የወያኔ ጦር በአንደኛ ደርጃ ተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ተዛዝ ተላለፈ ።
Facebook
ከቅርብ ግዜ ወዲህ የወያኔው ቡድን በኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ
ህገመንግስታዊ መብታቸው እንዲከበር ድምጻችን ይሰማ በሚል መሪ መፈክር በአንድነት በረቀቀ እና በተደራጀ መልኩ
ሰላማዊ ትግል በማካሄድ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። ይህ በመላው ሀገሪቱ ስር የሰደደው የሙስሊሙ ተቃውሞ የወያኔ ተራ
ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሳይበግረው ከእለት እለት በመላ ሀገሪቱ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ ለውያኔ እራስ ምታት
እየሆነበት መምጣቱ የማይካድ ሃቅ ነው።
ጥላውን የማያምነው ወያኔ የነብርን ጭራ ከያዙ አይለቁ
ከለቀቁ ? ነገር ሆኖበት የሃገሪቱን ጦር በአንደኛ ተጠንቀቅ ከማሰማራት አንስቷ ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ወገናችን
ላይ የጀመረው አስቃቂ የግድያ እና የአፈና ዘመቻ በቅርቡ አለማችንን ጉድ ካሰኘው ከበርማ ሙስሊሞች ዘግናኝ
ድርጊት የከፋ ሊሆን እንደ ሚችል መጤውን የወያኔን ቡድን ማንነት ጠንቕቀው የሚያወቁ ኢትዮጵያውያን ውስጥ፡አዎቂ
ምንጮች ይገልጻሉ።
እነዚህ ምንጮች በየወያኔ
ስረአት ውስጥ በተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ ቡድኑ መፈረካከስ መጀመሩን በመግለጽ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሰራዊት ይህን
በጭቁኑ ወገናችን የትግራይ ህዝብ ስም የሚነግደውን አናሳ የወያኔ ቡድን ነትሎ በመምታት ከሰፊው ህዝባችን ጫንቃ
አሽቀንጥሮ ለመጣል ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን የጀመረውን የሃይማኖት ጥያቄ በመቀላቀል ወደ አጠቃላይ የመብት ጥያቄ
ትግሉን በማሸጋገር የዚህን ቡድን ስረአት ቀብር ማረጋገጥ፡ እንደ ሚጠበቅብን አበክረው መክረዋል።
ከዚህ በታች በደሴ ሙስሊም ወገናችን ላይ ያለፈው የጁመአ ጸሎት ስረአት በወያኔው አናሳ ቡድን የአጋዚን ጦር የተፈጸመው አስቃቂ ግፍ መሆኑንን እንገልሳለን ።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር
No comments:
Post a Comment