ዛሬን
ጨምሮ ባሳለፍናቸው አራት የረመዳን ጁመዓዎች የኢትዮጵያ ሙስሊም የደረሰበትን የብስለትና የአይበገሬነት ደረጃ
በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድምና እህቶቻችን ታስረው በመቶዎች የሚቆጠሩቱ ደግሞ ተደብድበው ነገር ግን የበለጠ ትግላችን
ተጠናክሮ ለትግል ታሪካችን ድንቅ ምእራፍ ጨምረንለታል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ፍፁም ሰላማዊ በዲኑ ለመጡበት ደግሞ ቅንጣት
የማይደራደርና ለዲኑ እስከመጨረሻው ዘብ እንደሚቆም በድጋሚ አሳይቷል፡፡ ጌታችን አላህ በቁርዓኑ ‹‹የአላህን
ብርሀን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይከጅላሉ አላህ ግን ዲኑን መሙላት እንጂ እንቢ ይላቸዋል›› አይደል ያለን፡፡ እኛ
የአላህ ባሮች ነን ጌታችን ደግሞ አላህ ነው፡፡ አላህ ታላቅ ነው!! አላሁ አክበር!! እያልን ለዲናችን መከበር
ዘብ እንቆማለን!! ለመብታችን እስከ መጨረሻው ፀንተን እንታገላለን!! አላሁ አክበር!! አላህ ታላቅ ነው!!
ለመንደርደሪያ ይህንን አልን እንጂ ዛሬ የምናካፍላችሁ ምናልባት የብዙዎቻችንንትርታ ያደመጠ ነው ብለን ያሰበነውን ለውድ ኮሚቴዎቻችን የተፃፈ አንድ ደብዳቤ ነው፡፡ እስኪ እናንተም የልችሁን ፃፉ፡፡ ኢንሻአላህ አንድ ቀን በመድብል ተዘጋጅቶ ይደርሳቸዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ይድረስ ለውድ ኮሚቴዎቻችን
ባሸከምናችሁ ውክልና ለዲነል ኢስላም ስትሉ ሁሉ ነገራችሁን እርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በእስር ላይ የምትገኙ ውድ ኮሚቴዎቻችን እንደምን አላችሁ? ለሰባት ወራት የግል ስራችሁን ጥላችሁ የሰጠናችሁን ሀላፊነት ዳር ለማድረስ ሌትና ቀን ደፋ ቀና ስትሉ ያየን ሁላ ውድ የኢስላም ልጆች መሆናችሁን ደግመን አረጋግጠናል፡፡ የሰጠናችሁ ውክልና በእርግጥም የሚገባችሁ ብርቅዬ ኡስታዞቻችን ናችሁ፡፡ በዚህ ሁላ ጊዜ ከህዝብ የወጣችሁ የህዝብ አገልጋዮች በመሆን የከፈላችሁት መሰዋዕትነት ታላቅ ነበር፡፡ ለሹመኛ ባለማጎብደድ የህዝብ ሙስሊሙን የልብ ትርታ ለሚመለከተው ሁሉ በሚያስደንቅ ሰላማዊ ሂደት አድርሳችኋል፡፡ ዲናችንን ለመበረዝ የተላከውን መጤ አስተሳሰብና ሳንወድ በግድ የተጫነብንን መጅሊስ በመቃወም ለተነሳንለት ቁርጠኛ ዓላማ በቁርጠኝነት ታግላችኋል፡፡ የአላህን እርዳታን ብቻ በመከጀል ለቆምንለት ዓላማ ታግላችኋል፡፡ ግዜያችሁን፣ ስራችሁን፣ እውቀታችሁን ያላችሁን ነገር ሁላ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄና ለዲን መከበር ስትሉ መሰዋዕዓት አድርጋችኋል፡፡ ይህ እናንተን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሽተን የምንናገረው ሳይሆን በትክክል መሬት ወርዶ ያየነው እውነታ ነው፡፡ አላህ ይህን የገዘፈ መልካም ስራችሁን ይቀበላችሁ! እኛ በሀገርም በውጪም ያለን ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የናንተ ተወካዮቻችን መልካም ስራ መስካሪዎች ነን፡፡
