በአላህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩሕሩሕ
ዲሞክራሲና ተገላቢጦሹ፣ ብዙሃን ይቃወማሉ ጥቂቶች ይደመጣሉ
(ጁምዓ መስከረም 18 2005)
ዲሞክራሲና ተገላቢጦሹ፣ ብዙሃን ይቃወማሉ ጥቂቶች ይደመጣሉ
(ጁምዓ መስከረም 18 2005)
በዛሬው ዕለት የታላቁ አንዋር መስጂድን ጨምሮ በክልል ከተሞች ከፍተኛ ሕዝባዊ የተቃውሞ ትዕይን ተካሄዶ ዋለ፡፡ አልሐምዱሊላህ፡፡ በካድሬዎችና ኮፊያ በለበሱ የመንግስት
ደሕንነቶች ታጅበው በየቤቱ በመዞር ቅስቀሳ በማድረጋቸው ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ይመዘገባል ብለው ቢጠብቁም ይህ ስራቸው
ይበልጥ የሕዝብን ቁጣ ቀስቅሶ እነሆ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ሙስሊም ዛሬም እንደትላንቱ ለተቃውሞ አደባባይ
ዋለ፡፡
ዲሞክራሲ የብዙኃን ድምጽ መደመጥ እንዳለበት ቢያትትም በተጨባጭ እየሆነና እየተመለከትነው ያለነው ነገር ግን አሳፋሪና አሳዛኝ ነው፡፡ መንግስት ባለበትና ሕግ የበላይ በሆነበት ምድር ዓይን ያወጣ ሕገ ወጥነት ተንሰራፍቷል፡፡ ከማውገዝ በዘለለ ይህንን ሕገ ወጥ ሒደት ለማስቆም ምን ዓይነት እርምጃ መሰሰድ እንዳለበት ግራ የሚያጋባ ስራ በጥቂት ማን አለብኝ ባዮች ሲፈጸም ማየት እጅግ አሳፋሪ ነው ብሎ ማለፍም ይከብዳል፡፡እየሆነ ያለው ግን ይኸው ነው፡፡
ሕዝብ ምን ግዜም ያሸንፋል! የሕዝብ አቅም ይኸው ነው፡፡ “ምንም አያመጡም፣ ጮኸው ጮኸው ሲደክማቸው ይተውታል፣ ቢጮኹ ምን አገባን ስልጣናችንን እስካልነኩ ድረስ፣ እነሱም ይጩኹ እኛም ስራችንን እንቀጥላለን…” እያሉ ባደባባይ የሚያወሩትን እንሰማለን፡፡እንዲህም ሆኖ እኛም መጮኻችንን እንቀጥላለን፡፡
ባጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ሆኖ የምናየው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በየቤቱ እየዞሩ በማስፈራራት ጭምር መዝግበነዋል ካሉት ሕዝብና ና ምርጫውን በመቃወም ያለ ምንም ማስፈራራት በሙሉ ፈቃደኝነት አደባባይ ከወጣው ሕዝብ የትኛው እንሚልቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፈርዳል፡፡የነማን ድምፅ እየተከበረ እና የነማን እየታፈነ እንደሆነ በውል ይገነዘባል፡፡
በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ እና በክልል ከተሞች ለተቃውሞ የወጣው ሕዝብ ዛሬም ታሪክ መስራቱን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡በተለይም በአንዋር መስጂድ የነበረው የተቃውሞ ትዕይንት ፍፁም ጨዋነት የተስተዋለበት እና የተዘጋጀውን መርኃ ግብር ባከበረ ሁኔታ በሠላም የተጠናቀቀ ሆኗል፡፡አልሐምዱሊላህ፡፡
