Tuesday, September 4, 2012

Radio Bilal Sept 4, 2012 ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 29/2004



  1. በሻሸመኔ ኢማሞች  የተለየ እንቅስቃሴ ያላቸውን ግለሰቦች እንዲያጋልጡ ትዕዛዝ ደረሳቸው
  2. በአክሱም የሚገኙ ሙስሊሞች ሐይማኖታቸውን በነፃነት መተግበር እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
  3. በሱዳንና በደቡብ ሱዳን የጀመሩትን የሰላም ድርድር ሊቀጥሉ እንደሆነ ተገለፀ
  4. የአፍሪካ ልማት ባንክ 251 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር መስጠቱ ተጠቆመ
  
በሻሸመኔ ኢማሞች  የተለየ እንቅስቃሴ ያላቸውን ግለሰቦች እንዲያጋልጡ ትዕዛዝ ደረሳቸው
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 29/2004
          የሻሸመኔ ኢማሞቹ የደረሳቸው ትዕዛዝ በተለይ ከወቅታዊው የህዝበ ሙስሊም ጉዳይ ጋር ግንኙነት እና ተሳትፎ ያላቸውን ሙስሊም ግለሰቦች እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የመስጅድ ኢማሞቹ በመንግስት ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ተጠርተው በአካባቢያቸው እንቅስቃሴ ያላቸውና ሰላምን የሚያደፈርሱ ግለሰቦችን እንዲጠቁሙ ትዕዛዝ እንደደረሳቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
          ይህንንም ትዕዛዝ ተከትሎ በአካባቢው መስጅድ እንቅስቃሴ ያላቸው ግለሰቦች መካከል ሶስት ወጣቶች ለእስር እንደተዳረጉም ምንጫችን ጠቁመዋል፡፡ለወጣቶቹ መታሰር በዋነኛነት የቀረበባቸው ምክንያት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫን በተመለከተ ምርጫችን በመስጅዳችን መሆን አለበት የሚል አቋም ይዘው እንቅስቃሴ በማድረጋቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአክሱም የሚገኙ ሙስሊሞች ሐይማኖታቸውን በነፃነት መተግበር እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 29/2004
በአክሱም ከተማ የሚኖሩ ሙስሊም ምዕመናን ወቅታዊ የሰላት ስነ-ስርዓት እና አንዳንድ የዳዕዋ ስራዎችን የሚሰሩበት አንድም መስጂድ እንደሌላቸው በከተማዋ የሚኖሩ አንዳንድ የሬዲዮ ቢላል ምንጮች ገለፁ፡፡

በሱዳንና በደቡብ ሱዳን የጀመሩትን የሰላም ድርድር ሊቀጥሉ እንደሆነ ተገለፀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 29/2004
ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ነሐሴ 26/2004 በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ምክኒያት ቢራዘምም በያዝነው ሳምንት እንደሚቀጥል ተገለፀ፡፡
የሱዳን ተደራዳሪ ቡድን ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ሳብር ሐሰን ሁለቱም ሀገራት ተደራዳሪያቸውን በዚሁ ሳምንት እንደሚልኩ ገልፀዋል፡፡  ሁለቱ ሀገራት የሚያደርጉት ድርድር በአዋሳኝ የድንበር ግጭት የሚቆምበትንና አዋሳኝ ድንበር በመከለል አጀንዳ ላይ መሆኑ ተገልፆዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደቡብ ሱዳን ያቋረጠችውን እና በሱዳን በኩል ለገበያ የምታቀርበውን የነዳጅ ሀብቷን እንደገና በምትጀምርበት መንገድ ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መሰናዘሪያ ጋዜጣ ዘግቦታል፡፡
 --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የአፍሪካ ልማት ባንክ 251 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር መስጠቱ ተጠቆመ
አዲስ አበባ ነሐሴ 29/2004
          የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣይ ሶስት ዓመት ለሚመደበው በጀት ድጋፍ የሚሆን 251 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት መፈራረማቸው ተገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካይ ለሚን ባሮው መካከል ተገቢው የብደር ስምምነት መሰረት የብድር አገልግሎት ለተለያዩ ሁኔታዎች ይውላል ብለዋል ፡፡ የብድር አገልግሎቱም ለትምህርት ለጤና ለግብርና ለመንገድ ግንባታ ለንፅህና ውሃ አቅርቦትና ለሳኒቴሽን ኢትዮጲያ የምትመደበውን ጉድለት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከ2006 ጀምሮ የአሁኑን ጨምሮ በሶስት ፌዝ ለኢትዮጵያ የሰጠው ብድር ከ1.3ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መብለጡን የተወካዩ መረጃ ማመልከቱን መሰናዘሪያ ጋዜጣ ዘግቦታል፡፡

No comments:

Post a Comment