ጁመዓ ለአዲሱ መንግስት ድፃችንን በሰላማዊ መንገድ ለመጀመሪያ ግዜ እናሰማለን!!!
እየደረሰብን ያለው የህግ ጥሰት በአፋጣኝ እንዲቆም ተቃውሞአችንን እናሰማለን!!
ባለፉት የዝምታ ሳምንታት በሀገር ወዳድነት ስሜት ጋብ ያደረግነውን ተቃውሞ ለመቀጠል ባሳለፍነው ጁምዓ በሙሉ አቅም እና ወኔ ተነሳስተን ሳለ በድንገት መግታታችን ይታወሳል፡፡አዎን በእርግጥም ጥያቄያችን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽ ነውና የሚጠብቀው ባለፈው ሳምንት ተረጋግቶ ለጥሪያችን ምላሽ የሚሰጥ መንግስት ያልነበረ ሲሆን ጡንቻውን ከህዝብ ክብርና ከሃገር ጥቅም ጋር ላያመዛዝን የሚችል አካልም ሊኖር የሚችልበት እድል ሰፊ ነበር፡፡ ባለንበት ተጨባጭ ሃገርም ሆነ መንግስት በ

ተረጋጋ መንፈስ ላይ ይገኛሉና የፊታችን
ጁምዓ የድምፃችን ይሰማ ጥሪያችንን ለአዲሱ አመራር አሃዱ ብለን ማቅረብ እንጀምራለን፡፡ ተቃውሞአችን መቼም በማይናድ
ፅኑ ህዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን በዒድ ባሳየነው ታሪካዊ የተቃውሞ ትዕይንት አረጋግጠናል፡፡ ለዒድ ታሪክ
የሰራው ህዝብ እነሆ ዳግም በአንዋር በመገኘት የተቃውሞ ድምፁን ለማሰማት ጁመዓን በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል፡፡
በጁመዓ ተቃውሞ ምርጫን ቀርቶ መደበኛ ስራን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል አቅምም ሆነ መዋቅራዊ ብቃት በሌለው የኡለማ ምክርቤት ጀርባ በተደራጁ ህገወጥ አካላት ሊደረግ የተሰናዳውን ህገወጥ ምርጫን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ምርጫው ላይ አለመሳተፋችንን ብቻ ሳይሆን ህገወጥ በመሆኑ በምንም መልኩ ሊካሄድ እንደማይገባ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ የኡለማዎች ምክር ቤት የህዝቡን ሁኔታ በማየት የምርጫ ምዝገባን በማራዘም ስም ምርጫውን በአጠቃላይ የመሰረዝ አማራጭን ይዞ እየሰራ መሆኑን ምንጮች ዘግበዋል፡፡ በመሆኑም ጁመዓ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ፤ በመላ ሃገሪቱ በግፍ የታሰሩ ኮሚቴዎቻችንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን እንዲፈቱ እና የተጀመረው ህገወጥ ምርጫ በአፋጣኝ እንዲቆም አዲስ ለተዋቀረው መንግስት ድምፃችንን ከፍ አድርገን በመላ ሃገሪቱ ለመጀመሪያ ግዜ የምናሰማበት ወሳኝ ቀጠሮ ነው፡፡ በዚህም መሰረት
1. ሰላት ተሰግዶ እንዳበቃ በሰገድንበት ቦታ በመቆም ዛሬም እየተበደልን ሰላማዊ መሆናችንን ለማረጋገጥ ነጭ መሃረብ፤ ወረቀት ወይንም ሶፍት ለ 3 ደቂቃ እናውለበልባለን
2. ለ 3 ደቂቃ የፈጣሪያችንን ታላቅነትና የፍጡራንን ከንቱነት ‹‹አላሁ አክበር›› እያልን እንገልፃለን
3. ለ 3 ደቂቃ ጥያቄዎቻችን ዛሬም አልተመለሱምና፤ የታሰሩት እስከአሁንም እየማቀቁ ነውና፤ የምርጫ ድራማ ዛሬም አልቆመምና ‹‹ድምፃችን ይሰማ-----ጥያቄአችን ይመለስ›› በማለት ለአዲሱ አመራር እናሰማለን፡፡
4. አሁን የተጀመረው የምርጫ ድራማ ፍፁም ህገወጥ መሆኑን ለ 3 ደቂቃ ‹‹ምርጫው ህገወጥ›› በማለት እንቃወማለን
5. ለ 2 ደቂቃ ‹‹ሳይፈቱ ምርጫ የለም›› በሚል ዳግም በህገወጥ ምርጫ እንደማንሳተፍ ፅኑ አቋማችንን እንገልፃለን
6. በመጨረሻም በጠላት ሴራ ላንበታተን አንድ መሆናችንን ለ 1 ደቂቃ እጅ ለእጅ በመያያዝ ፅናታችንን አሳይተን እንለያያለን፡፡
ልብ እንበል፡- ይህ የሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያው ተቃውሞ እንደመሆኑ መጠን በሰላም ግን ደግሞ በድምቀት በማካሄድ በደማቁ ታሪካችን ላይ አንድ እርከን እንጨምርለታለን፡፡ ሁከት ፈጣሪዎች ባለመሆናችን መግለጫና ዛቻ ከአላማችን ቅንጣት አያዘናጉንም፡፡
በአንድ ብር ታሪክ እንስራ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን እየገለፅን የጁምዓውን ጥሪ ፌስ ቡክ ለማይጠቀሙ በማስተላለፍ ኃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ ጁምዓን በአንዋር!!! አላሁ አክበር!!!

No comments:
Post a Comment