በእርግጥ የናንተን ውድ ልጆቻችን የመታሰር ዜና በሰማን ሰዓት ቁጣችን የምንይዘው የምንጨብጠው አሳጥቶናል፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ በናንተ ላይ የተፈፀመው የህግ ጥሰት በኛ ውክልና የሰጠናችሁ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመ ህገወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ተግባር ነውና፡፡ በመሆኑም ይህን ስርዓት የለሽ የህግ ጥሰት በመቃወም በታላቁ አንዋር መስጂድ ቁጣችንን በጥቂቱ ስንተነፍስ በሺዎች የምንቆጠር ታስረናል ዱላም አርፎብናል፡፡ ይሁንና ለሰባት ወራት አብረን ሳለን ያሳያችሁን ሰላም ወዳድነት፣ አርቆ አሳቢነት፣ ህግ አክባሪነት፣ ከስሜታዊነት ርቆ ለዲን ተቆርቋሪ መሆንና እስከ መጨረሻው በመታገል ለዲናችን ዘብ መቆምን ነበርና ይህ ለዲናችን ስንል የምንከፍለው ትንሹ መሰዋዕዓትነት ሆኖ ትግላችንን ወደ ወሳኝ ምእራፍ አሸጋግሮታል፡፡
ውድ ኮሚቴዎቻችን ያ ስንመለከተው የቆየነው መልካም ስራችሁ፤ ትላንት ውሸትን አጋልጦ ሀቅን ሲናገር በጉጉት በየሳምንቱ እንሰማው የነበረው ድምፃችሁ ዛሬ ከአጠገባችን ሲርቅ ልባችን በሀዘን ተሞልቷል፡፡ ያ ይተላለፍልን የነበረው ብልህነትና አስተዋይነት የተሞላበት መልክታችሁ ሲቋረጥ ውስጣችን ቆስሏል፡፡ አይናችን አይናችሁን ማየት ባለመቻሉ በረጅሙ አንብቷል፡፡ ትላንት የገባችሁትን ቃል ዛሬ ፈፅማችኋል፡፡ ለኢስላም ሲባል የሚከፈለውን መሰዋዓትነት እንከፍላለን ትሉን ነበር እነሆ መራራውን መሰዋዓትነት ከፈላችሁ፡፡ እናንት ውድ የኢስላም ልጆች በምን ሁኔታ ላይ ሆናችሁ ይሁን? ለዲን ስትሉ የሞቀ ቤታችሁን፣ ልጅና ሚስቶቻችሁን ጥላችሁ አሁን የምትገኙበት ጨለማ ቤት እንዴት አድርጓችሁ ይሁን? ያ አላህ! ባሪያህን የምትንከባከብ ጌታ ነህና አንተው ተንከባከብልን! ሀያሉ ጌታችን ከበደለኞች ተንኮል ሁሉ ጠባቂ ነህና እኚህ ውድ ልጆቻችንን አንተው ጠብቅልን! ያ አላህ!!!!
ውድ ኮሚቴዎቻችን አይናችን አይናችሁን ለማየት ናፍቋል፤ ጆሮዋችን ድምፃችሁን ለማዳመጥ ጓጉቷል፤ ልቦናችን መልዕክታችሁን ለመስማት ተንጠልጥሏል፡፡ በናንት መታሰር የሚቆም አንዳችም ነገር የለም፤ ይልቁንም የበለጠ ጥንካሬን የበለጠ ፅናትን ይሰጠናል እንጂ፡፡ ይህንን ደግሞ ላለፉት አራት ተከታታይ የረመዳን ጁመዓዎች በመላው አለም የሚገኙ ለተንገላታችሁለት አላማ እራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ቁርጠኛ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የታየው ከፍተኛ ተቃውሞ እጅግ መስካሪ ነው፡፡ የተከፈተብንን የመብት ጥሰት ከማን እንደሆነ ለይተን በግልፅ አውቀናል፡፡ መብት የማስከበር ሂደቱን ዳር ለማድረስ ደግሞ ፀንተን እንታገላለን፡፡ እናንተ ሁል ግዜም ኮሚቴዎቻችን ናችሁ፡፡ ትግሉን የሚያስቀጥልና የምንሰማው አስተባባሪ ሊኖረን ግድ ነውና ያንን እያደረግን ነው፡፡ ግና የናንነት የኮሚቴዎቻችን መታሰር የወኪልነት