Saturday, September 29, 2012

ባንድራ በማቃጠል ሰላማዊ ተቃውሞአችንን ማጠልሸት አይቻላችሁም !!

ጸማቸውም የዚሁ እንቅስቃሴያቸው መገለጫ አንዱ ማሳያ ነው:: ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመልዕክተኛውን ክብር የሚነካ ተግባር መፈጸሙ እጅግ ቢያሳዝነውም በምንም መልኩ የአገራትን ክብር በሚነካ ሁኔታ የተፈጸመው ባንዲራ የማቃጠል ስራ ግን አይወክለውም፡፡ የዛሬው ተቃውሞም ሲጠራ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ በመንግስትና በመጅሊስ ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ከማውገዝ የዘለለ ሌላ አጀንዳ አልነበረውም፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላማዊ ተቃውሞው ውስጥ እስከዛሬ ድረስ ከህገ-ወጥ የመንግስት አካላት እንኳ ለደረሰበት የጭፍጨፋ ተግባር ምንም አይነት አፀፋዊ መልስ ባለመስጠት ያስመዘገበው ታሪካዊ ሂደት ደማቅ ነው :: በአንዋር መስጊድ መንግስት የሃይል እርምጃ በወሰደበት ዕለት መስጊዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ 40 ሺህ በላይ የሚሆን ሰው ተቃውሞ እያሰማ የነበረ ቢሆንም በተደጋገሚ ከሁሉም ይሰማ የነበረው “ ኮሚቴዎቻችን የፈለገ የህግ ጥሰት ቢካሄድብን እንኳ ምንግዜም ሰላማዊነታችንን እነዳንዘነጋ ያሉንን አንርሳ …” በሚል አንዱ ለአንዱ በማስታወስና እርስበርስ በመጽናናት ወደ አመጽ ሳይገባ መንግስትም የፈለገው ሳይሳካለት ጉዳታችንን በአላህ ብርታት ችለን ጉዟችንን መቀጠላችን ለሰላማዊነታችን ትልቅ ምሳሌ ነው:: ሰላማዊነት ድርጊቱ የሆነ ህዝብና የህግ ጥሰት ለፈጸመበት የህግ አካል እንኳ “ ህገመንግስቱ ይከበር ፤ ድምፃችን ይሰማ …” ከማለት ያልዘለለ ጀግና ትውልድ የዚህ አይነት ተግባር ይፈፅማል ብሎ ማሰብ ለማንም አይዋጥም :: በመሆኑም እንቅስቃሴውን ለማጠልሸት የሚደረገው ሩጫ ሁሉ በፍጹም አይሳካም ለማለት እንወዳለን :: በተለይ በአሁኑ ሰአት የውጭ መንግስታት ሳይቀር ለዚህ ሰላማዊ ህዝብና ላቀረበው የዜግነትና የሀይማኖት ጥያቄ መልስ መስጠት እንደሚሻል እያሳሰቡና በመንግስትም ላይ ጫና እያረበቱ ሲመጡ መንግስትና መጅሊስ መሰል የማስቀየሻ እስትራቴጅዎችን ለመጠቀም መሞከራቸው ባይገርመንም እኛ ሙስሊሞች መንቃታችንን ግን በግልፅ እንነግራቸዋለን:: በሰላማዊ ተቃውሞ ውስጥ የሚከፈለው ዋጋ ከባድ ቢሆንም እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ የሰላም ጥሪ እንደሚሆኑ ዛሬም ልናሳውቃቸው እንወዳለን :: ከተንኮላችሁም በአላህ እንጠበቃለን::ለመጅሊስና መንግስት አካላት ግልፅ መልእክት፡- "ባንድራ በማቃጠል ሰላማዊ ተቃውሞአችንን ማጠልሸት አይቻላችሁም !!"
ምስጋና ለአለማት ጌታ የተገባው ይሁን፡፡ በታላቁ አንዋር መስጊድና በአገሪቱ ባሉ ከተሞች ህዝበ ሙስሊሙ ለአዲሱ የመንግስት አመራር ሰላማዊ ጥያቄውን በሰላማዊና በተገቢ መንገድ በተሳካ ሁኔታ ዛሬም እንደወትሮው ማሰማት ችሏል:: ሆኖም የዚህ ህዝብ ሰላማዊነት ራስ ምታት የሆነባቸው የመጅሊስና የመንግስት አካላት ሁሌም እንቅስቃሴውን ከሰላማዊነት የሚወጣበትን ሴራ ከመሸረብ አይቦዝኑም:: በዛሬው ዕለት በአንዋር መስጊድ በተደረገው ሰላማዊ ተቃውሞ ፕሮግራም ላይ ጥቂት ግለሰቦች የሀገራትን ባንዲራ የማቃጠል ተግባር መፈ

No comments:

Post a Comment