ድምፃችን ይሰማ
በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊም ታሪክ ሰራ!!!በመላዉ ኢትዮጲያ የሚገኙ ሙስሊሞች ከኢድ ሰላት ቡሀላ ከፍተኛ ተቃዉሟቸዉን በማሰማት በኢትዮጲያ ታሪክ ዉስጥ የማይረሳ ታሪክ መስራታቸዉ ተገለፀ:: በመላዉ ሀገሪቱ የተካሄዱት ተቃዉሟዎች ፍፁም ተመሳሳይ ይዘት የነበራቸዉና ፍፁም ሰላማዊ ሆነዉ የተካሄዱ ነበሩ:: በተቃዉሞ ሰልፍ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ድምፃችን ይሰማ; ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ; በግፍ የታሰሩ ንፁሀን ሙስሊሞች ይፈቱ; ምርጫችን በመስጂዳችን; ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫ የለም; ሀስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል; ህገ መንግስቱ ይከበር, ኢስላም ሰላም ነዉ; እኛ አንድ ነን አንለያይም; አሻዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ; አሸባሪዎች አይደ
ለንም; ጥቂቶች አይደለንም; ጥያቄዎቻችን ይመለሱ; ኢቲቪ
ዉሸታም; ኢቲቪ ሌባ; ዉሸት ሰለቸን; ፖሊስ የህዝብ ነዉ; ዉሾቻችሁን እሰሩልን; አፈናና እስራቱ ይቁም; የሚሉ
በርካታ መፈክሮች ህዝበ ሙስሊሙ በመላዉ ሀገሪቱ ሲያሰማ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል:: ተቃዉሞ ከተካሄደባቸዉ ከተሞች
መካከል በጣም በጥቂቱ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:: በአዲስ አበባ ከተማ, በጅማ ከተማ, በአዳማ ከተማ, በድሬዳዎ
ከተማ, በደሴ ከተማ, በአማራ ክልል በወሎ ከሚሴ ከተማ,በአማራ ክልል በደጋን ከተማ, በሰበታ ከተማ, በአፉር ክልል
በዞን አምስት በዳዌ እና በኢሊወሀ ከተሞች, በአጋሮ ከተማ, በትግራይ ክልል በእደጋሀሙስ ከተማ, በወለጋ ጊንቢ
ከተማ, በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ, በሮቤ ማዳወላቡ ከተማ , በወላይታ እና በመጫራ ከተሞች ሰላማዊ ተቃዉሟዎችን
ህዝበ ሙስሊሙ ካሰማባቸዉ ከተሞች መካከል በጣም ጥቂቶች ናቸዉ:: በሁሉም ቦታዎች የተካሄዱት ተቃዉሞዎች በሰላም
የተጠናቀቁ ሲሆን በአዳማ ከተማ በተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግን ፓሊስ የከተማዎን ሙስሊሞች በመደብደብ ለመበተን
መሞከሩን ምንጮቻችን ገልፀዎል:: በመላዉ ሀገሪቱ ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ህዝበ ሙስሊሙ አረጋግጧል!!!
አላሁ አክበር!!!
No comments:
Post a Comment