በአንድ ብር ታሪክ እንስራ!
በመብት ረገጣና የድምፅ መታፈን የተሞላው ያሳለፍነው ሙሉ አንድ አመት እያማረረን ቢሆንም ብዙ ነገር እያስተማረንም ይገኛል፡፡ ላነሳናቸው ግልፅና ቀላል የመብት ጥያቄዎች እንደሰላማዊነታችን መልሳችን በሽልማት ታጅቦ ሊቀርብልን ሲገባ ስቃይ የለት ከለት ክፍያችን ሆኗል፡፡ የመልእክታችን እንደራሴዎች የሰላም አምባሳደሮቻች ተብለው ሊሸለሙ ሲገባ እንደወንጀለኛ ዘብጥያ ተጥለዋል፡፡ ከዚህ አልፎ እያንዳንዷን ደቂቃና ሰአት በከፋ ስቃይና እንግልት እንዲያሳልፉ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ ይሄን ሁሉ አድርገው እንኳን ለህዝብም ቅንጣት ታህል ክብር ባላሳየ ሁኔታ ጥያቄዎቻችንን ደፍጥጠው በእኩይ ተግባራቸው በማንአለብኝነት እየ

ገፉበት ይገኛሉ፡፡ እናም ይህ ጉዳይ
‹‹በቃ!›› ሊባል ይገባል፤ የስቃዩ ምእራፍ ሊዘጋ ይገባል፡፡ የተናቀው ህዝብ ታሪኩን ሊያድስ ግዜው ከመቼውም በላይ
አፍጥጦ መጥቷል፡፡ ሰላማዊ ትግላችን ስልቱን እየቀያየረ እስከዛሬ እንደዘለቀ ሁሉ ለዚህ ታሪክ የማደስ አኩሪ ገድል
መዳረሻ ይሆን ዘንድ የህብረተሰብ ንቅናቄ ወሳኝ በመሆኑ ‹‹በአንድ ብር ታሪክ እንስራ›› ታላቅ ሃገር አቀፍ
የህብረተሰብ ንቅናቄ ዘመቻ እንደ ቅድመ ዝግጅት ስራ ሊከፈት ነው፡፡ ስለዚህ ዘመቻ ምንነት ከማውራታችን በፊት
ይህንነ ፅሁፍ በማንበብ ላይ የምትገኘው ወንድም እና የምትገኚው እህት ማንበብህን/ማንበብሽን እዚህ ጋር ግቱትና
አንድ ጥያቄ ለራሳችሁ አቅርቡ፡፡ እውን በአንድ ብር ታሪክ መስራት ከተቻለ እኔ የዚህ ተቋዳሽ ለመሆን ምን
ይሳነኛል? በአንድ ብር ታሪክ መስራት እየተቻለ ወኔውና ቁርጠኝነቱን ካጣሁ ከህሊና፤ ከታሪክም ሆነ ከዲን ተወቃሽነት
የማመልጥበት ቀዳዳ ይኖር ይሆን?
ለነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መነሳሳትና ቁርጠኝነት በውስጣችሁ የተፈጠረ ወንድምና እህቶች ከዚህ በኋላ ለሚኖረው ‹‹በአንድ ብር ታሪክ እንስራ›› የዘመቻ ጥሪ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ቀጣዩን የፅሁፉን አካል አብረን እንድንዘልቅ ግብዣችን ነው፡፡
ይህ ጥሪ ምን እንደሚፈጥርባችሁ መገመት አየዳግትም፡፡ ምክንያቱም አንድ ብር ለአንድ ልብ፤ አንድ ብር ለአንድ ወገን እና መሰል ጥሪዎች ላይ በሙሉ ወገንተኝነት ምላሽ ስትሰጡ ኑራችኋልና፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ አዲስ ጥሪ በራችሁን እያንኳኳ ነው፡፡ ‹‹በአንድ ብር ታሪክ እንስራ››፡፡ በዚህ ታሪክ ላይ አንድ ብርህ/ብርሽ ብቻ ሳይሆን የሚፈለገው በብርህና በብርሽ አንተው/አንቺው ታሪክ መስራት ይጠበቅባችኋል፡፡ የአንተ፤ የአንቺ እና የእኛ የአንድ ብር ስራ በእርግጥም የጋራ ታሪክ ሆኖ እናየዋለን፡፡ አንድ ብር በመጠን ደረጃ ሃብታምን ከደሃ የማይለይ ነው፡፡ በውጤት ደረጃ ግን የአንተና የአንቺ አንድ ብር ከድማሚት በላይ ድምፅ ፈጥሮ ጠላትን የማስበርገግና ከነጋሪት በላይ እስተጋብቶ የትግል አጋርን የማሰባሰብ ብርቱ ኃይል ይኖረዋል፡፡
አውቀው የተኙትንና ድምፃችንን ለመስማት በትዕቢትም ይሁን በመዘናጋት አልሰማ በማለት ህዝብን እያንገላቱ ያሉትን አካላት ማስተባበያ ለመስጠት በማይችሉበት መልኩ መልእክታችንን ለማድረስና መብታችንን ሊሰጡን ካልቻሉ ለመውሰድ ከምናደርገው ይፋ ዘመቻ አንዱ የሆነውን የህብረተሰብ ንቅናቄ እንዴት እንደምንተገብረው አብረን እንመልከት፡፡ ከዚህ በፊት ግን ይህንን መልእክት ከቀደምቶቹ የሚለየውና ሁላችንም ማወቅ ያለብን ጉዳይ፡-
የድምፃችን ይሰማ አባልነትና የትግሉ አጋርነት አንድ ተጨባጭ ነገር ካልሰራን ማንበብ ብቻውን ታሪክ አይሰራም፡፡ ከፌስቡክ ግድግዳ ጀርባ የምናደርጋቸው (like, share, comment, tag....) ለዚህ ትግል ወሳኙን ድርሻ እየተወጣ ቢሆንም ይህ መልእክት ግን ተግባራዊ ምላሽን ይፈልጋል፡፡ እናም የፌስቡክ አስተያየት ብቻውን ታሪክ ስለማይቀይር በዚህ መልእክት አንድ እርምጃ ወደፊት እናምራ፡፡
‹‹በአንድ ብር ታሪክ እንስራ›› ዘመቻን ቀላልነት ለማሳየት ቀላል ቀመር ብንከተል እንኳን
• እስከአሁን ባለው መረጃ አሁን የምታነቡትን የድምፃችን ይሰማ ፔጅ ከ 15 ሺህ በላይ አባላት መልእክቱን በቀጥታ በፌስ ቡክ ግድግዳቸው ላይ ያገኙታል፡፡
• በድምፃችን ይሰማ ፔጅ የሚተላለፍ አንድ መልእክትን ከ150 እስከ 200 ሰዎች ለሌሎች ጓደኞቻቸው ሼር ያደርጋሉ፡፡
• ሁላችንም እንደምናውቀው የተወሰኑ ግለሰቦች ጥቂት ጓደኞች ብቻ ሊኖራቸው ቢችልም በርካታ የፌስ ቡክ ደንበኞች ግን ከ 100 እስከ አምስት ሺህ የሚደርሱ ጓደኞች አሏቸው፡፡
• አንድ የድምፃችን ይሰማን መልእክት በአማካኝ 150 ሰው ሼር ቢያደርግና አንደ ደንበኛ ደግሞ በአማካኝ 200 ጓደኞች ቢኖሩት መልእክቱ ለ30 ሺህ ሰው ይደርሳል ማለት ነው፡፡
• ይህ ቁጥር መልእክቱን በቀጥታ ከሚያገኙት 15 ሺህ አባላት ጋር ሲደመር 45 ሺህ ይደርሳል፡፡
