Saturday, September 8, 2012

የቀጣይ ትግላችንን አቅጣጫ ያመላከተ የመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዒድ ውሎ
ቻችን ለዚህ እለት ለመጠቀም አንሰስትም፡፡ ያለንን ውድ ነገሮች መቸር ለምደናልና በአመት አንዴ ብቻ የምናገኘውን የዒደል ፊጥርን ውድ እለታችንን ለዚሁ የመብት ጥያቄ ጉዳያችን ለመሰዋት ወሰንን፡፡ ያቀረብነው መሰዋእትም እንዲሁ ከንቱ አልቀረም፡፡ ሃገራችን አይታ የማታውቀው ታሪካዊ እለት ሆኖ አለፈ እንጂ፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን እንዲሁም በርካታ የሃገራችን የዒድ አደባባዮችን ማዕከል አድርጎ ተስተጋባ፡፡መላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከህይወታችን በላይ በሆነው ዲናችን ላይ የተቃጣውን ዘመቻ በመቃወም ሁለነገራችንን መሰዋእት ካቀረብን አመት ሊሞላን ነው፡፡ ግዜያችንን፤ ጉልበታችንን፤ የምናከብራቸውንና ለነሱ ፊዳ ብንሆን ደስ የሚለን ውድ ኮሚቴዎቻችንን፤ የዲን አማናቸውን በሚገባ የተወጡ ዱአቶቻችንን፤ እራሳቸውን ለኛ ሲሉ ከፊት በመሰለፍ መሰዋእት ያደረጉ የኢስላም አገልጋይ ወንድምና እህቶቻችንን፤ ሌላም፤ ሌላም፡፡ ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈልንበት ጉዳይ ግን አሁንም ተገቢ ምላሽ እየተሰጠው አይደለም፡፡ ዒድ የደስታ ቀናችን እንደመሆኑ መጠን ደስ የሚያሰኙ ነገሮ የዒድ ተቃውሞአችን ለእኛው ለባለጉዳዮቹ፤ ከዳር ሁነው ለሚታዘቡ፣ ለሌላ እምነት ተከታዮች፤ ለሃገር ውስጥና አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ለመላው በፍትህ እጦት ስር ለወደቁ ሰላማዊ ዜጎች አስደማሚነቱ ወደር የሌለው የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ጥሪ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህ እለት ተዘርዝረው የማያልቁ ድንቅ መገለጫዎች ቢኖሩትም ጥቂቶቹን እነሆ፡-


ባለቤቱ ህዝብ መሆኑ፡- አመት ሊሞላው የተቃረበውን የተቃውሞ ሂደታችንን መሪው እከሌ ነው ብለው በማሰር ለማስቆም ቢሞክሩም ጉዳዩ ከህዝብ መነጠል የተቻለ አልሆነም፡፡ ጉዳዩ የመላው ሙስሊም ጉዳይ በመሆኑ ሺዎችን በእስር ቢያጉሩም ሺዎች ይተኩታል፡፡ ይህ እውነት ደግሞ ከምንም በላይ በዒድ እለት ፍንትው ብሎ ታይቷል፡፡ መላው ሙስሊም ህብረተሰብ ለረጅም ወራት በጉጉት ሲጠብቀው በነበረው በዒድ እለት ሁሉም አስተባባሪ የሆነበት የቃላት ሙገሳ የማያረካው አይነት የህዝብ ባለቤትነት ታየ፡፡ ማንም ከሚጠብቀው በላይ የታፈኑ የአዛውንቶች፤ የሴቶች፤ የእናቶችና የአባቶች የመብት ናፋቂነት ጥሪ በረጅሙ ተስተጋባ፡፡ አመት ያልሞላቸው ህፃናት በተፈተሹበት ውሎ በሺዎች የሚቆጠሩ መፈክሮች ውሎውን በድምቀት አጀቡት፡፡ በእለቱ የተከናወኑ እያንዳንዷ ክስተት ጠንሳሹም ሆነ ፈፃሚው መላው ሙስሊም ነው፡፡ ይህ ህዝብ መብቱን ለመጠየቅ አጋጣሚ የሚጠብቅ እንጂ የማይፈራ መሆኑን በተግባር አሳየ፡፡ የትግሉ ሂደትም በፅኑ ህዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን አውቀው ላልተኙ ታዛቢዎች በግላጭ አሳየ፡፡


