ምርጫችን በመስጅዳችን !!!
ይህንን ሀሳብ ለወራት በመላው ሀገራችን የሚገኙ ሙስሊሞች ሲያዜሙት የከረሙት መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የህዝብን ድምፅ መደፍጠጥ እና የእኔ አውቅልሀለው ድርቀት የለከፋቸው አካላት ምርጫቹን እናንተ በፈለጋቹት ቦታ ሳይሆን እኛ ባሰናዳንላቹ የትወና መድረክ ነው ማካሄድያለባቹ ሲሉን ከርመዋል። ለዚህ ግልፅ የመብት ረገጣ ውሀ ማይቋጥሩ ምክንያቶችንን ሲደረድሩ ከርመዋል። በመሰረቱ እነርሱ ያስቀመጡዋቸው ችግሮች እውን እንደተባለው ምርጫውን በመስጅድ ለማካሔድ ችግር ሆነው ቢሆን ኖሮ እንኳ ለመምረጥ ተቸገርን እና ተባበሩን ብለን መጠየቅ የነበረብን እኛ ነበርን እንጂ እነርሱ ገና ለገና ምርጫው መስጅድ ውስጥ ከ

ተካሔደ
“ሀይማኖቱን የሚያገለግል ቅን የአላህ ባርያ ይመረጣል!” ብለው ስለሰጉ ምናባዊ (በተጨባጭ የሌሉ) ችግሮችን
በመደርደር ምርጫውን ከመስጅድ ውጭ ለማድረግ መሯሯጥ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ነች ይሏታል” እንደሚባለው
“ለማጭበርበር ያቀዱትን ምርጫ መስጅድ አይመችም ይሉታል” ካልተባለ በስተቀር እውን እንደተወራው ለኛ ከማሰብ የመነጨ
አይደለም!!!። እኛ ራሳችን ስለራሳችን እናውቃለን እነርሱ ስለኛ የሚሻለንን እናየሚበጀንን ለመንገርም ይሁን
ለማዘዝ እውቀቱም መብቱም የላቸውም። በዚህ ፅሁፍውስጥ ምርጫውን በመስጅድ ማካሔድ እንዴትይቻላል ለሚለው ነጥብ
በግርድፉ ምላሽ ይሰጣል። ሙሉ ዝርዝሩን ሰሞኑን ከወጣው “የኢትዮጵያ መጅሊስ አጣዳፊ ችግሮቹ እናአማራጭ መፍትሔዎች”
ከሚለው መፅሐፍ ማግኘት ይቻላል።
አማራጭ የመጅሊስ መዋቅር እና የምርጫ ስርዓት
1:- የጁምዓ መስጅድ መጅሊስ (የእስልምናጉዳይ ምክርቤት)
በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ጁሙዓ ሰላት የሚሰገድባቸው ማናቸውም አይነት መስጅዶች የአዲሱ መጅሊስ የበታች እርከንይሆናሉ። በአንድ አከባቢ ወይም መንደር የሚገኙ የጁምዓ ሰላት የማይሰገድባቸው ሶስት ኩታገጠም (ተጎራባች) መስጅዶች በአንድ ላይ በመሆን አንድ የጁምዓ መስጅድ የመጅሊስ መዋቅርን ይመሰርታሉ። ነገር ግን የመሰል ተጎራባች መስጅዶች ብዛት ከሶስት ካነሰ በዓቅራቢያቸው ከሚገኝ የጁምዓ መስጅድ ጋር እንዲጣመሩ ይደረጋል።
በዚህ መልኩ እነዚህ የጁምዓ መስጅዶች ዝቅተኛው የመጅሊስ መዋቅር የሚሆኑ ሲሆንበነዚህ መዋቅሮች ውስጥ ለቡሉግ (አቅመ አዳም/ ሔዋን) የደረሱ የአከባቢው ሙስሊም ምእመናን በአባልነት ተመዝግበው የሚፈለግባቸውን አመታዊ መዋጮ በማዋጣት የእርከኑን ጠቅላላ ጉባዔ ይመሰርታሉ። ለወረዳ፣ ለክልል እንዲሁም ለፌደራል መጅሊስ አባልነት ሊሰሩላቸው የሚችሉ ተወካዮቻቸውን በሶስት ምድብ (ከዑለማ፣ ከምሁራን፣ ከመደበኛ ምእመናን) መርጠው ወደ ወረዳ ይልካሉ።
በዚህ እርከን ውስጥ የሚፈፀመው ምርጫ እንደሌሎች እርከኖች በውክልና ሳይሆን በቀጥታ ተሳትፎ የሚከናወን ይሆናል። ሌሎች እርከኖች ላይ ግን ከታችኘው እርከን በቀጥታ በተመረጡ ወኪሎች አማካኝነት ምርጫው ይከናወናል።
2:- የወረዳ እስልምና ጉዳይ ምክር-ቤት
በአንድ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የዝቅተኛው እርከን የመጅሊስ መዋቅሮች (የጁምዓ መስጅዶች) የወከሉዋቸው መደበኛ ምእመናን፣ ዑለማ እና ምሁራን በየመንፈቅአመቱ አንዴ የሚሰበሰብ የወረዳ እስልምናጉዳይ ምክርቤት ጠቅላላ ጉባኤን ይመሰርታሉ።
