁፍ ከመጣ የ“ድምጻችን ይሰማ” የ Google+ page ተከታታይ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ በቀጣይነትም እንደ አማራጭ የተያዙ ተጨማሪ የመረጃ መለዋወጫ መንገዶችን የምናስተዋውቃችሁ ሲሆን እስከዛው ሁላችንም የ“ድምጻችን ይሰማ” የ Google+ page ተከታታይ መሆናችንን እንድናረጋግጥ አደራ እንላለን፡፡ የ“ድምጻችን ይሰማ” የ Google+ page ተከታታይ ይሁኑ (5 photos)

No comments:

Post a Comment