የዒድ ውሎ ይህን ህዝብ ዳግም ለማታለል መሞከርም ሆነ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ መጣር መዘዙ የከፋ እንደሚሆን ከባድ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፈ የሚሊዮኖች ትንግርታዊ የጀግንነት ታሪክ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ትውልድ ጀግና ነው፡፡ የዚህ ትውልድ አባል መሆን ምንኛ ያኮራል!! በዚያ ታሪካዊ የዒድ እለት የእድሜያቸውን የመጨረሻ ግዜ ለዲን ልእልና ለመስጠት የቆረጡና ከኔ ቀሪ እድሜ የቀሪው ትውልድ ህይወት ያሳስበኛል የሚሉ እናትና አባቶች ምነው ዝርያቸውን አብዝተውልን በሄዱ በሚል ያስመኛል!! በዲናቸው መነካት እረፍት በማጣት በኢስላም ላይ ከሚፈጠር ጉዳት እኔ ቤዛ ልሁን ሲሉ ለተመልካች የሚደንቅ አይነት ወኔ የተላበሱ ወንድሞች እነሱን መሰል ደጋግሞ ወልዶ ደጋግሞ ማሳደግ ያስመኛል!! እነዚህ ወጣቶች ሁሉም ዘመን የራሱ የሆነ ታሪክ ሰሪ ጀግና እንዳለውም ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው፡፡ የእዝነት ባህሪያቸው ከዲን በላይ የሚሳሳለት እንደሌለው አውቆ በእንባ እየታጠቡ በሌላ በኩል ደግሞ የነዚያን ድንቅ የሰሃቢያት ታሪክን የሚያስታውስ የሚያስደምም ቁርጠኝነት ያሳዩትን እህቶች ላየ ሚሊዮኖችን በተኩ ያስመኛል!! የነገዋ ኢትዮጵያም በነዚህ ድንቅ እህቶች ፍሬ እንደሚሞሉ ማሰብ ምንኛ ያስቀናል!! በተለምዶ ነብስ ያላወቁ የሚባሉት ህፃናት የነበራቸው እልህ የተሞላበት ተሳትፎ ለተመለከተ በነዚህ ታዳጊዎች ነገ የሚኖረውን ትውልድ ለማየት ያስናፍቃል!! የኢትዮጵያ ሙስሊም በዲኑ ጉዳይ የመጣውን ሁሉ ለመቀበል በዘር ሽኩቻ፤ በስልጣን ጥማት፤ በነዋይ ናፍቆት…..በየትኛውም አይነት አለማዊ አጀንዳ ያልተነካካ ንፁህ የዲን ፍቅር እንዳለው ያስመሰከረ ትውልድ መሆኑን ያቺ እለት ምስክር ነች፡፡ ያቺ እለት ዳግም ላትመለስ ምስክርነቷን የቂያማ እለት ልትሰጥ ሄዳለችና መልካም ምስክርነቷንና በሷ ሰበብ የሚኖረውን ምንዳ ከአላህ እጅጉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡


ግዜውን የጠበቀ መሆኑ፡- ትክክለኛ ስራ በተሳሳተ ግዜ ከተሰራ የተሳሳተ ውጤት ያመጣል የሚባል ብሂል አለ፡፡ ህዝባችንም ለዚህ እውነት ነጋሪ ሳያሻው ትክክለኛውን ውሳኔ በትክክለኛው ሰአት ወስኗል፡፡ በተለይም በቀጣይነት ለሚወስዱት እርምጃ የኢድ ውሎን እንደ አንድ መስፈርት ቆጥረው ለነበሩ አካላት ህዝብ ቢታፈን አጋጣሚውን ሲያገኝ ነፃነቱን እንደሚያውጅ፤ አወሊያና አንዋር ለተቃውሞ አለመውጣት በዲናችን ላይ ለከፈቱት ግልፅ ጦርነት እጅ መስጠት እንዳልሆነ በትክክለኛው ሰአት አሳይቷል፡፡ የተቃውሞ ሂደታችንን ሰላማዊነት ያስተባበሉና ለማየት አጋጣሚውን ላላገኙት በተግባር ለማሳየት ዒድ ትክክለኛ ግዜ ነበርና ሚሊዮኖች በመሆን ትክክለኛውን ውሳኔ ህዝቡ ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ህዝቡ በነገው ሂደቱ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ላይ አስቀድሞ ለመተማመን የሚያስችል አይነት ስሜት የሚፈጥር ነው፡፡ ከምንም ነገር በላይ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ በመላው ሃገሪቱ በእስር እየማቀቁ በሚገኙበትና ሌሎችን በሰበብ አስባቡ እንደበግ እየተጎተቱ ወደእስር በሚወረወሩበት ተጨባጭ ድምፁን እንዲህ ባለ መልኩ ማሰማት አማራጭ የሌለው ነበርና ውሳኔው በጣሙን ሰአቱን የጠበቀ ነበር፡፡ ይህን ከመሰለው የመላው ሙስሊም ስሞታ በኋላ ከዚህ በፊት የነበረውን የጭፍን እርምጃ መንግስት ከገፋበት ትርጉሙ ግልፅ ነው፡፡ ይኸውም፡-