3:- የዞን ወይም የክፍለከተማ መጅሊስ
የዞን ወይም የክፍለከተማ መጅሊስ የወረዳመጅሊስ በተቋቋመበት አኳኇን ይደራጃል። የየወረዳው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት(ከሶስቱም ዘርፍ የተወከሉ መሆን አለባቸው) የእርከኑን መጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ይመሰርታሉ።
4:- የክልል መጅሊስ እና የዲያስፖራ ሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች
የሁሉም ዞኖች የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአመት ሁለት ጊዜ የሚሰበሰበውንየክልሉን መጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤን ይመሰርታሉ። ጠቅላላ ጉባኤውም የስራ አስፈፃሚ አባላትን የዘርፍ እና የአከባቢተዋፅኦን አመጣጥኖ ከመካከላቸው ይመርጣል። ቀጥሎም ርእሰ መጅሊሱን እና ዋና ፀሀፊውን በስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ አቅራቢነት በቅድሚያ የሚሰይም ሲሆን የቀሩትን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለሁለት በመክፈል በየሁለት አመቱ የሚፈራረቁ መደበኛና ቋሚ የስራ አስፈፃሚኮሚቴ አባላትን ይለያል።
በሌላ በኩል የዑለማ ምክርቤት እና የሙስሊም ምሁራን መንፈሳዊ ማህበር በበታች እርክርን በተገለፀው የአወቃቀር ስልት የመጅሊስ መዋቅር አካል ሆነው መደራጀት ይኖርባቸዋል። ህጋዊ ህልውናቸው በመጅሊስ ስር የሚተዳደር በመሆኑ የተለየና የተነጠለ ትቋማዊ ህልውና ሊኖረው አይገባም በተለይ የማህበረ ቅዱሳንን ልምድ በመቀመር የተሞክሮ ልውውጥ ሊደረግ ይገባል።
በየክፍለ አህጉሩ የሚገኙና በሚኖሩበት ሀገር ስብስባቸውን አስመዝግበው የህግ ሰውነት ያገኙ ማህበረሰቦች የመጅሊስ መዋቅር አካል ሆነው እያንዳንዳቸው አንድወኪላቸውን የጠቅላላ ጉባኤው ልዩ በማድረግ እያንዳንዱ ክፍለ አህጉር እንደክልል መጅሊስ በአንድ አባል ይወከላሉ።
5:- ማእከላዊ መጅሊስ (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር-ቤት)
የሁሉም ክልል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአመት ሁለት ጊዜ የሚሰበሰበውንየማእከላዊውን ምውጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ይመሰርታሉ። የማእከላዊ ጠቅላላ ጉባኤም በተማሳሳይ መልኩ በሁሉም ዘርፍ ስብጥሩንየጠበቀ የክልል ተዋፅኦን ግምት ውስጥ አስገብቶ ከየክልሉ በሶስት ዘርፍ ሶስት ሶስት ተወካዮችን በመምረጥ የበላዩን መጅሊስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን ያደራጃሉ።
እንግዲህ ከላይ ያስቀመጥነው “የኢትዮጵያ መጅሊስ አጣዳፊ ችግሮቹ እናአማራጭ መፍትሔዎች” ከሚለው መፅሐፍ ምእራፍ አምስት የወፍ በረር ቅኝት ሲሆን መፅሀፉ የምርጫ ስርዓቱን ጨምሮ የመጅሊስመዋቅር ምን መምሰል እንደሚገባው በዝርዝር እና በጥልቀት የሌሎች ሀይማኖትተቋማትን ተሞክሮ ባማካተት ዘርዝሯል። ሁሉም ሙስሊም መፅሐፉን ገዝቶ ማንበብ ይጠበቅበታል። ችግራችንን ከማሳየት በዘለለ መፍትሔውም ምን ሊሆን እንደሚገባበደንብ የተቃኘበት መፅሐፍ በመሆኑ ጠቀሜታው የላቀ ነው።

No comments:
Post a Comment