ሰበር ዜና!!!
ሰመራ፣ አፋር፡፡
የፌደራል መጅሊስ ልዑካን በአፋር ክልል የኃፍረት ማቅ ተከናንበው ተመለሱ!
****
አፋሮች ‹‹ለፌደራል መጅሊስ ተወካያችንን ራሳችን መርጠን እንልካለን እንጂ እናንተ በምትፈልጉት መንገድ መርጠን አንልክም›› ብለዋል!!
****
ከሁለት ቀናት በፊት ከፌደራሉ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት (መጅሊስ) የተላኩ ግለሰቦች በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ ከየወረዳው የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን ሰብስበው ስለ ምርጫ ጉዳይ ለማነጋገር ባደረጉት ሙከራ ከተሰብሳቢዎች አስደንጋጭ ምላሽ ተሰጥቷቸው በኃፍረት ለመመለስ መገደዳቸውን የታመኑ ምንጮች ገለፁ፡፡
የፌደራሉ መጅሊስ ልዑካን አባላት ወደ አፋር ክልል የመጡት በሐገር አቀፉ የመጅሊስ ምርጫ ዙርያ የአፈፃፀም መመሪያ ለማስተላለፍ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ ከተሰብሳቢዎቹ፣ ‹‹ማን ነው የላካችሁ›› የሚል ጥያቄ እንደቀረበላቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
የልዑካኑ አባላት የተላኩት በመንግሥት መሆኑን መናገራቸውን ተከትሎ ተሰብሳቢዎቹ፣ ‹‹መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ሊገባ አይችልም›› የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር “የመጅሊስ ምርጫን በተመለከተ፣ እኛ በራሳችን መንገድ መርጠን ተወካያችንን እንልካለን እንጂ እናንተ በምትፈልጉት መንገድ መርጠን አንልክም” ሲሉ የማያዳግም ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡
ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንድ የክልሉ መንግሥት ባለሥልጣን ለመንግጅሊሱ ልዑካን፣ ‹‹እናንተ እዚህ እየመጣችሁ ህዝቡን በመከፋፈል እርስ በእርስ ልታጋጩን ስለሆነ አንቀበላችሁም›› በማለት የተናገራቸው ሲኾን፣ ይህንኑ አቋም የክልሉ መጅሊስ አባልን ጨምሮ የተለያዩ ተሰብሳቢዎች አጠናክረው ካስተጋቡት በኋላ ተሰብሳቢው በሙሉ ቤቱን በተክቢራ እንዳናወጡት ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል፡፡
በመጨረሻም የፌደራሉ መጅሊስ ልዑካን፣ ‹‹ራሳችን መጥተን ምርጫውን በምንፈልገው መንገድ እናስፈፅማለን የምትሉ ከሆነ ለሚፈጠረው ነገር ክልሉ ተጠያቂ እንደማይሆን፣ ማንኛውም ችግር ቢፈጠር እናንተ በኃላፊነት የምትጠየቁበት መሆኑን እንድታውቁ›› የሚል ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣቸው ምንም ሳያደርጉ በመጡበት ሁኔታ ሹልክ ብለው ተመልሰዋል፡፡
ከዚህ ቀደም መጅሊሱ ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአፋር ክልል የአህባሽ ሥልጠናን ባዘጋጀበት ወቅት ችግር ተፈጥሮ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት፣ ‹‹እንግዶቹን ዝም ብላችሁ ስሟቸውና ስብሰባውን በሰላም አጠናቅቁ፤ በግድ ተቀበሉ የሚላችሁ የለም›› በሚል ተሰብሳቢውን አረጋግተውት እንደነበረ ያወሱት ምንጮቻችን፣ በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ግን ‹‹በባህላችን እንግዳ ስለሚከበር የምትሉትን እየሰማን እስከዛሬ አብረናችሁ ቆይተናል፤ ከዛሬ በኋላ ግን ወደዚህ ድርሽ እንዳትሉ” በማለት ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንዳሰናበቷቸው አስታውሰዋል፡፡
የፌደራሉ መንግሥት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አካል የሆነው የዑለማ ም/ቤት መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ከዳር እስከ ዳር እያሰማ ላለው ጩኸት እና ከእምነት የመነጨ የመብት ጥያቄ ቁብ ባለመስጠት የመጅሊስ ምርጫን መስከረም 27 እናካሂዳለን በሚል በማን አለብኝነት መንገታገታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ይህ ፀረ ሕዝብ አካሄድ በመጨረሻ ለአሳፋሪ ውርድት ሊዳርግ እንደሚችል የአፋር ክልል ተሞክሮ በግልፅ የሚያመላክት ሲሆን፣ ይኸው ሁኔታ በሌሎች አካባቢዎችም መደገሙ እንደማይቀር የሚገምቱ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት መንግሥት ራሱን ከህዝብ ጋር ከማላተም ወደ አቅሉ ተመልሶ ነገሮችን በሰከነ መንገድ ቢያጤን መልካም እንደሆነ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡

No comments:
Post a Comment