ሕገ ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ለሕዝብ ባላቸው ከፍተኛ ንቀት እና ደረታቸውን በነፋው የመንግስት ጉልበት በመተማመን የሕዝብን መብት እንዳሻቸው እየተጫወቱበት ብንመለከትም የነሱ ሕገ ወጥነት አንድ ቀን መቀመቅ እንደፈሚያወርዳቸው እርግጠኞች ነን-ኢንሻ አላህ፡፡ ዲሞክራሲ እና ሕገ መንግስቱ በሚፈቅዱት እና ከነሱ በተቀዳው መርህ በመመራት ፍፁም ታሪካዊውንና አስደናቂ የሆነውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሂደታችንን እስከ መጨረሻው እንገፋበታለን-ኢንሻ አላህ፡፡በዚህ ሒደት መቀጠል እርግጠኝነት ላይ ፍፁም የማያወላዳ አቋም ስንይዝ ከመታፈሳችን፣ከመንገላታችን፣ከመታሰራችን… ጋር ህገ መንግስታዊ መርሆዎችን ለማክበር ያለንን ቁርጠኝነትንም ላፍታም አንዘነጋውም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊን ሙስሊሞች ነን፣ “ፅንፈኞች፣አክራሪዎች፣ አሸባሪዎች…” ሳንሆን ንፁህ ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ፍፁም ከፖለቲካ ጋር ንክኪ የሌለው ኃይማታዊ የመብት ጥያቄ ያነሳን ዜጎች ነን፡፡ ይህን መብታችንን ለመጠየቅ ሳናቅማማ ትግላችንን ስንቀጥል እንደ ዜጋ ግዴታችንን መወጣታችንን ላፍታ ዘንግተነው አናወቅም፣አንዘነጋውምም፡፡ ለዚህም ላለፉት 10 ወራት ባሳየናቸው የተቃውሞ ሂዶቶች የነበሩን ባሕሪያት እኛን በትክክል የሚወክሉ ናቸው፡፡ በተቃውሞ ሒደታችን መካከል መላ ኢትዮጵያዊያኖች ባሳለፏቸው መልካምም ሆኑ መልካም ያልሆኑ አጋጣሚዎች ሙሉ ተሳታፊዎች በመሆን እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ከኛ የሚጠበቀውን መወጣታችን እማኝ የማያሻው ሀቅ ነው፡፡ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሕገ መንግስቱን የማስጠበቅ፣ የዜጎችን ሠላም የማስከበር ና መሰል ተያያዥነት ያላቸው ኃላፊነቶች እንዳሉባቸው እናምናለን፡፡ይሁንና እኛም መብታችን ተጥሷል በማለት ለተቃውሞ አደባባይ የወጣን ሙስሊሞች ዜጎች መሆናችን ሊታወቅ ገባል፡፡ በመሆኑም ተቃውሞው ከዒድ በኋላ ጋብ ካለ በኋላ በአዲስ መልክ ሲጀምር ተቃውሟችንን በሠላማዊ መንገድ ከማሰማት ጋር በተያያዘ ያጋጠመን ይህ ነው የሚባል ትንኮሳ፣ ረብሻም ሆነ ሁከት የለም፡፡ ይህ የሚያሳየው እውነታ ሲኖር ያነሳናቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል በመሆኑም ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሞ ማሰማታችንን እንቀጥላለን የሚለው አሻሚነት የሌለው ቀዳሚው ይሆናል፡፡ እንደ ስራ ኃላፊነት በዙሪያችን መገኘታችሁ የማያሰጋን ሲሆን ላለፉት ሁለት የተቃውሞ ሳምንታት ያሳያችሁን ዓይነት ባሕሪ በቀጣይም ሊኖር እንደሚገባ እናምናለን፡፡
ሕገ ወጥ የመጅሊስ አመራሮችና ጀሌዎቻቸው የ“ምርጫ” ምዝገባቸውን በማጠናቀቅ እንደተለመደው ለመስከረም 20 ጥሪ አድርገዋል፡፡እንዲህ እያሉ እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡የዛሬ ሳምንት በሚኖረን የተቃውሞ ውሎ ተቃውሟችንን በተጠናከረ ሁኔታ እናሰማለን፡፡
አላህ ይገዘን፡፡

No comments:
Post a Comment