ቦታችሁን ከልቦናችን በጭራሽ አይፍቀውም፡፡ ዛሬ በየመንደሩ እየዞሩና በጥቅማጥቅም በመደለልና በማስፈራራት እንደማናቃችሁ እና እንድናወግዛችሁ የሚወተውቱን ሃይሎች ልቦቻችን ውስጥ ያላችሁን ስፍራ ቢያውቁ ኖሮ ምንኛ ባፈሩ ነበር፡፡ የናንተን በእስር መቆየት መቼም ቢሆን አንታገሰም፡፡ በናንተ የሚመጣብንን ፈፅሞም አንደራደርም፡፡ እስክትፈቱ ትግላችን በፅናት ይቀጥላል፡፡ እናንተን ከእስር አጉረው እንዳሻቸው አድርገው አስቀድመው የጨረሱትን የምርጫ ድራማ እንድንታደም እያስገደዱን ይገኛሉ፡፡ ነገር አለሙ ሁሉ የመጅሊስ ምርጫነት መልኩን በመሳት ፈፃሚውም አስፈፃሚውም የሃይማኖት መሪ ሳይሆን ሌላ አካል በመሆን የመገናኛ ብዙሃኖቹ ገና ከአሁን ስለፍትሃዊነቱ እየደሰኮሩለት ይገኛል፡፡ ግና እናንተን ለእስር ዳርገን ይህንን መሰሉን ድራማ የማየት ወኔው እንዴት ሊኖረን ይችል ይሆን!!! እንጃ በኔስ በኩል!!! እናንተ ታስራችሁ ምርጫ የሚባል ነገር አይታየኝም፡፡ እናንተ ታስራችሁ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት የምርጫ ሂደት ህገ ወጥና በምንም መልኩ የማልቀበለው ነው፡፡ እናንተ ተፈታችሁ እንደተለመደው ተነጋግረን የምንደርስበት አቋም ሳይኖር በቲቪም ይሁን በሬድዮ እንደፈለጋቸው ቢለፍፉ እነርሱ እንዳልሰሙን እኛም አንሰማቸውም፡፡ ጆሮዋችን እንደሆን እኛው ዘንድ ነው ያለው፡፡ በሚድያ የሚሰሩት ሸፍጥና ድራማ የለመድነው ስለሆነ አይገርመንም፡፡ እውነታውን ለማወቅ እነርሱ የሚናገሩትን ገልብጠን በተቃራኒው መረዳት ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡
ውዶች በመጨረሻም የሁሉ ነገር ባለቤት አላህ ነው፡፡ አላህ ከናንተ ጋር ይሁን፡፡ እኛም እስከመጨረሻው ከጎናችሁ ነን፡፡ የትግላችን ሁለተኛው ገፅታ ዱዓችን ነው በዚህ በተከበረው የረመዳን ወር ቀን በፆም አፋችን አላህ እንዲነስረን በደለኞችን እንዲይዝልና እናንተን እንዲያስፈታልን አጥብቀን ዱዓ በማድረግ ላይ ነን፡፡ ከዚህ በፊት ይደርስብን የነበረውን በላ እንዲያነሳልን ሰበብ የሆነን የሰደቃ ፕሮግራም ዛሬ በመላው አለምና በየቤቱ ይህነኑ ታሳቢ በማድረግ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ውጤቱንም በአይናችን እያየነው፤ በጆሯችን እየሰማነው፤ ከኛ አልፎ በሌሎች በውል እየታወቀ ነው፡፡የአወሊያውን የሰደቃ ፕሮግራም ‹የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ለማወክ› ማለታቸው ሲታወስ የመላው አለም የሰደቃ ፕሮግራሞችንስ ምን ሊሏቸው ይሆን? በኛ ውክልና ዳፋ የሚደርስባችሁን ስቃይ ጀሊሉ መፍትሄ እንዲያበጅለት ለይል በመስገድ በጀመዓና በተናጠል በሁሉም መስጂዶቻችን ውስጥ እጆቻችን ወደ አላህ ተዘርግተው አይኖቻችን እያነቡ ዱዓ እያደረግን ነው፡፡ መቼም ከዚህ ሁሉ የብሶት እንባ መሀል አላህ እሺ ብሎ ታሪካዊ ምላሽ የሚሰጠው እንደሚኖር ምንም ጥርጥ አይኖረንም፡፡ ‹‹ ሀስቡን አላህ ወኒዕመል ወኪል›› መመኪያችን አላህ ነው ምን ያምር መመኪያ!!!

No comments:
Post a Comment