1. ለህዝብ ያለው መልእክት፡- እንዲህ ሚሊዮኖች ሁናችሁ በአደባባይ ያለአንዳች ጠጠር ውርወራ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› በማለት ጮሃችሁ መፍትሄ ካጣችሁ መሰረታዊ ችግሩ የመጅሊስ ጉዳይ አለመሆኑን ሲሆን

2. ለመንግስት ደግሞ ያለው መልእክት፡- ህዝብ መብቱን በሰላም ለመጠየቅ ሚሊዮኖች ሆኖ በአንድነትና በፅናት ከቆመ ለመብቱ መከበርም ሰላማዊ ውጤት እስካመጡለት ድረስ እረጅም የሚባለውን መንገድ ሊጓዝ እንደሚችል፡፡

እነዚህ ሁለት መልእክቶች ለህዝባችን የማይነጋ ህዝባዊ መሰረት ያለው ጠንካራ ትግል ለማድረግ መንስኤም ጉልበትም ይሆኑታል፡፡ ለመንግስትም ጉዳዩን እንደከዚህ ቀደሙ በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረ ችግር እና በመጅሊስ ላይ የተነሳ ጥያቄ እያሉ የሚያስተባብሉበት ዘመን እያበቃ ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ለመውጣት ከማይቻል ውጥንቅጥ ውስጥ ሊገባ የሚችልበት በር መክፈት መሆኑን ያመላክታል፡፡ እናም ሁላችንም እንንቃ!! ሁላችንም እንዘጋጅ!! ሁላችንም እንፅና!! ድል ለሙእሚኖች የተገባች ነችና በአላህ ላይ ያለንን እምነት አጠናክረን ሰወኛ ሰበብን ግን አንጠፍጥፈን ለመጠቀም እንቁረጥ!!! የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስን የቀብር ስነስርዓት በማስመለከትና ለአዲሱ አመራር ግዜ ለመስጠት ተቃውሟችንን ጋብ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ በመንግስት አስፈፃሚዎች በኩል ግን ሃዘኑም የነካቸው ጥረታችንንም ያልተረዱት በሚመስል ሁኔታ ወከባውና እንግልቱን አጠናክረው ገፍተውበታል፡፡ በመሆኑም የብሔራዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴው የሀዘን ሥነ-ሥርዓቱ መጠናቀቁን እና በሀዘኑ ምክንያት ዝቅ ብሎ የነበረው የሀገሪቱ ባንዲራ ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ማወጁን ተከትሎ በቀጣይ እኛም ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ ተቃውሟችን በምንም መንገድ እንደማይቆም ደግመን እናውጃለን!! በጥያቄዎቻችን የማንደራደር ሰላማዊነታችንንም የማንስት መሆናችንን ይፋ እናውጃለን!!

የዒድን ውሎ ለመተንተን ቦታ ቢገድበንም ህዝባችንን ከማድነቅ ግን ለአፍታም አንቆጠብም፡፡ ይህ መሰሉን የፅኑ ህዝበ አጋርነት ያለው ትግልም በአላህ እገዛ ፍፃሜው ድል እንደሚሆን ሙሉ እምነቱ አለን፡፡ አላሁ አክበር!!

No comments:

Post a Comment