‹‹በአንድ ብር ታሪክ እንስራ›› ዘመቻ ተካፋዮች ስራቸውን የሚጀምሩት እዚህ ጋር ነው፡፡
• አንድ ሰው በየእለቱ አንድ ብር ለማውጣት ከአላህ ጋር ቃል ይጋባል፡፡
• በዚህ አንድ ብርም አንድ በድምፃችን ይሰማ የሚተላለፍ እለታዊ አጭር የስልክ መልእክት (አንዳንዴ እንዳስፈላጊነቱ ሊዘለል ይችላል) ለ3 ሰዎች ያስተላልፋል፡፡
• ከላይ ያሰላነው 45 ሺህ የዘመቻው ተሳታፊ በሙሉ አቅሙ ከሰራ በአንድ ቀን 135 ሺህ ፌስ ቡክ ተጠቃሚ ያልሆነ ሰው ትክክለኛና ቀጥተኛ መረጃ ይደርሰዋል ማለት ነው፡፡
• ሶስተኛና አራተኛ ወገኖች የሚያስተላልፉትን መልእክት ብንተወውና 135 ሺህ ሰዎች እለታዊ ግዴታቸውን መወጣት ቢችሉ በአንድ ቀን 405 ሺህ ሰዎች አጭር የስልክ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡
• ይህም አሃዝ ቀድሞ ከደረሳቸው 135 ሺህ ሰዎች እና የየፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ጋር ሲደመር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የዘመቻው ተሳታፊ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህንን እለታዊ መልእክት በሳምንት ስናሰላው ከሶስት ሚሊየን አምስት መቶሺህ ሰዎች በላይ የየእለቱ መነጋገሪያ አጀንዳቸው የኛው ወሳኝ አጀንዳ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በህብረተሰብ ንቅናቄ ዘመቻ ይህ በጣም ከፍተኛ ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል፡፡ በሃገራችን ተጨባጭ ምናልባት መደበኛ የራዲዮና የቴሌቪዥን መረጃዎችን ከሚያገኘው ህዝብ በላይ የኛ መረጃ በየቤቱ ይዳረሳል፡፡ የሰማው ለሌላው ሲያሰማ ደግሞ ውጤቱ እልፍ ይሆናል፡፡ ለዚህ ትንግርት መሳይ ግን ደግሞ ቀላል ውጥን መሳካት የአንተ/የአንቺ ሚና ሁሉንም ነገር ያጠቃለለ ነው፡፡ አንተ/አንቺ ከተሳፈተፍሽ ውጥኑ ሙሉው ይሳካል፡፡ አንተ/አንቺ ካልተሳተፍሽ ደግሞ ውጥኑ መና ይሆናል፡፡ ያሳለፍነው አንድ አመት ጀግንነትና የአላማ ፅናታችሁ ግን በአንተ/በአንቺ ምክንያት ይህን መሰል ታሪካዊ ዘመቻ ከታቀደው በላይም ተሳክቶ እንደምናየው ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡ በመሆኑም፡-
• ድምፃችን ይሰማ ፔጅ በየእለቱ (አንዳንዴ እንዳስፈላጊነቱ ሊዘለል ይችላል) አንድ ወቅታዊ አጭር የስልክ መልእክት በግድግዳዋ ላይ ትለጥፋለች
• ለጀመርነው ትግል መነሻ የሆኑና በመሃልም ተፈጥረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉ ሌሎች የፌስ ቡክ ግሩፖችና ታዋቂ ግለሰቦች ይህንን ስራ ለማቀላጠፍ እንደተለመደው ከፍተኛና ቋሚ ቅስቀሳ ያደርጋሉ
• ከላይ በተላለፈው መሰረት እያንዳንዱ የድምፃችን ይሰማ አባል እለታዊ አጭር የስልክ መልእክቶችን በሞባይሉ በመፃፍ ለሶስት ፌስ ቡክ ለማይጠቀሙ ሰዎች በመላክ እለታዊ ግዴታውን ይወጣል፡፡
በአንድ ብር ታሪክ ለመስራት ዝግጁ ነን?

No comments:
Post a Comment